TIKVAH-ETHIOPIA
#ታላቁ_የኢድ_ስግደት ! ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ የተናገሩት ፦ " ... ከፊታችን ረመዳን እየመጣ ነው። ያው እንደምታውቁት የመጀመሪያው ሂጅራ የሚባለው ፣ የመጀመሪያው የእስልምና እንቅስቃሴ የተጀመረው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው / የነበረው እንቅስቃሴ የመጣው ወደ ኢትዮጵያ ነው። የሚቀጥለው ረመዳን ኢድ ታላቁ የኢድ ስግደት በኢትዮጵያ ይደረጋል። ይሄንን ታላቁን የኢድ ስግደት ከሁሉም ዓለም የሚገኙ…
#eid_to_eid
" ከኢድ እስከ ኢድ - ወደ ሀገር ቤት " መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ።
በዚህ መሰረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ከሚያዚያ 3 እስከ ግንቦት 3 ቀን /2014 ዓ/ም የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።
በመርሃ ግብሩ መሰረትም ሚያዚያ 19 በወዳጅነት አደባባይ " የእንኳን ደህና መጣችሁ " መርሃ ግብር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ከዚህም በኃላ በሚያዚያ 21 በመስቀል አደባባይ " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር " ስነ ስርዓት እንደሚካሄድ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።
ከሚያዚያ 27 - ግንቦት 3 በግጭት እና ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን የመጠየቅ ስነስርዓት የሚኖር ሲሆን ይህም በአፋር፣ ሶማሌ፣ አማራ ፣ ኦሮሚያ ክልሎች እና በደቡብ ኦሞ እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈ " ታላቁ የኢድ ሶላት " በስታዲየም ሚያዚያ 24 የሚካሄድ ሲሆን ከሚያዚያ 17 እስከ ሚያዚያ 23 በኤግዝቢሽን ማዕከል የኢድ ኤክስፖ መኖሩ ይፋ ተደርጓል።
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ በምስሉ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#Afar
" በእሳት አደጋው 160 የሚጠጉ ሱቆች እና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ
በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር አሳውቋል።
የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር አቶ ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ በሰጡት ቃል ፤ " የእሳት ቃጠሎ አደጋው የደረሰው ወደ 10 : 00 ሰዓት አካባቢ በድንገት ከቢንዝል መሸጫ ቤት በተነሳ እሳት ነው " ብለዋል።
በድንገተኛው የእሳት አደጋ ምክንያት የደረሰው ውድመት ወደፊት የሚጣራ ሁኖ በግምት ግን ከ80 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደዚሁም ወደ 80 ሊጠጋ የሚችል የተለያዩ የንግድ ሱቆች ወድመዋል።
በእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አሳውቀዋል።
በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ንፋስ መኖሩ እና የውሀ እጥረት በመኖሩ ቃጦሎው በፍጥነት በመባባሱ ምክንያትም እሳቱን ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ከፍተኛ ውድመት መከሰቱን አስተዳዳሪው አስረድተዋል።
ለተጎጂዎቹ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የቢንዚል ሽያጭ ከሚከናወንበት ቦታም በቀላሉ የእሳት አደጋ እየተፈጠረ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቂ ሊደረግ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
መረጃው የአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ነው።

#ነዳጅ መንግስት ከተመረጡ የብዙሃን አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ውጭ የነዳጅ ድጎማን በሂደት እንደሚነሳ ታውቋል። ይህ ድጎማ ሲነሳ የተሽከርካሪ ባለቤቶች ጫና ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ይታመናል። አቶ ገብረመስቀል ጫላ (የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር) ፦ " ነዳጅ በጣም ውድ ምርት ነው ። እኛ ሀገር ግን እንደ ውድ ምርት አንጠቀምም። ስለዚህ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ያለው ዜጋ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም…
#ነዳጅ
የነዳጅ ድጎማን የተመለከተ ዝርዝር መረጃ !
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ፤ ከመጪው #ሃምሌ 2014 ዓ/ም ጀምሮ የነዳጅ ድጎማ እየተደረጉ የሚቀጥሉ ተሽከርካሪዎችን ዝርዝር መረጀ ክልሎች ለይተው እንዲልኩ አዟል።
መረጃው ተሰብስቦ ወደ ማዕከላዊ ቋት የሚገባ ሲሆን ለሁሉም ነዳጅ ማደያዎች የተደጓሚ ተሽከርካሪዎች ዝርዝር ይሰጣቸዋል ተብሏል።
የማይታይም እና ሎጅስቲክስ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ ሰይፉ እልፉ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል ፤
" ምን ያህል ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ? የሚለውን ነገር አዋጁን መሰረት በማድረግ ዝርዝር መረጃዎችን አደራጅተን ለክልሎች በሙሉ ስልጠና ሰጥተን መረጃዎች ከክልል እየተሰበሰቡ ነው።
ትክክለኛ የሆነ መረጃ ፣ መደጎም ያለባቸው መኪኖች እነዚህ ናቸው ብለው ክልሎች ለይተው ያሳውቃሉ፤ እኛ ወደ ዳታ እናስገበ እና መደጎም ያለባቸው መኪኖች ተለይተው ይታወቃሉ።
ዝርዝር መረጃ ውስጥ በምንገባበት ወቅት የጠራ የመረጃ የለም የጠራ መረጃ እንዲኖር ነው እየተሰራ ያለው።
ይህን በአጭር ጊዜ ልንጨርስ ክልሎች ኃላፊነት ወስደው እየሰሩ ያሉ አሉ አንዳንዶቹ ክልሎች በከፊል መረጀዎችን ጨርሰዋል " ብለዋል።
ለተመረጡ የትራንስፖርት ሰጪዎች ብቻ የሚደረገው የነዳጅ ድጎማ በምን አይነት መልኩ ነው አሰራሩ ላይ ቁጥጥር የሚደረገው ለሚለውም አቶ ሰይፉ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል ፦
" ድጎማው ከማንዋል ወጥተን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ነው የሚሆነው።
GPS ይገጠማል Speed Limit ጋር የተጣመረ ነው የሚገጠመው ፤ በሌላ በኩል የሚገጠመው GPS ፤ የነዳጅ ሴንሰር አለው ፤ በኪሎ ሜትር ምን ያህል ሄደ ? ስንት ኪሎ ሜትር ላይ ምን ያህል ተጠቀመ የሚለው በሙሉ ይታወቃል።
ይሄን በምናደርግበት ሰዓት የሚደጎሙ መኪኖች በሙሉ ልዩ መታወቂያ ይሰጣቸዋል፤ ታግ ይለጠፋል።
ማደያዎች ያውቃሉ ዝርዝራቸው እነሱ ጋር ስለሚሰጠ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማደያ በሙሉ ይሰጣቸዋል፤ እነሱ ያን ታግ አሳይተው ነው የሚቀዱት።
አሮጌና አዲስ መኪኖች አሉ ። እነዚህ በሙሉ ይለያሉ ደረጃ 1፣ 2፣ 3 የሚባለው የነዳጅ አጠቃቀምና የኪ/ሜትር ሽፋናቸው ይታወቃል። ስለዚህ በዛ መሰረት እያንዳንዱ ተለይቶ ነው የሚሰጠው።
ለምሳሌ ፦ አዲስ አበባ ላይ ከፒያሳ - መገናኛ የሚሄድ ታክሲ ኪ/ሜትሩ ይታወቃል ፤ ስንት ጊዜ ተመላለሰ የሚለው ይታወቃል ይህን ሂሳብ ተሰርቶ በቀን ስንት ኪ/ሜትር ሸፈነ ፤ በአንድ ሊትር ስንት ኪ/ሜ ይሄዳል የሚለው ስለሚታወቅ በሱ መጠን ነው ነዳጅ የሚቀዳው።
ከዚህ ውጭ ነዳጅን ባልተሰጠው ነገር ሄጄ እቀዳለሁ ካለ ገበያው ባስቀመጠው ዋጋ ነው የሚቀዳው እንጂ በታሪፉ አይካተትም።
አሁን GPS ገጣሚዎችን በሙሉ ስልጠና ሰጥተናል። እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አድርገናል መንግስት በራሱ በኩል አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል " ብለዋል።
👉 ታክሲዎች
👉 ሃይገሮች
👉 ባጃጆች
👉 የሃገር አቋራጭ አውቶብሶች የነዳጅ ድጎማው የማይነሳባቸው ሲሆን ነገር ግን ለመደጎም በማህበር መደራጀት ግዴታቸው ነው ተብሏል።
ባለንብረቶች በማህበር ካልተደራጁ በግለሰብ ደረጃ ማንም ሊደጎም እንደማይችል አቅጣጫ ተቀምጧል።
በሌላ በኩል ፤ ከፌዴራል እስከ ክልል ባለው መዋቅር ለመንግስት ስራ የሚያስፈልጉ መኪኖች ድገማው የማይመለከታቸው ሲሆን በወቅታዊ የገበያ ዋጋ እየገዙ ይጠቀማሉ ተብሏል።
አቶ ሰይፉ ፤ " መንግስት አይደጎምም ፤ መንግስት ከድጎማው ይወጣል ፤ አይደጎምም በነፃው ገበያ ነው መቅዳት ያለበት። ምክንያቱም መደጎም ያለበት ድሃው የህብረተሰብ ክፍል ነው። " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
Credit : ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

#Afar " በእሳት አደጋው 160 የሚጠጉ ሱቆች እና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር አሳውቋል። የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር አቶ ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ በሰጡት ቃል…
" ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ነው ያሉት ፣ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል " - አቶ ሀሰን ሀንድዬ
ትናንት ከሰአት 11 ሰአት ገደማ በሰሙሮቢ ወረዳ ኮማሚ ቀበሌ በተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በርካታ ንብረት በመውደሙ የተነሳ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ ችግር በመዳረጉ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀሰን ሀንድዬ ጥሪ አቅርበዋል።
" ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ነው ያሉት ፣ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል " ብለዋል።
አልባሳት፣ ምግብ ነክ ነገሮች፣ መጠለያና የመጠጥ ውሃ በአፋጣኝ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።
ከ3 ቀን በፊት በተቋረጠው ኤሌክትሪክ ምክንያት ህብረተሰቡ ለውሃ ጥም መዳረጉን ገልፀው አሁን የደረሰው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ሲጨመርበት በዚህ #የፆም ሰአት ህብረተሰቡን የበለጠ ተጎጂ አድርጓል ብለዋል።
አቶ ሀሰን እንዳሉት በትላንቱ አደጋ እያንዳንዳቸው 80 የንግድ ቤቶች ውስጥ የነበሩ 500 ሺ ብር በላይ ሸቀጣ ሸቀጥና ጥሬ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን በ80 መኖሪያ ቤቶችም የነበሩ እቃዎችና እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ እያንዳንዳቸው 200 ሺህ ብር ገደማ ወድሟል።
አጠቃላይ ንብረት ላይ የቤቶችን ግምት ሳያካትት በቤት ውስጥ የነበረ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ እቃዎችና ጥሬ ብር የደረሰው አደጋ አሀዝ 56 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።
በአቅራቢያ በሚገኙት ሸዋሮቢት ሆነ ደብረብረሃን ከተሞች አንድም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለመኖሩ ምክንያት ውድመቱን መቀነስ እንዳልተቻለ ዋና አስታዳዳሪው ገልፀዋል።
" መነሻው በቀዳሚነት በቤንዚን ነው ተብሎ ታስቦ የነበረው ትክክል አልነበረም " ያሉት አቶ ሃሰን በተደረገ ማጣራት መነሻው የኤሌክትሪክ ንክኪ ተፈጥሮ ወደ ቤንዚን ቤት በማምራቱ ነው ብለዋል።
መረጃው ከአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

#Russia
የሩሲያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸውን ሩስያን ለማግለል የሚደረገው ሙከራ አይሳካም ሲሉ ምእራባውያንን አስጠነቀቁ።
ሩስያ በዩክሬን የጀመረችውን " ልዩ ወታራዊ ዘመቻ " ተከትሎ ጠንከር ያሉ ማዕቀቦችን በጣሉባት ምእራባውያን እና አሜሪካ ላይ እምነት እንደማይኖራት ገልጻለች፡፡
ፕሬዜዳንት ፑቲን ፥ " በሶቬት ህብረት ጊዜ ጠቅላላ ማእቀብ ተጥሎ ነበር፤ ሙሉ በሙሉ ተገልላም ነበር፤ ነገርግን ሶቬት አሁንም በስፔስ ቀዳሚ ነች " ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዝደንቱ የመገለል ፍላጎት እንደሌላቸው እና በዚህ ዘመናዊ አለም ማግለል እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሩሲያ በዩሪ ጋጋሪ አማካኝነት ወደ ስፔስ ያደረገችው በረራ እና በፈረንጆቹ 1957 የስፑትኒክ አንደኛ ወደ ስፔስ መብረር አሜሪካን አስደንግጦ ነበር፡፡ በወቅቱ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ለመወዳደር ስትል ናሳን አቋቁማ ነበር፡፡
ፕሬዜዳንት ፑቲን በዩክሬን " ወታደራዊ ዘመቻ " ለማድረግ የተገደዱት፤ አሜሪካ ዩክሬንን እና ኔቶን በመጠቀም ለማስፈራራት ስለሞከረች እና ይህንም መከላከል ሲለሚገባ ነው ብለዋል፡፡
ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን ሁሉንም የምትፈልገውን አላማ ታሳካለች ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

#Update የደቡብ ክልል ፖሊስ ፤ በጂንካ ከተማና አካባቢው በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ተሳትፈዋል ተብሎ የተጠረጠሩ 133 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል 4 የፖሊስ አባላት አሉበት ተብሏል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ለዋልታ ቴሌቪዥ በሰጠው ቃል. ፤ " በመንግሥት መዋቅር ስር ያሉ የአመራር አካላት፣ ራሳቸውን የሕዝብ ወኪል አድርገው…
#Udpate
በጂንካና አካባቢው ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች 22 ሲፈቱ ቀሪዎቹ ላይ ምርመራ መቀጠሉ ተሰምቷል።
ዞኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የተከሰተው ችግር በቁጥጥር ስር ውሎ ማኅበረሰቡም ወደ ቀደመው የኑሮ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብሏል።
የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ ፤ ከፀጥታው ችግር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ካሉበት አድኖ በሕግ ጥላ ሥር የማዋል ሥራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን ለጊዜው እስካሁን 132 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ ከእነዚህ መካከል በተደረገ የማጥራት ሥራ 22ቱ ዛሬ ተፈተዋል ሲሉ ተናግረዋል።
[NB. ትላንት የደቡብ ፖሊስ ሰጥቶ በነበረው ቃል የተያዙ ተጠርጣሪዎች 133 ናቸው ብሎ ነበር]
አቶ ደሞ የጸጥታ ኃሎች በሰሩት ስራ አብዛኛው አካባቢ አንፃራዊ መረጋጋት መፈጠሩን ገልፀዋል።
በዚህም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚመች መልኩ ተግባራቸውን ለማከናወን ተንቀሳቅሰዋል።
ኃላፊው፤ የፀጥታው ኮማንድ ፖስት ባካሄደው ወቅታዊ ሁኔታ ግምገማ በቶልታና መጸር 145 ቤቶች በእሳት የተቃጠሉ ሲሆን ከዚህ መካከል 1 መስጂድ ይገኝበታል ብለዋል።
አንድ ቀበሌ ያልተጣራ ያለ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይ አጣርቶ ለሕዝብ ግልጽ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።
በጂንካ ዙሪያ 6 ቤቶች መቃጠላቸውን አሳውቀዋል።
በፀጥታ መዋቅሩ የተገመገመና የተለየ የተፈናቀሉ አባወራ 237፤ እማወራ 136 በአጠቃላይ 333 አባወራና እማወራዎች ተፈናቅለው በት/ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ።
979 ቤተሰቦች ከቤት-ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ይህም ለጊዜው በጸጥታ አካላት ተለዩ ናቸው። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሪፖርት ሲመጣ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ ሊያሻብቅ እንደሚችል ተገምቷል።

#Udpate በጂንካና አካባቢው ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች 22 ሲፈቱ ቀሪዎቹ ላይ ምርመራ መቀጠሉ ተሰምቷል። ዞኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የተከሰተው ችግር በቁጥጥር ስር ውሎ ማኅበረሰቡም ወደ ቀደመው የኑሮ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብሏል። የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ ፤ ከፀጥታው ችግር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ካሉበት…
ቀይ መስቀል ድጋፍ እያደረገ ነው።
የደቡብ ኦሞ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቶልታ፣ መጸርና በርካ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አፍርጓል።
የሰሞኑን ፀጥታ ችግር ተከትሎ በደቡብ አሪ ወረዳ መፀር፣ ቶልታና በርካ አካባቢዎች ከፍተኛ የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት የተከሰተ ሲሆን ነዋሪዎቹም ከስፍራው ሸሽተዋል፡፡
ራሳቸውን ለማዳን በሐይማኖት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶችና በፖሊስ ጣቢያዎች የተጠለሉት የማኅረሰቡ አካላትን የደቡብ ኦሞ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከራሱና ማኅበረሰቡን በማስተባባር የዕለትና ሌሎችንም ድጋፍ ለመስጠጥ ችሏል፡፡
የተደረገው ድጋፍ ፦ ለሶስቱም አካባቢዎች ለበርካ፣ ቶልታና መፀር 130 ደርዘን እሽግ ውሃ፣ 3 ሺህ ዳቦ፣ 50 አገልግል እንጀራ፣ 10 ኩንታል ሞኮሮኒ፣ 2 ኩንታል ሩዝ፣ 6 ኩንታል ነጭ ዱቀት፣ 2 ኩንታል ጤፍ፣ 18 ደርዘን ጁስ፣ 6 ደርዘን ብስኩት እና ሌሎችም ይገኙበታል።
አሁንም ድጋፉን ለማጠናከር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ቀይ መስቀል ጥሪ አቅርቧል፦ ችግር ላይ የወደቁ ወገኖችን ለማገዝ በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ERCS 1000040792981 መላክ እንደሚችሉ ተገልጿል።

#ትኩረት📣
የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ፤ " የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ቅዱስ ላልይበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሊመለከት ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።
ብፁዕነታቸው ቅዱስ ላልይበላን በማስመልከት ዛሬ በተሰጠ መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በነበረው ጦርነት የቅዱስ ላልይበላ ቅርስ የቱሪዝም እና የከተማው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቁን ገልጸዋል፤ በዚህም አገልጋዮች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን አሳውቀዋል።
ቅዱስ ላልይበላ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሐብት እንደመሆኑ አቅም በፈቀደ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ለድጋፍ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕነታቸው " ሁላችንም የድርሻችንን በመወጣት ቅርሳችን እንጠብቅ " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዜጎች ድጋፋቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አቢሲኒያ እና ዳሽን ባንኮች በ 👉 0712 የባንክ የሒሳብ ቁጥር ማድረግ ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911061164 እና 0913912457 መደወል ይቻላል።
ምንጭ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

የሲዳማ ክልል ወጣቶች ጥያቄ 💬
(የድምፅ ባለቤት ዶቼ ቨለ ሬድዮ ሲሆን - ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በሚሆን መልኩ በፅሁፍ የተዘጋጀ)
በሀዋሳ ከተማ ፤ የብልፅግና ፓርቲ ከሲዳማ ወጣቶች ጋር ለመምከር የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህ መድረክ የተሳተፉ አብዛኞቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች ሲሆኑ ለበርካታ አመታት ያለ ስራ መቀመጣቸውን በመግለፅ ጠንካራ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ፦
" አሁን ወጣቱን አደራጅተን እንደዚህ እያደረግን ነው ብላችሁ እያወራችሁ ነው። የትኛውን ነው ?
ለምሳሌ ፦ ኮንቴነር በየክፍለ ከተማው ፈትሹ ያለውን ነገር ታያላችሁ ፤ አመራሩ እጅ ነው ያለው ኮንቴነር። አደራጅ እና አስተባባሪ ተብሎ የተቀመጡ ሰዎች እነሱ እጅ ነው ያለው ኮንቴነር ለወጣቱ ይሰጥ ተብሎ የተሰራው ፤ የምን ብልፅግና ነው እናተ ምትመሩት ?
ይህንን ወጣት ፤ በቀን 3 ጊዜ መብላት ያልቻለን ህዝብ እየመራችሁ እንዴት ነው ? እናተ በV8 እና በተለያየ ላንድክሩዘር መኪኖች እየዘነጣችሁ የምትሄዱት ? በምን አግባብ ነው ? "
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ፦
" ... ብልፅግና ፓርቲ መነፅር ብቻ ነው የቀየራችሁት ። ሙሉ ኢህአዴግ የነበሩ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ለውጡን ለመቀበል ዝግጁ አይደሉም። በሌብነት ፣ በዘረኝነት የተጠመዱ ሰዎች ናቸው።
ብልፅግና ፓርቲ ቢያንስ ወጣቱን የሚሰማ ከሆነ እኛ በትዕግሥት መንግስቱ አልተረጋጋም ፣ ጫና አለበት የውስጥም የውጭም ብለን በትዕግስት ጠብቀናል ሶስት ዓመት ሙሉ አሁን 4ኛ ዓመት ልንይዝ ነው ሁሌ በዚህ ይቀጥላል ? የኛም ዝምታ በዚህ ይቀጥላል ? እሱን ጊዜ የሚፈታው ነገር ነው። "
ከዚህ በተጨማሪ የውይይት ተሳታፊዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ቢጥሩም እንዳልቻሉ ፤ በክልላቸው ዴሞክራሲና ነፃነት የለም ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል።
እንዲሁም በክልሉ ፦
👉 ሰብአዊ መብቶች ይጥሳሉ፣
👉 የመልካም አስተዳደር ጉድለት አለ፤
👉 ሙስና ተንሰራፍቷል ፤
👉 ባለስልጣናት ለወጣቶች መገልገያ የተገነቡ ተቋማትን ለዘመዶቻቸዉና ለቤተሰቦቻቸዉ ሰጥተዋል፣
👉 ባለስልጣናት ዉሳኔዎችን የሚያሳልፉት ለእነሱና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ በሚጠቅም መልኩ ነዉ ብለዋል።
በወጣቶች ለተነሱት ጥያቄዎች በመድረኩ ከተገኙት አንዱ የሲዳማ ብልፅና ፓርቲ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘማች እርጥባ ተከታዩን ብለዋል ፦
" ቁጥር ብዙ ለሆነ ወጣት ስራ እድል ያልተፈጠረለት ሁኔታ አለ። እየተፈጠረም ያለው እራሱ የባለሃብት ቤተሰብ ፣ የአመራር ቤተሰብ የሚለው ትክክል ነው።
ምን እያደረጋችሁ ነው ያላችሁት ? ቢሚል ለነሳችሁት መጀመሪያ የሚሆነው ይህን ሲፈፅም የነበረው ሊመራ ኃላፊነት የተሰጠው አመራር በአግባቡ ያልመራውን እርምጃ ወስደናል አሁን።
በዚህ ዓመት አሁን እስካለንበት ከ80 በላይ በሆኑት ላይ እርምጃ ተወስዷል። ይሄ ብቻም አላቆመም ቀጥሎም በኃላፊዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ በከተማ ፓርቲ ደረጃ ፤ በመንግስት ደረጃ የሚኬድበት ሁኔታ ይቀጥላል "
የብልፅግና ወጣቶች ሊግ አመራር አንዱ ታረቀኝ ለገሰ ፦
" የምታነሷቸው ጥያቄዎች በሰፊው አሉ። ስራ አጥነት አለ። የ3 ዓመት ብቻ አይደለም ፤ የ7 ዓመት ስራ ያልተቀጠረ ወጣት ፤ ስራ ያላገኘ ወጣት ያለው እኛ ጋር በዝርዝር አለ። እያንዳንዱን ጥያቄ በዝርዝር ይዘናል ፤ እንደተባለው ቀጥታ ይሄ ለፌዴራል ብልፅግና ፓርቲ ግብአት ሆኖ የሚሄድ ነው። "
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT