TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MustafaMohammed

የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን በሚመለከት ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

• የክልሉ ህዝብ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት፣ በዜጎች ህይወት ልያስከትል የምችለውን አደጋና የክልሉ ህዝብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥንቃቄዎች አይመጣጠንም ብለዋል።

• የሶማሌ ክልል ህዝብ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ከፌዴራል እና ከክልሉ መንግሥት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መተግበሪያዎችና መመሪያዎችን በአግባቡ ተግባራዊ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

• የሶማሌ ክልል በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠረጠሩ እና የተገኘባቸው ሰዎችን የለይቶ ማቆያና የህክምና ድጋፍ የሚሰጡ ማዕከላትን ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።

• የክልሉ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ ለመግታት የተለያዩ ኮሚቴዎች ማቋቋሙን ተናግረዋል።

• የህክምና ባለሙያዎች ቀን ተሌሊት በወትሮ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

• ፀጥታ አካላቱ ከአጎራባች ሀገራትና ክልሎች ምንም አይነት የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት እንዳይገቡ ተሰማርተዋል።

#SRTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia