TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BidenHarris

"... ቆጠራው ሲጠናቀቅ እኔ እና ካማላ ሀሪስ (ምክትላቸው) አሸናፊነታችን ይፋ እንደሚደረግ አልጠራጠርም" - ጆ ባይደን

* ከሰዓታት በፊት የተናገሩት (AlAIN)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BidenHarris

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትረምፕን ያሸነፉት ጆ ባይደን ከወዲሁ የአስተዳደር ርክክብ ዝግጅት ፈጥነው ጀምረዋል።

በመጪው ጥር 20 (እ.አ.አ) ቃለ መሃላ ፈጽመው ሲረከቡ ቁልፍ የሆኑ የትረምፕ ፖሊሲዎችን ይቀለብሳሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ፥ ጆ ባይደን 'በጠባብ አጠቃላይ ድምጽ' ባሸነፉባቸው ክፍለ ግዛቶች ላይ የተፈጸሙ የድምጽ ቆጠራ መዛባቶች ሲፈተሹ ውጤቶቹ ተቀልብሰው አሸናፊ እኔ እሆናለሁ በማለት ክሶች መስርተዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ ትናንት የሽግግር ዌብሳያታቸውን ከፍተዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ በምርጫው መሸነፋቸውን ለመቀበልም ሆነ ለጆ ባይደን ስልክ ደውለው ለማነጋገር ፈቃደኛ አልሆኑም ሲል #ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia