TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰሜን_ኮሪያ ሰሜን ኮሪያ ሁለት የተጠረጠሩ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳኤሎችን (SRBM) በመዲናዋ ፒዮንግያንግ ከሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር ማሳወቁን ሮይተርስ ዘግቧል:: ጃፓን በተመሳሳይ መወንጨፉን ሪፖርት አድርጋ ድርጊቱን የሰላም እና የፀጥታ ጠንቅ ነው ስትል አውግዛለች። ቻይና በበኩሏ ሁሉም ወገኖች የቀጠናውን መረጋጋት እንዲያስጠብቁ ስትል አሳስባለች:: ዛሬ ሰሜን ኮሪያ…
#NorthKorea

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማክሰኞ 2 ተጨማሪ የክሩዝ ሚሳዬሎችን በመተኮስ መሞከሯን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታወቀ፡፡

ይህ በአዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት አምስተኛው የሚሳዬል ሙከራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ጦር ዝርዝሩ እየተጠና መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በአዲሱ ዓመት ውስጥ ብቻ ባደረገቸው 5 ሙከራዎች 8 ሚሳዬሎችን መተኮሷ ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1950 የተካሄደውን የኮሪያ ጦርነት ስምምንት መሠረት አሜሪካ በደቡብ ኮሪያ ወደ 28ሺ ወታደሮችን አስፍራለች፡፡

አሜሪካ ፤ የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ሙከራዎቹን በማወገዝ አሳሳቢ መሆናቸውንም እየገለጸች ሲሆን በተከታታይ የእንነጋገር ጥሪዋን ስታሰማ መቆየቷን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል አስወነጨፈች። ትላንትና ለሊት ሰሜን ኮሪያ የተጠረጠረ ባላስቲክ ሚሳኤል ወደ ምስራቅ ባህር ማስወንጨፏን ጎረቤቶቿ እየገለፁ ይገኛሉ። የደረሰ ጉዳት የለም። ፒዮንግያንግ ይህ የሚሳኤል ማስወንጨፍ ሙከራዋ 2022 ከገባ ጊዜ አንስቶ 9ኛው መሆኑ ነው። የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ የደህንነት ባለስልጣናት የሰሜን ኮሪያን እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተሉት ነው ተብሏል። @tikvahethiopia
#NorthKorea

ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራዋን ገፍታበታለች።

በዚህ አመት እጅግ ተደጋጋሚ የሚሳኤል ሙከራ ስታደርግ የነበረችው ሰሜን ኮሪያ በአመቱ 12ኛ ነው የተባለውን የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል።

ሰሜን ኮሪያ ትላንት ትላንት ቅዳሜ 2 ሚሳኤሎችን በሰሜን ምስራቅ የባህር ጠረፍ ላይ ከምትገኘው ሃምሁንግ ከተማ ማስወንጨፏ እና 68 ማይል መጓዛቸው ተነግሯል።

የአሁኑ ሙከራ ከቀድሞዎቹ በኃይል ያነሰ ቢሆንም በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ውጥረት ባለበት ሁኔታ ወቅት መፈፀሙ አሳሳቢ እንዳደረገው ተነግሯል።

በሌላ በኩል አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ዓመታዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን ሰኞ ይጀምራሉ። ይህን ልምምስ ሰሜን ኮሪያ በፅኑ አውግዛዋለች። ሀገሪቱ የሁለቱን አጋሮች የጋራ ልምምዶች እንደ ወረራ ልምምድ የሚቆጠር ነው ብላዋለች።

@tikvahethiopia
#USA #NorthKorea

አሜሪካ #ኑውክሌር_የመሸከም አቅም ያላቸውን " B-52 " ቦምብ ጣይ ጄቶቿን ዛሬ በደቡብ ኮሪያ አቅራቢያ ለልምምድ ማብረሯን ቪኦኤ ዘግቧል።

በረራው ከሰሜን ኮሪያ ሊመጣ የሚችልን ስጋት የመመከት አቅሟን ለማሳየት ነው ተብሏል። በተጨማሪም F-22 የተባሉትን ስቲልዝ ተዋጊ ጄትችንም ማብረሯ ተሰምቷል።

ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ F-35A እና F-15K ይተሰኙ ተዋጊ ጄቶቿን በልምምዱ ማሳተፏን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሀገራቱን ልምምዱን ያደረጉት በዚህ ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሚሳዬል ሙከራ ላደረገችውና በአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ላይ ዛቻዋ እየጨመረ ለመጣው ሰሜን ኮሪያ ጡንቻቸውን ለማሳየት እንደሆነ ነው የቪኦኤ ዘገባ የሚያስረዳው።

2ቱ አገሮች ወታደራዊ ልምምዳቸውን ለማጠናከርና በአሜሪካ በኩል የሚቀርቡትን የመሣሪያና ጄቶችን ቁጥር ለመጨመር፣ እንዲሁም አሜሪካ ደቡብ ኮሪያን ለመከላከል የገባቸውን ቃል በተግባር እንድታጠናክር ባለፈው ወር ተስማምተው ነበር።

የደቡብ ኮሪያው የመከላከያ ሚኒስቴር ፤ ያንን ስምምነት በመጥቀስ፣ ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌርና የሚሳዬል ዛቻ መልስ ለመስጠት ሁለቱ አጋሮች የመከላከያ ብቃታቸውን ማሳየታቸውን ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት ብቻ እጅግ ተደጋጋሚ ሚሳኤል ስታስወነጭፍ የነበር ሲሆን ከቀናት በፊትም መካከለኛ ርቀት ያላቸውን ባሊስቲክ ሁለት ሚሳዬሎች አስወንጭፋለች።

ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የስለላ ሳተላይት ለመላክ ወሳኝና የመጨረሻ ሙከራ ነው ማለቷን ዘግባው ያሳያል።

@tikvahethiopia