TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሜሪካ ከወራት በፊት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመቻቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ (ከሰኔ በፊት) ከስልጣናቸው ሊለቁ ነው።

ከስድስት ወር ላነሰ ጊዜ በልዩ መልዕክተኛነት ያገለገሉት ሳተርፊልድ ከስልጣናቸው ሲለቁ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ ፔይቶን ኖፕፍ ቦታውን እንደሚረከቡ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸድ ምንጮች መስማቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

በቅድሚያ የአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ ከኃላፊነታቸው ሊለቁ እንደሚችሉ መረጃውን ያወጣው ፎሬይን ፖሊሲ ሲሆን የእሳቸው ከኃላፊነት መልቀቅ፤ ከፍተኛ የፖለቲካ አለመራጋጋት፣ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እና የረሃብ ስጋት ባለበት የአፍሪካ ቀንድ ትልቅ የዲፕሎማሲ ክፍተት የሚፈጥር እንደሆነ አስፍሯል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ እና ምክትላቸው ኖፕፍ ዛሬ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ አስታውቋል።

2ቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጠናት ፣ ከዲፕሎማቲ አጋሮች እና ከረድዔት ድርጅቶች ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኃላፊነት መነሳት ላይ በይፋ የሰጠው አስተያየት አንደሌለ ሮይተርስ ፅፏል።

@tikvahethiopia
#ዋግኽምራ📍

ጦርነት ክፉኛ ከጎዳቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች አንዱ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ነው።

በእዚህ አካባቢ ያሉ ወገኖች ለከፋ ችግር ተጋልጠው ሜዳ ላይ መውደቃቸው እና አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጥሪ ሲቀርብ እንደነበር ይታወሳል።

ምንም እንኳን በቂ ባይሆንም የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ ተስተውሏል።

ዛሬ ከዋግ ኽምራ ኮሚኒኬሽን በተገኘ መረጃ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው በሰቆጣ መጠለያ ለሚገኙ የዋግ ተፈናቃዮች 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስንዴ (300 ኩንታል) ድጋፍ አድርጓል።

ዩኒቨርሲቲው በችግር ላይ ለወደቁት ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳውቋል።

በተጨማሪ በዞኑ የተለያዩ ምርምሮችን ተግባራዊ በማድረግ የህብረትሰቡን ችግር ለመፍታት የበኩሉን እንደሚወጣ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በከተማዋ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም የካዳስተር ምዝገባ እና እወጃ ሥራ እንደሚካሄድ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም የመሬት ይዞታቸውን በካዳስተር ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መረጃዎቻቸውን ለሚቀጥሉት ተከታታይ 15 ቀናት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ተነግሯል።

ከተማ አስተዳደሩ ከ10 ዓመት በፊት ጀምሮ ሕጋዊ የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ (ካዳስተር) ሥራ እየሠራ ሲሆን በዚህ ዓመት በመዲናዋ የለሚኩራ ክ/ከተማን ሳይጨምር በ10 ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ 25 ቀጠናዎች ላይ የመሬት ይዞታን የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራ እንደሚሠራ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት ይዞታ የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለ5 ወራት እንደሚሠራ ተመላክቷል፡፡

በዚህ ወቅት በሕግ ተይዘው ካሉ የመሬት ጉዳዮች እና የሕግ ክርክሮች ውጪ ምንም ዓይነት #የስም_ዝውውር_እንደማይካሄድ ነው የተገለጸው፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከ2008 ዓ. ም እስከ 2011 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ከ118 ሺህ በላይ የመሬት ይዞታዎችን እና ከ161 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በካዳስተር መመዝገቡ ተጠቁሟል።

ኤጀንሲው የምዝገባ ሒደቱ ተዓማኒ እንዲሆን ከማህበረሰቡ የተውጣጡ ታዛቢዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ማለቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ እና አንዋር መስጂድ አካባቢ ያሉት ስማርት የመኪና ማቆሚያዎች ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል።

መገናኛ ስማርት የመኪና ማቆሚያ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን መንስኤው የኤሌክትሪካል ቴክኒክ ችግር ነው ተብሏል።

አንዋር መስጂድ አካባቢ ያለው ስማርት የመኪና ማቆሚያ የኤሌክትሪክ መስመሩ በመቆረጡ አገልግሎት ሳይሰጥ እንደቆየ ተገልጿል።

አሁኑ ላይ ሁለቱም ስማርት የመኪና ማቆሚያዎች ተጠግነው #ለአገልግሎት_ክፍት መሆናቸውን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

መገናኛ ስማርት የመኪና ማቆሚያ 90 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ባለ 15 ደረጃ ያለው ሲሆን፥ ከአጠገቡ 105 መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችል የመሬት ላይ መኪና ማቆሚያ አለው፡፡

በተመሳሳይ በአንዋር መስጂድ አካባቢ ለ80 መኪናዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል፤ በመሬት ላይ ደግሞ 110 መኪናዎችን የመያዝ አቅም አለው፡፡

#AddisAbaba_Transport_Bureau

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ38 ዓመታት ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ትላንት አዲሱን…
#EthiopianAirlines

በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት አቶ መስፍን ጣሰው አዲስ የማኔጅመንት ቡድን አዋቅረዋል፡፡

በተዋቀረው በአዲሱ ማኔጅመንት ቡድን ቀደም ሲል በተጠባባቂነት የሃላፊነት ቦታዎች ይዘው ሲያገለግሉ የነበሩ ሀላፊዎች ቦታው ፀድቆላቸዋል።

አንዳንድ ሀላፊዎች ደግሞ ከቦታቸው ተነስተው በሌሎች ባልደረቦቻቸው መተካታቸውን " ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ " ዘግቧል።

(ዝርዝሩ ከላይ በምስሉ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Gambella

በጋምቤላ ክልል መዠንገር ዞን ፤ ሜጢ ከተማ ከፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደ ማረሚያ ቤት 22 እስረኞችን ሲመልስ የነበረ የፖሊስ ተሽከርካሪ ተገልብጦ ከባድ አደጋ መድረሱ ተሰምቷል።

በአደጋው የአንድ እስረኛ ህይወት አልፏል።

አጠቃላይ በተሽከርካሪው 22 እስረኞችና 4 የፖሊስ አባላት (26 ሰዎች) የአደጋው ሰለባ ሲሆኑ በአደጋው የሞት፣ ከባድ ፣እና ቀላል ጉዳት ተመዝግቧል።

የመዠንገር ዞን ፀጥታ መምሪያ ለሸገር ኤፍ ኤም በሰጠው ቃል ፤ መኪናው ከፊት ለፊት ባጃጅ ገብቶበት እሱን አድናለው ሲል መገልበጡን ገልጾ ጉዳት የደረሰባቸው እስረኞች እና የፖሊስ አባላት ቴፒ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ከእስረኞች መካከል ያመለጠ እንደሌለ ያሳወቀው ፀጥታ መምሪያው አንድ ታራሚ ህይወቱ እንዳለፈ ሌሎቹ ግን በሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

22ቱ ግለሰቦች በተለያየ ጥፋት ተጠርጥረው ማረሚያ የወረዱ መሆናቸውን የገለፀው የፀጥታ መምሪያው ከአዲስ አበባ የሚላክ " የስንዴ እርዳታ " ወደ ህዝብ ሳይደርስ መንገድ ላይ ሲሸጡ እና ለግል ጥቅም ሲያውሉ የነበሩ ሰዎች መኖራቸውን መጠቆሙን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሆን የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፅድቋል።

የዓለም ባንክ፥ በኢትዮጵያ በተከሰቱት ግጭቶች የሰው ህይወት መጥፋቱን ፣ ሰብአዊ ቀውሶች መከሰታቸውን፣ የግልና የመንግስት ንብረቶች መውደማቸውን እና ማህበረሰቦች ከፍተኛ ድጋፍ እንዲሹ ማድረጉን ገልጿል።

በተጨማሪ የተከሰቱ ግጭቶች በመላ ሀገሪቱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት መሆናቸውን እና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን (GBV) የበለጠ እንዲባባስ ማድረጉን አመልክቷል።

እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት እና ኢትዮጵያን ለመርዳት የዓለም ባንክ በግጭት ለተጎዱ ማህበረሰቦች ምላሽና መልሶ መቋቋም ለሚውል ፕሮጀክት የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጽድቋል።

ፕሮጀክቱ የህብረተሰቡን አፋጣኝ ፍላጎቶች ለመቅረፍ፣ በግጭት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም እና በግጭት ሳቢያ የመጡ ተፅእኖዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ብሏል።

ፕሮጀክቱ ምንም እንኳን ሀገራዊ መልክ ቢኖረውም ቅድሚያ የሚሰጠው በቅርቡ በተከሰተ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው እና ከፍተኛ የሆነ የውስጥ ተፈናቃዮች ለሚገኙባቸው የአፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች ነው።

ከአካባቢያዊ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመ ፈጣን እና ቀልጣፋ ድጋፍን ለማረጋገጥ ፕሮጀክቱ በፌዴራል፣ በክልልና በማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች ይተገበራል ተብሏል።

ከፍተኛ የሆነ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ በገለልተኛ 3ኛ ወገን አካላት ተግባራዊ ይሆናል።

https://www.worldbank.org/en/news/press-release/2022/04/12/world-bank-supports-ethiopia-s-conflict-affected-communities-targets-over-five-million-people

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል። አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል። የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ…
#Russia #Finland #Sewden

ሩስያ NATOን ለመቀላቀል ከሞከራችሁ እጅግ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ] ይኖራል ስትል ካስጠነቀቀቻቸው ስውዲን እና ፊንላንድ መካከል ስውዲን NATOን ለመቀላቀል ለማመልከት መወሰኗ ተሰምቷል።

የስዊዲን ጠ/ሚ ማግዳሌና አንደርሰን ሀገራቸው በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ለNATO ጥምረት አባልነት ለማመልከት መወሰኗን ገልፀዋል።

ፊንላንድ በበኩሏ ፤ አሁን ይኽ ነው የሚባል ውሳኔ ላይ ባትደርስም በሚቀጠሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ NATOን ለመቀላቀል የማመልከት ውሳኔ ላይ እደርሳለሁ ብላለች።

የፊንላንድ ጠ/ሚ ሳንና ማሪን እና የስዊድን ጠ/ሚ ማግዳሌና አንደርሰን በአካባቢው የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በስቶክሆልም ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በሩስያ እና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት አሁንም መፍትሄ የላገኘ ሲሆን ሩስያ ዩክሬን ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረችባቸው ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ NATOን ለመቀላቀል ሙከራ ማድረጓና ለደህንነቷ ስጋትን በመደቀኗ መሆኑ ይታወቃል።

የዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኃላ ሩስያ ፤ ስውዲን እና ፊንላድ እንዲህ ያለውን ነገር እንዳይሞክሩት ፤ የሚያደርጉት ከሆነ ግን ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጎጂ ውጤቶች እንደሚኖሩ አስጠንቅቃቸው ነበር።

አሁን ላይ ስውዲን NATOን ለመቀላቀል ጥያቄ እንደምታቀርብ መወሰኗ ፤ ፊንላንድም በቀጣይ ሳምንታት ውሳኔ ላይ ደርሳለሁ ማለቷ ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ከአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ይፋ በሆነ መረጃ ውይይቱ ፥ በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በሀገራቱ መካከል ስላለው ወሳኝ ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ግንኙነት ላይ ትኩረት ያደረገ…
#US

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነርና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ይታወሳል።

በኃላም ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር በኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረው ነበር።

ትላንት ከኢትዮጵያ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ጋር በገለልተኛ የዳኝነት ስርዓት እንዲሁም የሰብአዊ መብት አያያዝ አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

በዛሬው ዕለት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጋር ተገናኝተዋል።

ሰላም እና እርቅ እንዲፈጠር እንዲሁም ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እርዳታ እንዲደርስ ያላቸውን ተስፋ መጋራታቸውን ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ባገኘነው መረጃ ደግሞ ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የአሜሪካን ተጠባባቂ አምባሳደር ጃኮብሰንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ይገልፃል።

አምባሳደር ኣን ጃኮብሰን ፤ ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ለመቀበል እና ይፋዊ የሥራ ትውውቅ ለማድረግ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ መሆናቸውን መረጃው ይገልፃል።

ቅዱስነታቸው ከአምባሳደሯ ጋር በነበራቸው ቆይታ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት በማስተላለፍ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን የሚችሉበት ይሆን ዘንድ አባታዊ ተምኔታቸውን ገልጸው በቡራኬ ሸኝተዋቸዋል።

@tikvahethiopia
#Afar

ህወሓት ኃይሎቹን ከአፋር ክልል፤ " ኤሬብቲ " ማስወጣቱን በመግለፅ መግለጫ አውጥቷል።

ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት ኃይሎቹን ከአፋር ክልል ኤሬብቲ ያስወጣው ሰብዓዊ እርዳታ የማድረስ ስራን ለማገዝን ነው ብሏል።

የሰብዓዊ እርዳታ ወደክልሉ እንዲገባና ችግር ላይ ላሉ ዜጎች እንዲደረስ ከዚህ ቀደም ለሰብዓዊነት ተብሎ የተደረሰው ስምምነት ለማክበር ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቋል።

ኃይሎቹን ከኤሬብቲ ማስወጣቱን የገለፀው ህወሓት በሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት ላይ አፋጣኝ ለውጥ እንደሚጠብቅ ገልጿል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲደርስና ሁሉም አስፈላጊ አገልግሎቶች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ለማድረግ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት በኩል የወጣውን መግለጫ "የተሳሳተ" ብሎታል።

ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል፤ አሁንም አፋር ውስጥ ወረዳዎችን እንደያዙ ነው ብለዋል።

አቶ ከበደ፥ "እንደዚህ አይነት ነገር ሰማን (ወጡ የሚል) ትርጉም ያለው መልቀቅ አይደለም፤ የተያዙ ቦታዎች አሉ ለቀቁ የሚል እምነት የለንም በኛ በኩል። ሰብዓዊ እርዳታው በአግባቡ እንዲደርስ በሚል ነው መንግስት ያለ ቅድመ ሁኔታ ስለፈቀደ ነው እንጂ አልተለቀቁም" ብለዋል።

ከዚህ ቀደ። የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታው እንዲሳለጥ የህወሓት ኃይል ከአፋር ክልል ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስት የህወሓት ኃይሎች በአፋር ክልል ዞን 2 በኃይል ይዘዋቸዋል ካላቸው ወረዳዎች መካከል አብአላ፣ መጋሌ፣ ኤሬብቲና በራህሌ ይገኙባቸዋል።

ለሰብዓዊት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ከታወጀ በኃላ እስካሁን በአፋር በኩል ወደትግራይ የገባው 26 ተሽከርካሪ ነው።

@tikvahethiopia