#IFTAR
ዛሬ እና ትላንት በተለያዩ ከተሞች ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ታካሂዷል።
የኢፍጣር ስነስርዓት ከተካሄደባቸው ከተሞች አንዷ መዲናችን አዲስ አበባ ስትሆን በቤተል አደባባይ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።
በደ/ወሎ ልጓማ ከተማ፣ ሶማሌ ክልል ቀብሪደሃር ከተማ ፣ በወራቤ ከተማ ፣ በአፋር ማንዳ ከተማ ፣ በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ፤ ኬራቴ ከተማ ፣ ሻሸመኔ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።
ትላንት ደግሞ ፤ በለገጣፎ ለገዳዲ ፣ በጅማ ዞን ኦማንዳ ወረዳ ፣ በኢሊአባቦር ዞን አልጌ ሰቺ ወረዳ ፣ ሰንዳፋ በኬ ፣ ቡራዩ ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ፣ ጅማ ዞን ዴዶ ወረዳ፣ በወልቃይት ሁመራ እና በወልቂጤ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።
የሁሉንም የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፎቶዎች ይመልከቱ ፦ https://telegra.ph/Iftar-04-22
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19Ethiopia - Health Worker Training Platform
ኮቪድ-19 ሰልጠና ሰርተፍኬትዎን አሁኑኑ በሰልክዎ ባለው መተግበሪያ መውሰድ ይችላሉ።
የኮቪድ-19 ስልጠና ወስደው ሰርተፍኬትዎን መውሰድ እንዴት እንደሚችሉ ለማወቅ ከላይ ቪድዮውን ይመልከቱ።
https://bit.ly/3apv5J2 ይህንን ማስፈንጠርያ በመጫን አፕልኬሽኑን ያዘምኑ።

#LineAddis
የከፍተኛ ትምህርትዎን በተለያዩ ሀገራት ለመማር በሚያደርጉት ሂደት የአድቫንስድ እንግሊዝኛ ስልጠና ፣ የዶክመንቴሽን ዝግጅት እንዲሁም የቅድመ እና ድህረ በረራ አገልግሎቶችን ቢፈልጉ ላይን አዲስ ኮንሰልታንሲ #ያማክርዎታል። ለተጨማሪ ቴሌግራም ቻነል @lineaddisconsultancy ይጎብኙ።
ስልክ፦ 0116671693 / 0115580951
አድራሻ ቦሌ ራክሲም ፕላዛ 5ኛ ፍሎር ወይንም ለቡ ፎዝያና ሕንፃ 5ኛ ፍሎር

#ዋግኽምራ 📍
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ፤ ዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን መጎብኘታቸውን ፅ/ቤታቸው አስታውቋል።
ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከማህበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀው እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ አመልክተዋል ተብሏል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚስተዋለውን የግጭት ሁኔታ አንስተውም ሰላምን ማስፈን የሰላማዊ ወኪል ለመሆን ወስኖ በቁርጠኝነት የሰላም እሴቶችን መገንባትን ይጠይቃል ማለታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
ዋግኽምራ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ፣ እንግልት እና ስቃይ የደረሰበት አካባቢ ሲሆን አሁንም ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው ይገኘሉ።

" ከሚያስፈልገው ጋር ሲነፃፀር በውቂያኖስ ላይ ጠብታ ውሃ እንደመጨረ ነው " - ዴቪድ ባስሌይ
በተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ወደ ትግራይ አንድ እርዳታ የጫነ ተሽከርካሪ ከመግባቱ በፊት 105 ቀናት ተቆጥረው እንደነበር አስታውሰዋል።
ከጥቂት ቀናቶች በፊት 2 ኮንቮዮች ምግብ፣ ነዳጅ እና መድሃኒት ይዘው ትግራይ መግባታቸውን አስታውሰው ፤ ይህም እጅግ አስፈላጊ እርምጃ ነው ብለዋል።
ነገር ግን በየቀኑ ከሚያስፈልገው የሰብዓዊ ፍላጎት ጋር ሲነጻጸር በውቅያኖስ ላይ አንዲት ጠብታ እንደመጨመር ያህል ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ባስሌይ ፤ ተጨማሪ መዘግየቶች በተፈጠሩ ቁጥር ውጤቱ ሰዎች በረሃብ እንዲሞቱ እንደሚያደርግ አስገዝበዋል።
"ሁሉም ወገኖች በጋራ ሆነው ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው ተደራሽነት እንዲኖር እና በሰሜን ኢትዮጵያ የህይወት አድን ዕርዳታን ለማድረስ አስፈላጊ የሆኑትን ኮሪደሮች እንዲከፍቱ እንፈልጋለን ፤ ይህም በፍጥነት መሆን አለበት ነው ያሉት።
ባስሌይ ፤ ያለው ሁኔታ ለሚሊዮኖች አስከፊ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

#እንድታውቁት
የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ #መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

#Ligebuoy
መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንልን! የበዓል ደስታችን እንዲዘልቅ እጃችንን በላይፍቦይ ታጥበን እንመገብ። ላይፍቦይ ከበሽታ አምጪ ባክቴሪያ እና ቫይረሶች ይከላከላል!!
#Lifebuoy #LifebuoyEthiopia #Handwashing #Easter #EthiopianEaster #holiday #Ethiopia

የትንሳኤ በዓል መልዕክት ፦
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦
" ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ መተባበር ለሁላችንም ክርስቲያኖች ሃይማኖታዊ ግዴታችን ነውና ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በትንሣኤው ዕለት ተርበውና ተጠምተው፣ ታርዘውና ተስፋ ቈርጠው መዋል ስለሌለባቸው በልዩ ልዩ ምክንያት መከራ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን የሚያስፈልጋቸውን በማቅረብ ፋሲካውን አብረናቸው እንድናከብር ነው፡፡
እንደዚሁም የሰላምና የፍቅር፣ የዕርቅና የይቅርታ ኃይሎች ሆነን በመመላለስ ሀገራችንን ከፈተና ሕዝባችንን ከሰቆቃው እንድንታደግ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ "
✝
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል
ሊቀጳጳሳት ዘካቶለካውያን
" በመጨረሻም ለመላው የአገራችን ሕዝቦች በሙሉ በየቤታችሁና በሆስፒታሎች ለምትገኙ ህሙማን ሁሉ ምሕረትን፣ በየማረሚያ ቤት ለምትገኙ የህግ ታራሚዎች መፈታትን፣ በስደት ላይ ያላችሁ ወደ አገራችሁና ወደ ቀያችሁ መመለስን፣ በጦርነትና በግጭት ቀጠናዎች መካከል ላላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሰላምን እየተመኘሁ ለሁላችሁም ክርስቲያን ወገኖች በድጋሚ እንኳን ለመድኃኒችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልጽላችሃለሁ "
✝
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርትሲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጄ ጀንበሩ፦
"የትንሳኤው መገለጫ ፍቅር በመሆኑ በዓሉን በፍቅርና በመተሳሰብ ማሳለፍ ይገባል። በዓሉን ተርበውና ተጠምተው ለተጨነቁ ወገኖችን እንዲሁም በሰላም እጦት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ተስፋቸው ለጨለመባቸው ወገኖችም ያለንን በማካፈል ማሳለፍ ይገባል"
ያንብቡ : telegra.ph/Easter-04-23

#Update
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ ዛሬ 74 ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ ትግራይ ክልል መላካቸውን አስታውቋል።
በ3ኛ ዙር ወደ ትግራይ ክልል ከተላኩት ተሽከርካሪዎች ውስጥ 6ቱ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ናቸው ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፥ በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ የገባውን ቃል በማክበር ምቹ የሰብአዊ ዕርዳታ ማጓጓዣ ሁኔታን ለመፍጠር እየሠራሁ ነው ብሏል።
ከዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እና ሌሎችም አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
በዚሁ መግለጫው በችግር ላይ ያሉ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ህወሓት አሁንም ከያዛቸው የአፋር እና አማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጣ ፤ ምቹ የእርዳታ ማስተላለፊያ መስመርን መዘርጋት እንዲቻል እንዲሁም ቡድኑ ከሚነዛቸው የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎች እንዲቆጠብ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ሊያደርግ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቧል።
በተጨማሪ እስካሁን ድረስ ያልተመለሱ 1 ሺህ 25 ተሽከርካሪዎች በፍጥነት እንዲመለሱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

#Ethiopian_Civil_Service_University
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በተመረጡ የት/ት መስኮች ለማስተማር መዘጋጀቱን አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በማታ እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር በ17 የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለማስተማር መወሰኑን ገልጿል።
በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርትን የምታሟሉ አመልካቾች ከሚያዝያ 24 እስከ ግንቦት 06/2014 ዓ.ም ምዝገባ ማከናወን ትችላላችሁ ተብሏል።
በ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላችሁ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና ኮፒውን እንዲሁም የመመዝገቢያ 150 ብር የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ ሲ.ኤም.ሲ. መንገድ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲው በተገለጹት ቀናት በመገኘት መመዝገብ ይቻላል።
(ትምህርት የሚሰጥባቸው መስኮች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity

የትንሣኤ ሎተሪ ወጣ !
የትንሣኤ ሎተሪ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 15/ 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል ፦
1ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0337949
2ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር1202412
3ኛ. 1,250,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0674207
4ኛ. 600,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0765249
5ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0554605
6ኛ 150,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር1127709
7ኛ.100,000 ብር የሚያስገኘው የ7ኛ ዕጣ ቁጥር 1750931
8ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 3,000 ብር የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 24699
9ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 74363
10ኛ.180 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 600 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 1684
11ኛ. 180 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 0538
12ኛ. 180 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 150 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 3850
13ኛ. 1,800 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 120 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 534
14ኛ. 1,800 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 90 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 687
15ኛ 18,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር45 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 50 (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 1 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡
ምንጭ፦ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር