TIKVAH-ETHIOPIA
ሩብል📉 የምዕራባውያን ማዕቀብ እጅጉን የበረታባት ሩስያ የመገበያያ ገንዘቧ የሆነው #ሩብል ከአሜሪካ #ዶላር አንፃር በእጅጉ ቀንሷል። አሁን ላይ 1 የሩስያ ሩብል $0.0085 ከ1 የአሜሪካ ሳንቲም በታች ወይም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ117.18 የሩስያ ሩብል እየተመነዘረ ነው። አንድ የአሜሪካ ዶላር በሩስያ ሩብል ሲመነዘር ፦ • ከአንድ ወር በፊት : 76.2 ሩብል • ከአንድ ሳምንት በፊት : 81.4…
#Rubel
ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በምዕራባውያን ብርቱ የሆነ ማዕቀብ ምክንያት የሩስያ የመገበያያ ገንዘቧ የሆነው #ሩብል ከአሜሪካ #ዶላር አንፃር በእጅጉ ቀንሶ እንደነበር ይታወሳል።
ከሳምንታት በፊት በተለዋወጥነው መረጃ 1 የአሜሪካ ዶላር በ117.18 የሩስያ ሩብል እስከመመንዘር ደርሶ ነበር።
ይህም ፥ የሩሲያው ሩብል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ደረጃ ዋጋው እንዲወርድ አድርጎት ነበር።
አሁን ላይ ግን በሩብል እና የአሜሪካ ዶላር ያለው ልዩነት በእጅጉ ጠቧል።
ከሳምንታት በፊት በ117.18 ሩብል ሲመነዘር የነበረው የአሜሪካ ዶላር ዛሬ በ80.25 ሩብል እየተመዘረ ይገኛል።
👉 የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ/ም - አንድ የአሜሪካ ዶላር 117.18 ሩብል ፤
👉 ዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2014 ዓ/ም - አንድ የአሜሪካ ዶላር 80.25 ሩብል ፤
የምዕራባውያን ጠንካራ ማዕቀቦችን ተከትሎ የኢኮኖሚ ተንታኞች የሩስያ ኢኮኖሚ በአጭር ጊዜ ሊሽመደመድ እንደሚችል እና የከፋ ችግር ላይ እንደምትወድቅ መግለፃቸው ፤ ሩስያ በበኩሏ እየተጣሉባት ያሉት ማዕቀቦች ይበልጥ ነፃና ጠንካራ ሀገር እንደሚያደርጋት መግለጿ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

#ATTENTION📣 በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ ከተማና አካባቢው ውጥረት መኖሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጂንካና አንባቢው አባላት አሳውቀዋል። ውጥረቱ ከሰሞኑን የጀመረ ሲሆን ወዲያው መፍትሄ አግኝቶ ይቆማል ተብሎ ቢታሰብም አልሆነም ፤ ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ያለው ሁኔታ ዜጎችን ለጭንቀት ዳርጓል። ከ8 ዛሬ ቀን በፊት የደቡብ ኦሞ ዞን ም/ቤት መደበኛ ጉባኤውን አካሂዶ ነበር። በዚሁ ጉባኤ ላይ የአሪ…
#TikvahFamily
ከሰሞኑን በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጅንካና አካባቢው አለመረጋጋት መፈጠሩ ይታወቃል።
ትላንት ለሊት በላክንላችሁ መልዕክት ፤ አለመረጋጋቱ የተፈጠረው በአሪ የመዋቅር ጥያቄ ምክንያት ነው።
ከጥቂት ቀናት በፊት በነበረው የደ/ኦሞ ዞን ም/ቤት ጉባኤ ላይ የአሪ በዞን የመደራጀት ጥያቄ በአጀንዳነት አለመያዙ ህዝቡን አስቆጥቶታል በዚህም ምክንያት ለተፈጠረው ሁኔታ የዞኑ አስተዳደሪ ወጥተው በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል፤ ከዚህ በኃላም ውይይቶችን ለማድረግ ተሞክሯል ፤ ሁኔታው እንዲረግብ መልዕክት ሲተላለፍም ነበር።
ምንም እንኳን ይህ ቢደረግም አለመረጋጋቱ ተባብሶ የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ላይ እስከመጣል ደርሷል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥም ሁሉም ዜጋ ከጫፍ እስከ ጫፍ የኢትዮጵያ ምድር ባለቤት እንዳልሆነ ሁሉ በአንዳንድ አካላት " ከዚህ አካባቢ አይደላችሁም ፤ ከሌላ ቦታ ናችሁ ፤ ማንነታችሁም እንዲህ ነው " በሚል የተሳሳተ እና አደገኛ አመለካከት የዜጎችን መብት ለመጣስ ተሞክሯል።
ይህን መሰል ነገር ከዚህም ቀደም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችም የታየ ግን እስካሁን ያልታረመ በየትም ቦታ ላይ የመኖር መብትን በአደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ቀጥሏል።
ችግር በተፈጠረ ቁጥር አይልም ጥያቄ በተነሳ ቁጥር ከማህበረሰቡ በሚወጡ አንዳንድ አካላት ከጉዳዩ ጋር የማይገናኙ ዜጎችን አደጋ ላይ መጣል፣ አጋጣሚውን በመጠቀምም ዜጎች በላባቸው ጥረው ያፈሩትን ግል ንብረት መዝረፍ ፣ ሰዎችን ማጥቃት ፣ ከቤታቸው ማፈናቀል የመሳሰሉ ድርጊቶች ከዚህ በፊትም በተለያየ ቦታ ታይቷል።
ከሰሞኑን በጂንካ እና አካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ይኸው ተስተውሏል። ንብረቶች ተዘረፈዋል፤ በእሳትም ጋይተዋል፤ ሰው ላይም ጥቃት ተፈፅሟል ፤ ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ እንዲያርፉ ሆነዋል።
መንግስት የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ የጣሉ ፣ ይህንን የሚደግፉ ፣ የሚያስተባብሩ ፣ እና በዚህ ድርጊት ላይ የሚሳተፉትን ተጠያቂ ማድረግ እና የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።
አሁን የኢትዮጵያ 🇪🇹 ሀገር መከላከያ ሰራዊት የፀጥታ ችግር ባለባቸውና አለመረጋጋት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በመግባት የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Family-04-10

Telegraph
Tikvah-Family
" ችግር በተፈጠረ እና ጥያቄ በተነሳ ቁጥር አጋጣሚውን በመጠቀም የሚፈፀሙ ጥቃቶች እና ትንኮሳዎችን መንግስት ሊከላከል እና የዜጎችን ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል " - የቲክቫህ ጂንካ አባላት ከሰሞኑን በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጅንካ እና አካባቢው አለመረጋጋት መፈጠሩ ይታወቃል። ትላንት በላክንላችሁ መልዕክት ፥ አለመረጋጋቱ የተፈጠረው በአሪ የመዋቅር ጥያቄ ምክንያት ነው። ከጥቂት ቀናት በፊት በነበረው…
ሃጅ ለህዝብ ዳግም ተፈቅዷል።
በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ባለፉት 2 አመታት ተቋርጦ የነበረው የሓጅ ስነ ስርአት 1 ሚሊዮን ሃጃጆችን ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ ዘንድሮ እንደሚደረግ ከሳዑዲ የሃጅና ዑምራ ሚኒስቴር የወጣ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።
የዘንድሮ ሃጃጆች ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት ፦
1. የዕድሜ ጣራ ከ65 አመት በታች የሆኑና የኮቪድ ክትባት የወሰዱ
2. ከጉዞው በፊት ከኮቪድ ነፃ ምርመራ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
#EthiopianIslamicAffairsSupremeCouncil
#Hajj2022 #Hajj1443 #ሃጅ1443 #ሃጅ2014

#AddisAbaba🏫
የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና፣ ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን የመምህራንና የትምህርት ቤቶች አመራር ፈቃድ ቡድን መሪ ሰንደቁ ያዛቸው ፦
" በ2013 ዓ.ም የተደረገ ጥናት በአዲስ አበባ በግል ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን 24 በመቶ የሚሆኑት #በመምህርነት ሙያ ያልሰለጠኑ መሆናቸውን ያሳያል።
በመንግስት ት/ ቤቶች በማስተማር ላይ ከሚገኙት መካከል 4 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑ መምህራን ባልሰለጠኑበት የመምህርነት ሙያ በማስተማር ላይ ይገኛሉ።
ይህም ለትምህርት ጥራት መጓደል ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ አለው። ችግሩን ለመቅረፍ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርት ሚኒስቴር ተቀናጅተው መስራት አለባቸው "
🏫 በአዲስ አበባ 1 ሺ 562 የግል ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲሆን በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥም ከ23 ሺህ 400 በላይ መምህራን እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ።
#ENA

#TikvahFamily ከሰሞኑን በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጅንካና አካባቢው አለመረጋጋት መፈጠሩ ይታወቃል። ትላንት ለሊት በላክንላችሁ መልዕክት ፤ አለመረጋጋቱ የተፈጠረው በአሪ የመዋቅር ጥያቄ ምክንያት ነው። ከጥቂት ቀናት በፊት በነበረው የደ/ኦሞ ዞን ም/ቤት ጉባኤ ላይ የአሪ በዞን የመደራጀት ጥያቄ በአጀንዳነት አለመያዙ ህዝቡን አስቆጥቶታል በዚህም ምክንያት ለተፈጠረው ሁኔታ የዞኑ…
" እስካሁን እኔ ባለኝ መረጃ አንድ ሰው ሞቷል " - አቶ ንጋቱ ዳንሳ
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስታዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ አቶ ዛሬ ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ በጅንካ እና አካባቢው በተፈጠረው አለመረጋጋት በንብረት እና በሰው ላይ ጉዳይ መድረሱን አረጋግጠዋል።
" በቤቶች ፣ በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል " ያለቱ ዋና አስተዳዳሪው ፥ ጉዳቱ በግለሰቦች ንብረት ላይ አልፎ አልፎም በመንግስት ንብረቶች ላይ የደረሰ መሆኑን አመልክተዋል።
አንዳንድ ተዘግተው የነበሩ ቦታዎች ላይ ገና ዛሬ ሰራዊቱ እየገባ እየተከፈተ በመሆኑ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት ሲጠቃለል ይገለፃል ብለዋል።
በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰው ጉዳት ሲያብራሩ ፥ " እካሁን ባለኝ መረጃ አንድ ሰው ሞቷል፤ ቆስሎ ሆስፒታል ከገባ በኃላ ሞቷል ፤ ሌላው መረጃ እስካሁን አልደረሰኝም " ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪው ፥ ሁከቱን ያስተባበሩ እና የመሩ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።
ቤታቸው በድንጋይ ከተደበደበባቸው ነዋሪዎች አንዱ ለሬድዮ ጣቢያው " የዞን ጥያቄ የሚያነሳው ይሄ ከሆነ ቤት ማፍረስ እና ንብረት ማውደም፣ ሰው መጉዳት፣ ንብረት መዝረፍ የዞን ጥያቄ አይደለም፤ የወሮበላ እና የዘረፋ ተግባር ካልሆነ በስተቀር ፤ የሚደረገው ነገር እና የሚቀርበው ጥያቄ ተመሳሳይነት የለውም " ብለዋል።
ሌላ አንድ ነዋሪ ደግሞ ሰው ተንቀሳቅሶ መስራት እንዳልቻለ ፤ ሌላው ቀርቶ ወደ ህክምና ተቋም ለመሄድ እንደማይቻል በተፈጠረው አለመረጋጋት አገልግሎት ሰጪዎች በራቸውን መዝጋታቸውን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል አስረድተዋል።
አሁን ላይ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ችግር ወዳለባቸው ቦታዎች ገብቶ ከፌዴራል ፖሊስ እና የክልል ፀጥታ ኃይል ጋር የማረጋጋቱን ስራ እየሰራ ይገኛል።

#SEMU
በሚያሽከረክሩበት ወይም በእግር በሚጓዙበት ጊዜ አዝናኝ ወይም አስተማሪ ነገር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
የስሙ ኦዲዮ ቡክስ መተግበሪያን ከጎግልና አፕል ማከማቻ በማውረድ በደንበኝነት ምዝገባ ወይም በአንድ ጊዜ ክፍያ በርካታ ነጻ ድምፀ-መጻሕፍት እና ፖድካስቶችንም ያግኙ።
በመተግበሪያው ላይ ሲመዘገቡ ነዋሪነትዎ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ በስልክ ቁጥርዎ ፣ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ከሆነ ደግሞ በኢሜይል አድራሻዎ ይመዝገቡ።
ጉግል ማከማቻ ፡ bit.ly/SemuGooglePlay
አፕል ማከማቻ፡https://apple.co/3gzblVH
ድረ-ገፅ፡ https://www.semuaudiobooks.com/

" ችግሮች መፍታት የሚቻል ከሆነ በፍጥነት ቢፈቱ እና ህዝቡ ወደ ቀድሞው ኑሮው እንዲመለስ ቢደረግ መልካም " - የቲክቫህ አባላት
ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በክልሉ ላለው ችግር እካሁን ይሄ የሚባል መፍትሄ ባለመምጣቱ ህዝቡ ስቃዩ እየተራዘመ ነው ብለዋል።
በቅርብ ሳምንት የታዩት በጎ ነገሮች መልካም ቢሆንም በፍጥነት ወደ ታች ወርዶ በችግር ላይ ያለውን ህዝብ መታደግ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።
ነዋሪዎች ባለፉት በርካታ ወራት ፦
👉 ያለ ባንክ፣
👉 ያለ ስልክ፣
👉 ያለ ትራንስፖርት ፣
👉 ያለ የንግድ ልውውጥ፣
👉 ያለ ስራ፣
👉 ያለ ትምህርት
👉 ከምንም በላይ ደግሞ ያለ በቂ ህክምና ላይ ነው የሚገኙት ይህን ለአንድ ቀን እንኳን ለማሰብ የሚከብድ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ያሉት ችግሮች የሚፈቱበት አግባብ ቢፋጠን ፤ ዜጎችም ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ቢደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።
ለበርካታ ወራት ባለው ሁኔታ ምንም ፖለቲካ የማያውቁ ፣ ስላለው ሁኔታ በቅጡ የማይረዱ እጅግ ብዙ ሰዎች አብረው የችግሩ ገፈጥ ቀማሽ ሆነዋል፤ ሌላው ቢቀር ለትንንሽ ህፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ተብሎ ፈጣን መፍትሄ ቢፈግ ሲሉም ተማፅነዋል።
በተለይም ፤ ከባንክ አለመኖር ጋር በተያያዘ ብዙ ችግር መከሰት ከጀመረ ወራት መቆጠሩንና ይህም ችግር ለማንም ግልፅ እንደሆነ አንስተዋል።
መልዕክታቸውን ከላኩ ቤተሰቦቻችን አንዱ " ቤተሰቦቼ የሚኖሩት ትግራይ ክልል ነው። ታድያ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ላይ ባንኮች አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ምክንያት ህዝቡ በብዙ ችግሮች ውስጥ እየኖር ነው " ብሏል።
አክሎም ፤ " ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በአቋራጭ መበልፅግ የሚፈልጉ እራስ ወዳዶች ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቤተሰቦቹ ብር መላክ ከሚፈልግ ሰው አላማጣ ላይ ባሉት ሰዎቻቸው ሆነው አዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ መቀመጫቸውን ካደረጉ ግለሰቦች እስከ 50 በመቶ ማስላክያ ክፍያ በመቁረጥ ከሚልከውና ከሚቀበለው ህዝብ እየዘረፉ ይገኛል " ሲል አስረድቷል።
በዚህ ላይ አስፈላጊውን እርምት ሊወሰድ እንደሚገባና በአፋጣኝ በትግራይ የባንክ አገልግሎት እንዲጀመር ሊደረግ ይገባል ሲል ጠይቋል።
በትግራይ ፤ በብር እጦት ምክንያት ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ምንም የማያውቁ ንፁሃን እየሞቱ እና እየተንገላቱ ነውና ፈጣን መፍትሄ ያስፈልጋል ብሏል።
ከዚህ ቀደም የቤተሰቦቻችን አባላት ፤ በክልሉ ውስጥ ስላለው ሁኔታ በተደጋጋሚ መግለፃቸው እና በተለይ በተለይ ለ #ህፃናት ፣ #ሴቶች እንዲሁም #አረጋዊያን ካለው ችግር እንዲወጡ ፈጣን መፍትሄ እንዲፈለግ መማፀናቸው ይታወሳል።

#Russia
ሩስያ ወደ ውጭ በሚላክ ስንዴ፣ በቆሎ እና ገብስ ላይ የታክስ ጭማሪ አደረገች።
የሩሲያ መንግስት ወደ ውጭ በሚላከው ስንዴ ፣ በቆሎ እና ገብስ ላይ የታክስ ጭማሪ ማደረጉን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ፤ ከሀገሪቱ ወደ ውጭ በሚላክ ስንዴ ላይ የተደረገው የታክስ ጭማሪ በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል፡፡
በዚህም መሰረት አንድ ቶን ስንዴ ወደ ውጭ ሲላክ 101 ነጥብ 4 ዶላር እንዲከፈል መንግስት ወስኗል።
በተጨማሪም ወደ ውጭ ሀገራት የሚላኩ የበቆሎ እና ገብስ ምርት ላይ በተደረገድ የታክስ ጭማሪ አንድ ቶን በቆሎ ወደ ውጭ ሲላክ የሚከፈለው ታክስ 70 ነጥብ 6 እንዲሂም አንድ ቶን ገብስ ወደ ውጭ ሲላክ 75 ነጥብ 4 ዶላር እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል።
በስንዴ፣ ገብስና በቆሎ ላይ የተደረገው የታክስ ጭማሪ በምርቶቹም ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያመጣ አመላካች ነውም ተብሏል።
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ በስንዴ ምርት ላይ ከፍተኛ እጥረት አሊያም የዋጋ ጭማሪ ሊከሰት እንደሚችል ፍርሃቶች መኖራቸው እየተገለፀ መሆኑን አል ዓይን ኒውስ (Al AIN) ዘግቧል።

" ሕዝቡ የሰላም እጦትና ጦርነት አንገሽግሾታል "
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ ለኢፕድ የተናግሩት ፦
" ለብሄራዊ መግባባት ውይይቱ ስኬታማነት ሁሉም መብቱን ሊጠቀምና ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
ወሳኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ሕዝቡ የሰላም እጦትና ጦርነት አንገሽግሾታል፣ ከባድ መስዋዕት ከፍሏል ከዚህ መውጣት ይፈልጋል።
ሁሉንም ነገር ብሄራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ይፈታዋል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው። የኮሚሽኑ ተግባር አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠርና ማመቻቸት ነው። ውሳኔና ሃላፊነቱ የሕዝቡ ነው።
ወጣቶች በስፋት ሊሳተፉ ይገባል። የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያንገበግባቸው፣ ስለኢትዮጵያ ያገባናል የሚል ወገን በሙሉ ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ መጻኢ እጣ ፈንታ ተወያይቶ መወሰን አለበት።
ሚዲያው ለሕዝብ ቅርብ መሆን ለሰላም መስፈን መስራት ይጠበቅበታል።
አጀንዳው የሚሰበሰበው ከሕዝብ ነው። ጉዳዩች ተነቅሰው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በማስቀደም የመጀመሪያ ውይይት ይካሄዳል።
ገለልተኛ የሆኑ፣ የሕዝብን አጀንዳ እንደራሳቸው አድርገው ትክክለኛ የውይይት መርሃ ግብሩን የሚያስፈጽሙ አወያዮች ይኖራሉ።
በጦርነት በርካታ ወጣቶች አጥተናል፣ አካል ጎድሏል፣ ረሃብም አንገሽግሾናል ሕዝቡ ይበቃል ብሏል። ውይይቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለራሱ ሲል እንደሚያሳካው የተስፋ ጭላንጭል ይታየኛል።
አሁን ጉዳዩ አገር ሆኖ የመቀጠልና ያለመቀጠል ስለሆነ ትኩረት በመስጠት ስኬታማ ውይይት ለማድረግ መነሳት ያስፈልጋል።
ውይይቶቹ ወደ መግባባት እንደሚወስዱ ተስፋ እናደርጋለን። የውይይት ውጤቶቹ በእርቅና የአገር ግንባታ ላይ የራሱ ተጽእኖ ይኖረዋል።
ከጅማሬው ስራዎቻችን በጥንቃቄና በጥራት መጀመር አለብን በሚል እምነት ስራዎች እየሰራን እንገኛለን። "
ምንጭ፦ telegra.ph/EPA-04-11

" እስካሁን እኔ ባለኝ መረጃ አንድ ሰው ሞቷል " - አቶ ንጋቱ ዳንሳ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስታዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ አቶ ዛሬ ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ በጅንካ እና አካባቢው በተፈጠረው አለመረጋጋት በንብረት እና በሰው ላይ ጉዳይ መድረሱን አረጋግጠዋል። " በቤቶች ፣ በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል " ያለቱ ዋና አስተዳዳሪው ፥ ጉዳቱ በግለሰቦች ንብረት ላይ አልፎ አልፎም በመንግስት…
#Update
በጅንካ እና አካባቢው የተከሰተውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ እየሰራ ሲሆን ኮማንድ ፖስቱ በባለሁለት እግር ተሽከርካሪ (ሞተር) ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሏል።
ችግሮች በተፈጠረባቸው አካባቢዎች የማረጋጋቱን ስራ ለመስራት የገባው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከክልል ፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የተረጋገጠ ሰላምና ደህንነት እንዲኖር ጥረቱን መቀጠሉ ተገልጿል።

#አቢሲንያ_ባንክ
ገንዘብ በጣም አስፈለገዎት፣ ክፍት የሆነ ባንክ የለም ? የ ኤ.ቲ.ኤም ካርድዎንም አልያዙም ? አይጨነቁ የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን ተጠቅመው በአቅራቢያዎ ከሚገኙት የ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ያለ ካርድ ገንዘብዎን በቀላሉ ማውጣት ይችላሉ።
የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እገዳ ተጥሎባቸው የቆዩትን ቦይንግ 737 MAX አውሮፕላኖች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር ክልል መብረር እንደሚችሉ አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በረራ ቁጥር ET-302 ቦይንግ 737 MAX አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ መሠረት በማድረግ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ሥሪት ተለዋጭ መመሪያ እስካልወጣ ድረስ በኢትዮጵያ አየር ክልል እንዳይበር እገዳ መጣሉ ይታወሳል።
ይሁንና አውሮፕላኑ የተፈበረከበት አገር የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር አውሮፕላኑ ለአደጋው መንስኤ የሆኑ ችግሮችን በመለየት አደጋውን ሊቀርፍ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ በማውጣት መመሪያዎቹ ተግባራዊ እንደሆኑ አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ መመለስ አንደሚችሉ ገልጿል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በአውሮፕላኖቹ ላይ የተደረገውን የዲዛይን ማሻሻያ እና የአየር መንገዱን የበረራ መመሪያዎች እና ሥልጠናዎች በተገቢው ሁኔታ በመፈተሽ አየር መንገዱ መመሪያዋቹን ተግባራዊ ማድረጉን በማረጋገጥ ከዛሬ ጀምሮ ጥሎት የነበረውን የበረራ እገዳ ማንሣቱን አስታውቋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን