TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አክቲቪስት #ጃዋር_መሀመድ በሰሞኑ የሀረር ጉዞ ከህዝብ ጋር ባደረገው ውይይት ከተናገረው በጥቂቱ የተተረጎመ…

(በዘሪሁን ገመቹ)

"ቄሮ ነኝ..ከዚህ በፊት ታግዬ ነበረ... ታስሬ ነበር ስለዚህ አሁን ደሞዜ ሊከፈለኝ ይገባል ብሎ #ዘረፋ ውስጥ የሚገባ..ስልጣን ይገባኛል ብሎ የሚያስፈራራ እሱ ቄሮ ሳይሆን ወያኔ ነው። መኖሪያውም ከሜቴክ ባለስልጣን ጋር ቃሊቲ ነው መሆን ያለበት። ለህዝባችን ነፃነት እንጂ #ለግል ኑሮአችን አልታገልንም። የታገልነውም #መስዋዕትነት የከፈልነውም #ህዝባችን ለምኖን ወይም አስገድዶን ሳይሆን በራሳችን ፍላጎት ነው። ስለሆነም ከ ህዝብ የተለየ ነገር ማግኘት አለብን ብላችሁ የመጠየቅ መብት የላችሁም። ወላጆችም ልጆቻችሁ ለከፈሉት መስዋዕትነት ከማመስገንና ተገቢውን ክብር ከመስጠት ባለፈ ከህግ ውጭ እንዲሆኑ #ፊት_አትስጧቸው...ካለበለዚያ #አሸባሪ ነው የሚሆኑባችሁ። ቄሮ ማንኛውንም መኪና ኮንትሮባንድ የጫነ ነው ብሎ ሲጠረጥር ለፓሊስ እና ለህግ አካላት #መጠቆም እንጂ #የመፈተሽ_ስልጣን_የለውም። እንደዛ ማድረግ በቄሮ ስም ለሚነግዱ #ዘራፊዎች ሁኔታዎችን እያመቻቸሁላቸው ስለሆነ አካሄዱ መስተካከል አለበት። ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመት መንግስታችን አንድ ነው ። አሁን ስልጣን ላይ ያለው። አዲስ አበባ ተመዝግቦ መጥቶ ፅ/ቤት የሚከፍት ማንኛውንም ፓርቲ ተቀበሉት፣ቢሮውን እንዲከፍት አግዙት፣ ኑሯችሁን እንዴት ለማሻሻል እንዳሠበ ቁጭ ብላችሁ ስሙ..ከዛ ቀኑ ሲደርስ የተሻለውን #ትመርጣላችሁ..ካዛ ውጭ ግን ዛሬ አዲስ:አበባ ተቀምጦ #ፓለቲካ_እያወራ እዚህ መሳሪያ #እንድትታኮሱ የሚጠይቃችሁ ካለ እሱ #ጠላታችሁ ስለሆነ ከተማችሁ ሳይገባ በሩቁ ተከላከሉት። የነፃነትን #መጠጥ በልኩ ጠጥቶ #መደሰት አግባብ ነው…ተገኘ ተብሎ ከመጠን በላይ በመጠጣት መስከር ግን ጥፋት ነው። ሪፎርሙ #ከከሸፈ በፊት ወደነበርንበት አንመለስም...እንደሱማሌ እና ዪጎዝላቪያ #በመፈረካከስ ተጫርሰን #እናልቃለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በአሸባሪነት የተፈረጁ አካላትና ያልተፈረጁ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት በሀገራዊ ምክክሩ ይሳተፋሉ ?

በኢፌዴሪ ህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብለው የተፈረጁም ሆነ ያልተፈረጁም " ትጥቅ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ " ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሀገራዊ ምክክር መድረኩ አካል ይሆናሉ ? ? የሚለው ጥያቄ የብዙሃኑ ጥያቄ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ በርካቶች የገዢውን 'ብልፅግና ፓርቲ' ቁርጥ ያለ አቋም ምን እንደሆነ ለማወቅም ይፈልጋሉ።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አደም ፋራህ በፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህንን ጥያቄ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ አደም " ተሳታፊን መለየት እና መወሰን የብልፅግና ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። " ብለዋል።

ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የሀገራዊ ምክክር የኮሚሽኑ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ነገር ግን ኮሚሽኑ እነዚህ አካላት ለምክክሩ እና ለሀገር አቀፍ አካታች መድረክ እንዲቀርቡ ቢወስን ብልፅግና ይቀበላል ወይ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ አደም ፋራህ ፦

" ብልፅግና ለአካታች ሀገር አቀፍ ምክክሩ ስኬታማነት አስተዋጽኦ የሚያበረክት ጉዳይ በሙሉ ፤ ኢትዮጵያ እንድትረጋጋ ፤ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ፤ ዴሞክራሲ እንዲዳብር ፤ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ማንኛውም ጉዳይ ኮሚሽኑ ይዞ ከመጣ ህግና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ፤ አስፈላጊ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ዝግጁ ነው " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሌላው እዚህ ላይ የተነሳ ጥያቄ እንዴት ነው ኮሚሽኑ ቢፈልግ እንኳን በህግና ስርዓቱ በአሸባሪነት የተፈረጁ አካላት ተሳታፊ መሆን የሚችሉት ?

በህግ እና በስርዓቱ አሸባሪ ተብለው የተፈረጁ አካላት ትጥቃቸው እስካልፈቱ ድረስ እንዲህ ያለው ሰላማዊ መድረክ ላይ አይሳተፉም ይላል። ስለዚህ " ብልፅግና በሁለት ካርድ እየተጫወተ ነው " ፤ በሚል ለሚነሳው ክስ አቶ አደም ፋራህ ተከታዩን ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል ፦

" የህግ የበላይነት የሚባለው ለሁሉም አካል በህግ ፊት እኩል ነው። ሁሉም ከህግ በታች ነው። እንዳሻው ህግን የመጣስ መብት የሚሰጠው አካል አይደለም።

ብልፅግና ፓርቲም ህዝብ ሲመርጠው ህግና ስርዓትን አስከብር፣ በሀገሪቱ ህግ ምራኝ ፣ በህግ እና ስርዓት ምራኝ ፣ ሰላም እና ደህንነትን አስከብር፣ በማኔፌስቶው ላይ ያስቀመጥከውን በትክክል ተግብር ፣ ፈፅምልኝ ነው ያለው። ስለዚህ ብልፅግና ፓርቲ ከህግ እና ስርዓት ውጪ ወስኖ የመሄድ ስልጣን የለውም። ኮሚሽኑም በዛው ልክ ነው።

ዋናው ጉዳይ ፤ ኮሚሽኑ ለአካታች የሀገራዊ ምክክሩ ስኬትታማነት ፣ የሚለዩትን አጀንዳዎችና አጀንዳዎቹ ላይ መሳተፍ የሚገባቸው አካላት ከለየ በኃላ እነዚህ አካላት በዚህ ጉዳይ ላይ ቢሳተፉ ለአካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ይጠቅማል ብሎ ካመጣው ፤ ብልፅግና ለሀገርና ለህዝብ ነው ቅድሚያ የሚሰጠውና ይቀበላል።

የቀረበው የሀገርን እና የህዝብን ጥቅም የሚያስከብር ከሆነ ሲያስፈፅምም ህግና ስርዓትን በጠበቀ አኳኃን ነው የሚያስፈፅመው።

ስለዚህም ፤ አንድ #አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ድርጅት ከአሸባሪነት የሚወጣው በምን ስርዓት ነው የሚለው ህግ እና ስርዓት ያስቀመጠው አለ ፤ ስለዚህ ህግ እና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ነው የምናስተናግደው።

እንደብልፅግና ፓርቲ ለአካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬት በእኛ አቅም፣ በእኛ ስልጣን ማድረግ የሚገባንን ነገር በሙሉ እናደርጋለን። ይሄን ስናደርግ ህግ እየጣስን መሆን የለበትም። ስለዚህ ህግ እና ስርዓትን በጠበቀ መንገድ ሂደቱን ጠብቀን ኮሚሽኑ የሚያቀርባቸውን ነገሮች እንደመንግስት ተቀብለን የምናስተናግድበት እና ለአካታች የሀገራዊ ምክክሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ፤ ሁኔታዎችን የምናመቻችበት ሁኔታ ይኖራል።

ስለዚህ ሁላችንም ከህግ በታችን ነን ፤ ብልፅግናም ሲሰራ እያንዳንዱ እንቅስቃሴው ሂደቱ በህገመንግስቱ መሰረት ፣ በሀገሪቱ ህጎች መሰረት መሆን መቻል አለበት።

መሻሻል የሚገባው ህግ ካለ ፤ ለዚህ ሂደት እንቅፋት ሊሆን ይችላል ወይም ምቹ ሁኔታ አይፈጥርም ተብሎ የሚታሰብ ካለ የህግ ማሻሻያ ሂደቱን ተከትለን ነው የምናሻሽለው እንጂ ብልፅግና መሪ ፓርቲ ስለሆነ ይሄን ጥዬዋለሁ ፣ ይሄን ፈቅጃለሁ የሚልበት ሁኔታ አይኖርም።

ግን ፥ ለአካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ እንደ መንግስትም ፤ እንደ መሪ ፓርቲም እኛ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ፣ አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ ፣ ህግ የሚፈቅድልንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ፤ ቁርጠኛ ነን ፤ በትክክልም እናደርገዋለን " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#RUSSIA ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች። የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል። ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦ ° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)…
#ሩስያ

ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት #የግብረሰዶም እንቀስቃሴን #ሕገወጥ እና #ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን #የአክራሪነት እና #የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።

በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።

ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች #አክራሪ እና #አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።

በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት / ባር ሰራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዛው እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወሷል።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር።

በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)
° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።

በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም

በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia