የቀድሞው ጉምቱ ባለስልጣን ፤ አሁን ላይ በባህር ዳር ከተማ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት አቶ በረከት ስምኦን የረሃብ አድማ መምታታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።
ትላንት ጀመሩት የተባለው ይህ የረሃብ አድማቸው መነሻው ለወራት ወደ አዲስ አበባ ለመዘዋወር ለማረሚያ ቤቱ ሲያቀርቡት የቆየ ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ነው ተብሏል።
የአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ግን አቶ በረከት የረሃብ አድማ ስለማድረጋቸው የማውቀው መረጃ የለም ብሏል።
አቶ በረከት መልካም በሆነ ጤንነት ላይ እንዳሉ እንጂ ረሃብ አድማ ስለማድረጋቸው አላቅም ያለው ኮሚሽኑ ጉዳዩን አጣርቼ አሳውቋለሁ ብሏል።
አቶ በረከት ከተፈረደባቸው የስድስት ዓመት እስር ውስጥ አንድ ሶስተኛውን አገባደው #በአመክሮ ከእስር ለመውጣት ጥያቄ አቅርበው ነበር።
አቶ በረከት ትላንት ጀምሮ መቱት የተባለውን የረሃብ አድማ በተመለከተ ባለቤታቸው ወ/ሮ አሲ ፈንቴ መረጃው እንዳላቸው ገልፀዋል።
ወ/ሮ ኢሲ ከአቶ በረከት ጋር አብረዋቸው ታስረው የቆዩት አቶ ታደሰ ካሳ በከፍተኛ ህመም ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ከመጡ 5 ወራት መቆጠራቸውን እና አቶ በረከት አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻቸው ታሰረው መቆየታቸው አንዱ ለረሃብ አድማው ምክንያት መሆኑ ገልፀዋል።
የረሃብ አድማው ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸውም ተናግረዋል።
ወ/ሮ አሲ ባለቤታቸው የልብ ህመም እንዳለባቸው እና በረሃቡ ምክንያት የከፋ አደጋ እንዳይደርስ ቤተሰባቸው ስጋት ውስጥ መውደቁን ገልፀዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-04-16-2
@tikvahethiopia