TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አይደለም #ዴሞክራሲ እና #ነፃነትን ልንሸከም ቀርቶ ፌስቡክን እንኳን በአግባቡ #መሸከም አልቻልንም። 10,000,000 የላይሞላ የፌስቡክ ተጠቃሚ የ100,000,000 ሰዎችን ኑሮ እያናጋ ነው። ከጥላቻ እና ከስድብ ተቆጠቡ!

#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“በሰበብ አስባብ ግጭት አያስፈልግም፣ እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት ለውጥ ውስጥ ላለ አገር አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው Natural ነገር ነው፤ ታስሮ የተፈታውም ድጋሜ ይገባል አይገባም ድንጋይ ወርውሮ ይሞክራል፣ #ዴሞክራሲ ዝም ብሎ የተከፈተ ስለሚመስል ሰው ራሱን ለመግራት ይቸገራል፡፡ ነገር ግን ይህ ጉዳይ ወደ ሁለት ነገር ነው የሚያመራው፡፡ አንደኛው #በብስለት መብትን መጠየቅና ግዴታን መወጣት ድንበር እንዳለው አውቀን ወደተሻለ ዴሞክራሲ የሚያሸጋግረን ይሆናል፣ ወይም ደግሞ የለየለት #አምባገነን መንግስት እንዲፈጠር ይሆናል። አምባገነን መንግስታት የሚፈጠሩት በህዝባቸው ምላሽ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ውሃ ቀጠነ እያልን መኪና የምንሰባብር ከሆነ መንግስት ፖሊስ ስላለው #የተለመደውን ነገር ማድረጉ አይቀርም፡፡ መንግስት ወደዚያ እንዳይገባ ህዝብ፣ ማህበረሰብ በበሰለ መንገድ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ ክፍት ነው ብለው ሕግን ሕገ መንግስትን እየጣሱ መሄድ ተገቢ አይደለም፡፡ ሕገ መንግስቱ ችግር ያለው እንደሆነ በውይይት፣ በምክክር፣ የህዝቡን ፍላጎት ታሳቢ አድርጎ ማሻሻል ይቻላል፡፡ ሕጉ እያለ ያንን የሚተላለፍ ነገር ማድረግ ይጎዳናል፡፡ ጥያቄ ያለው ማንኛውም ኃይል ሌላውን ሰው #ሳያውክ ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል፡፡ እኔ ስረብሽ ሁላችሁም #ቁሙ ከሆነ ግን ጸረ ዴሞክራሲ ነው”፡፡

▪️▪️ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ▪️▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቦትስዋና 👏 #ዴሞክራሲ

" ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " - ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ

በአህጉራችን አፍሪካ የተረጋጋ የዲሞክራሲ ስርዓት ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደሟ ቦትስዋና ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አድርጋለች።

በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ለ58 ዓመታት ስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዢ ፓርቲ ድምጻቸውን ነፍገውታል።

ፓርቲው አስደንጋጭ ነው የተባለ ሽንፈትን ተከናንቧል።

የፓርቲው መሪና የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል።

ምንም እንኳን እስካሁን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረመው ፓርቲያቸው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ ከፍተኛ ድምጽ አግኝቷል።

የፓርቲው እጩ ዱማ ቦኮ በዓለም ከፍተኛ አልማዝ አምራች ከሆኑት ሃገራት ውስጥ አንዷ የሆነችው ቦትስዋና ፕሬዝደንት ለመሆን ተቃርበዋል።

ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለተቀናቃኛቸው ቦኮ ስልክ በመደወል በምርጫው መሸነፋቸውን ነግረዋቸዋል።

" በዲሞክራሲ ሂደቱ እጅግ ኩራት ተሰምቶኛል። ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " ብለዋል ፕሬዜዳንት ማሲሲ።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ማሲሲ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ሂደት ደስ እንደተሰኙ ገልጸው " የህዝቡን ፍላጎት እና ምርጫ አከብራለሁ " ብለዋል።

ደጋፊዎቻቸውን ረጋ እንዳሉ በእርጋታቸው እንዲቀጥሉና ከአዲሱ የሀገሪቱ መንግስት ጀርባ ተሰልፈው እንዲደግፉ በይፋ ጥሪ አቅርበዋል።

ቦትስዋና በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደም ነች በሚል ስትሞካሽ፣ በዓለም ከሩሲያ በመቀጠል ሁለተኛ የአልማዝ አምራች ሃገር ነች፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ ማግኘቱን ይገልጻል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦትስዋና

ከሰሞኑን በቦትስዋና በተካሄደው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸውን ያመኑት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዜዳንት ዱማ ቦኮ በይፋ በሰላም ፤ አቅፈዋቸውን ስልጣናቸውን አስረክበዋል።

ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ' የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ' ህዝቡ በድምጹ ቀጥቶት ከባድ ሽንፈት አስተናግዶ መሪነቱን ተነጥቋል።

ይህ ፓርቲ አፍሪካ ውስጥ ረጅም ዓመታትን በግዢነት የቆየ ነው።

ተቃዋሚ ፓርቲ የነበረው ' አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ' በከፍተኛ ብልጫ በማሸነፍ ፕሬዜዳንታዊ ስልጣኑን ተቆጣጥሯል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት በምርጫ መሸነፋቸውን ካመኑ በኃላ መላው ህዝብ በአንድነት አዲሱን የመንግሥት አስተዳደር እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በተረጋጋ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

#ዴሞክራሲ #ምርጫ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል። የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው። ሌቪት ፥ ትራምፕ…
#ዴሞክራሲ #አሜሪካ

" ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን

ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የ2024 የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን ዶናልድ ትራምፕ ካሸነፉ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር አድርገዋል።

በዚህም ፥ ለተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ስልክ ደውለው " የእንኳ ደስ ያለዎት !" መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል።

ባይደን ከዲሞክራቷ ዕጩ ካማላ ሀሪስ ጋር እንደተናጋገሩ አስታውቀው " መልካም አጋር እና የሕዝብ አገልጋይ ናት " ብለዋል።

የካማላ የምርጫ ዘመቻን " አነቃቂ " ሲሉ ያሞገሱት ባይደን ምክትል ፕሬዝደንቷ በሥራቸው እንዲኮሩ መክረዋል።

" አንዲት ሀገር ምርጫዋ አንድ ነው። ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ባይደን " ስናሸንፍ ብቻ አይደለም ሀገራችንን የምንወደው፤ ስንስማማ ብቻ አይደለም ጎረቤታችንን የምንወደው " የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አስታውቀዋል።

የምርጫ አስተባባሪዎችም " ምስጋና ይገባቸዋል " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥር 12/2017 በኦፊሴላዊ መንገድ መንበረ-ሥልጣኑን ይረከባሉ።

የ2024 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ " ታሪካዊ ነው " ያሉት ባይደን በሚቀጥሉት 74 ቀናት ያልተቋጩ ሥራዎችን ጨርሰው ሥልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ አሳውቀዋል።

" መሸነፍ ያለ ነው። ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ ይቅር የማንለው ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ የሆነው ለፕሬዝዳንትነት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፎካከሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለተመራጩ ፕሬዝዳንት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ሃሪስ፥ ለትራምፕ ስልክ ደውለው " እንኳን ደስ አለዎ " ማለታቸው ተዘግቧል።

ሃሪስ ለትራምፕ ስልክ ደውለው የ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን በማሸነፋቸው ውጤቱን መቀበላቸውን የሚያመለክት መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዴሞክራሲ 👏 #ሶማሌላንድ

" የምርጫ ውጤቱን እንቀበላለን " - ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።

በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " ምርጫውን አሸንፈዋል።

በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ " የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንትንም " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

" ባስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አልዎት " ያሉት ፕሬዜዳንት ቢሂ " ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ  " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" የአገልግሎት ዘመንዎ ሰላምን ፣ እድገትን እና ዘላቂ ስኬትን ለሀገራችን እንዲያመጣ እመኛለሁ " ብለዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ቢሂ ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት " ፕሬዝዳንታችሁ ሆኜ እንዳገለግላችሁ ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" የስልጣን ዘመኔ ማብቂያ ላይ ሆኜ የምለው ነገር ለሀገራችን እድገት ያለኝ ቁርጠኝነት ጸኑ መሆኑን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በአንድነት እና በጋራ ተነስተን ለሶማሌላንድ ብልፅግና እንስራ " ብለዋል።

6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ " ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት። ከሶማሊያ መንግሥት ጋርም ግንኙነት የላትም። ላለፉት በርካታ ዓመታት ራሷን በራሷ እያስተዳደረች ነው።

እጅግ ሰለማዊ ፣ የተረጋጋ ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግ ትወደሳለች።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
#Somaliland

@tikvahethiopia