TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Somali

የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል ፈተናዎችን በክልሉ ለሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ማከፋፈል ጀመረ።

በሶማሌ ክልል የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል ፈተናን ከሰኔ 21 እስከ ሰኔ 23 ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

በክልሉ በሚገኙ 735 ትምህርት ቤቶች 44,144 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትላንት ሰኔ 11 ጀምሮ ለዘንድሮ አመት የተዘጋጀውን የ8ኛ ክፍል ፈተናዎችን በክልሉ ለሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ማከፋፈል ጀምሯል።

ፈተናዎቹ ታትም በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነበር የቆዩት። #SMMA

@tikvahethiopia