TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዳማ ግጭት ተፈጥሮ በነበረበት ቦታ አሁን ላይ መረጋጋት አለ። ግጭቱ በተፈናቃዮች እና በአዳማ ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረ ነው።

ይህ አጋጣሚ ተጠቅመው ግጭቱን የብሄር ግጭት ለማስመሰል በፌስቡክ የሚፃፉ ፅሁፎችን እየተመለከትን እንገኛለን ነገር ግን #ማረጋገጥ የቻልነው በአዳማ የተፈጠረው ግጭት ምንም አይነት የብሄር መልክ የያዘ ግጭት እንዳልነበረ ነው። ከዚህ ባለፈም በፌስቡክ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ ተብሎ የሚወራው #ውሸት ነው ምንም ቤተ ክርስቲያን አልተቃጠለም።

*ስለደረሰው ጉዳት ተጨማሪ መረጃዎች እየመጡልኝ ስለሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ጌታቸው ከሀገር ወጡ??❗️

ይህ የአንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ዘገባ ነው...

"ሰበር ዜና-ከአዲስ አበባ ለአዋዜ የደረሰው ትኩስ ዜና። የቀድሞው ተፈሪ የብሄራዊ ስለላና ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ ከኢትዮጵያ #ጠፍተው ሱዳን መግባታቸው በይፋ #ተረጋገጠ። አንድ ከፍተኛ ውስጥ አዋቂ ምንጭ ምሽቱን ለአዋዜ እንደተናገሩት ከሆነ ፌደራል መንግስቱ በህግ ይፈልጋቸው የነበሩ ባለስልጣን ናቸው ጌታቸው አሰፋ።

ማዕከላዊ መንግስቱ በይፋ በህግ #ሊጠይቃቸው እና #ሊፋረዳቸው የሚፈልጋቸው ባለስልጣን ሆነው ሳሉ በትግራይ ፖሊስ ሽፋን ወደ ሱዳን እንዲወጡ አድርጓል ብለዋል ለአዋዜ። በዚህ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።"

ጋዜጠኛ አለምነህ ጨምሮ እንደገለፀው ከሆነ እየተደረገ በሚገኘው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ አቶ ጌታቸው አሰፋ አልተገኙም። ይህም የሆነው ከሀገር በመውጣታቸው ነው ብሏል ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ ከምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ እንዲህ ብሎ በሰበር ዜናው ዘግቧል⬇️

"የእስር ማዘዣ የተቆረጠባቸው የቀድሞ የደህንነት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሱዳን #መሸሻቸው ተነገረ።"

◾️ውድ የተከባራቹ የቻናላችን ቤተሰቦች ይህን ዜና #እስካሁን ድረስ ከሌሎች የመንግስትም ሆነ የግል የሚዲያዎች #ማረጋገጥ አልተቻለም።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርቅ ኮሚቴ አባላት ታፍነው ተወሰዱ‼️

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥትን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የግንባሩን ወታደሮች #ለመቀበል ወደ #ቄለም_ወለጋ አቅንተው የነበሩ ከሦስት ያላነሱ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላት #ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል።

የእርቅ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ #በየነ_ሰንበቶ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የኮሚቴው አባላት የሆኑ ሁለት አባ ገዳዎች እና አንዲት ሴት በቄለም ወለጋ #አንፊሎ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ታፍነው እንደተወሰዱ ተናግረዋል።

አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ''ለማግባባት ወጣ እንዳሉ ነው ታፍነው የተወሰዱት፤ ክፉ ነገር #እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ነኝ። ይህንም ችግር በቅርቡ እንፈታዋለን'' ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

''ብዙ ፈተናዎች እንደሚኖሩን እየወቅን ነው እርቅ ወደማውረዱ የገባነው። እርቅ ለማምጣት ነው እየሰራን ያለነው። ሰላምም ይሰፍናል። የሚያጋጥሙን ችግሮች ወደ ኋላ አያሰቀሩንም'' ሲሉም ጥረታቸውን በዚህ ምክንያት እንደማያቋርጡም ተናግረዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቢቢሲ ያነጋገረው የየኮሚቴው ፀሃፊ #ጀዋር_መሃመድም የእርቅ ኮሚቴ አባላት ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ተናግሯል።

''የገጠመ ችግር አለ። በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ከኮሚቴው አባላት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ለህዝቡ መግለጫ እንሰጣለን'' ሲል ጀዋር ገልጿል።

ጀዋር ሃሙስ ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ ታፍነው ተወስደዋል ያላቸውን አራት ሰዎች ከስም ዝርዝራቸው ጋር አውጥቷል። ታፍነዋል ተወስደዋል የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግሯል።

በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ወለጋ መነ ሲቡ ወረዳ የቴክኒክ አባላቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከነዋሪዎች ተሰምቷል። ተፈጸሟል ስለተባለው ድብደባ ግን ከቴክኒክ ኮሚቴው አባላት #ማረጋገጥ አልተቻለም።

የእርቅ ኮሚቴ አባላቱን ማን አፈናቸው?

የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶም ሆኑ የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድ የእርቅ ኮሚቴውን አባላት ያፈነው ኃይል ይህ ነው በማለት በስም ከመጥቀስ #ተቆጥበዋል

ጀዋር የአባላቱን መታፈን ይፍ ባደረገበት ጽሁፍ ''እየደረሰብን ያለውን #ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን። አባ ገዳዎች፣ እናቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር ሰላም እና እርቅ ለማውረድ ነው የሚደክሙት እንጂ ምንም በደል አልፈጸሙም። በአስቸኳይ እንዲለቀቁን እንጠይቃለን'' ሲል በፌድቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ደለሳ ቡልቻ ለሁለት ቀናት ታፍነው ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸው ይታወሳል። ዶ/ር ደለሳ የገጠማቸውንና ማን እንዳፈናቸው ለመናገር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ባንኮች በተዘረፉበት ወቅትም የባንክ ሰራተኞችም ታፍነው ተወስደው እንደነበረ ይታወሳል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የባለ ዕድለኛ የዕጣ ዝርዝር ላይ ስማችሁን ማግኘት ያልቻላሁ / ባለዕድለኛ #መሆን #አለመሆናችሁን ማረጋገጥ የምትፈልጉ ፦ - በቅድሚያ የPDF ፋይሉን https://t.iss.one/tikvahethiopia/74809 አውርዱ (Download) - በመቀጠልም ከላይ በምስሉ የሚታየውን የመፈለጊያውን ምልክት ተጫኑ፤ - በመጨረሻም ስማችሁን በማስገባት የመፈለጊያውን ምልክት…
Addis Lissan Hidar 8-2015 .pdf
52.3 MB
የ20/80 እና የ40/60 የቤት ባለዕድለኞች የስም ዝርዝር በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ (በልዩ ዕትም) ታትሞ ወጥቷል።

ከላይ የተያያዘው " የአዲስ ልሳን " ጋዜጣ ቅጂ (ሶፍት ኮፒ) ነው።

ከላይ የተያያዘውን " 52.3 MB " PDF ፋይል በማውረድና በመክፈት የመፈለጊያ ምልክቷን በመጫን ስምዎትን በአማርኛ / በእንግሊዝኛ በማስገባት ስምዎት በጋዜጣው ላይ ታትሞ ስለመውጣቱ #ማረጋገጥ ይችላሉ።

Credit : Addis Lissan

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል።

የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የትምህርት ሚኒስቴር አካላት #ማረጋገጥ ችሏል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት #በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ኘሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደትም እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስመቅጧል።

2ኛ. በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 /2015 እስከ ሐምሌ 13 /2015 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።

3ኛ. የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

በተጨማሪም እንደ አገር ዓመታዊ የትምህርት ካላንደር ከ2016 ጀምሮ ለማስተካከል ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚሁ ማዕቀፍ አንዲያስተካክሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል።

ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የተለያዩ #ያልተረጋገጡ መረጃዎችን እየሰሙ አለመረጋጋት ውስጥ መግባታቸውን ሲገልፁልን ነበር ፤ በቀጣይም ትምህርት ሚኒስቴር / የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሚሰጡትን ትክክለኛ መረጃ #ብቻ እንድትከታተሉ ፤ በቀረው አጭር ጊዜም ዝግጅታችሁን ታጠናክሩ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።

(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል #ትክክለኝነቱን ያረጋገጠው ነው።)

@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT
" ሞሳድ " ኢራን ውስጥ ገብቶ አንድን ግለሰብ ጠልፎ መወሰዱ ተሰማ።

ለመገናኛ ብዙሃን እምብዛም መረጃ የማይሰጠው የእስራኤሉ የስለላ  ድርጅት "ሞሳድ" ቆጵሮስ ውስጥ እስራኤላውያንን ለመግደል አቅዷል የተባለ ቡድን መሪ ነው ተብሎ የተጠረጠረን ግለሰብ ኢራን ውስጥ ዘልቆ በመግባት ለመያዝ መቻሉን አስታውቋል።

"ሞሳድ" በእስራኤላውያን ዜጎች ላይ ቆጵሮስ ውስጥ ግድያን ሊፈጽም ስለነበረው ገዳይ ቡድን ለቆጵሮስ ባለሥልጣናት መረጃ መስጠቱን እና ጥቃት ፈጻሚ ህዋሱም እንዲበተን መደረጉን አመልክቷል።

"ሞሳድ" ባወጣው መግለጫ ላይ ተካሄደ ያለውን ተልዕኮ "በኢራን ግዛት ውስጥ የተፈጸመ ልዩ ድፍረት የተሞላበት" በማለት ገልጾታል።

አንድ ከፍተኛ የሞሳድ ከፍተኛ ባለሥልጣን፤ "በየትኛውም የዓለም ክፍል ውስጥ በሚገኙ አይሁዳውያን እና እስራኤላውያን ላይ የሽብር ጥቃትን የሚያስፈጽሙ ባለሥልጣናትን የኢራን ግዛትን ጨምሮ ባሉበት ቦታ ሁሉ እናገኛቸዋለን" ስለማለታቸው ተነግሯል።

ይህ የሞሳድ ኦፕሬሽን ለረጅም ዘመናት በጠላትነት ሲፈላለጉ በነበሩት እስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ተዘዋዋሪ ፍልሚያ መቀጠሉን ያመለክታል ተብሏል።

እስራኤል ቆጵሮስ ውስጥ ዜጎቿን ለመግደል በኢራን አማካይነት ተቀነባብሮ ነበር ያለችውን ሴራ ከገለልተኛ ወገን #ማረጋገጥ ያልተቻለ ሲሆን ከኢራንም ሆነ ከቆጵሮስ በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

በ "ሞሳድ" የተያዘው ግለሰብ ምን አለ ?

በእስራኤል ባለሥልጣናት ይፋ በተደረገ ቪዲዮ ላይ ዋነኛ ተጠርጣሪ እንደሆነ የተገለጸው ዩሴፍ ሻሃባዚ የተባለ ግለሰብ ከኢራን ውጭ ለ " ሞሳድ " ወኪሎች በፋርስ ቋንቋ ሲናገር አሳይቷል።

በዚህ ቪድዮ፥ ግለሰቡ አንድ እስራኤላዊ ነጋዴን ለመግደል በቱርክ ቁጥጥር ሥር ወዳለው ሰሜን ቆጵሮስ በመግባት በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡቡ ክፍል መግባቱን ያስረዳል።

የግለሰቡን አድራሻና ፎቶግራፍ በኢራን አብዮታዊ ዘብ ውስጥ ያለ አዛዡ እንደላከለት ተናግሯል።

"ግለሰቡን እዚያ መኖሩን እና የት ሊሄድ እንደሆነ ካወቅኩ በኋላ ዕቅዴ እንቅስቃሴ የሌለበት እና ጸጥ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር በጥይት መግደል ነበር" በማለት ሲናገር ይሰማል።

ግለሰቡ ኢላማው የሆነውን እስራኤላዊ ከለየ እና የመኖሪያ ቤቱን ፎቶ ካነሳ በኋላ፣ በፖሊስ እየተፈለገ መሆኑ ስለተነገረው ከቆጵሮስ በመውጣት ወደ ኢራን ተመልሷል ተብሏል።

በሞሳድ ከኢራን ተይዞ የወጣውና ግድያውን ሊፈጽም እንደነበር ሲያምን በቪዲዮ የተቀዳው ግለሰብ በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ቃሉን እየሰጠ ይሁን አይሁን ግልጽ አይደለም።

ግለሰቡ መቼ ተያዘ ?

"ሞሳድ" ግለሰቡን ከኢራን ግዛት ውስጥ መቼ እና ከየት ቦታ ይዞ እንዳወጣው እንዲሁም ቆጵሮስ ውስጥ ሊፈጸም የነበረው ጥቃት ለመቼ ታስቦ እንደነበር ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

የእስራኤል እና ኢራን ግንኙነት...

እስራኤል፤ ኢራንን ለረጅም አመታት እንደ ዋነኛ ጠላቷ አድርጋ ትቆጥራታለች።

የኢራን መንግሥት እስራኤልን ለማውደም የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ዛቻና ጥቃት የሚፈጽሙባትን ታጣቂ ቡድኖችን ትደግፋለች በሚል ነው እንደጠላት የምታያት።

እስራኤል ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለመገንባት እየጣረች መሆኗን ታምናለች።

በቅርብ ዓመታት እስራኤል በኢራን የኑክሌር ተቋማት ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን የፈጸመች ሲሆን በርካታ የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቶችን በመግደል ትከሰሳለች።

ከ5 ዓመት በፊትም የሞሳድ ወኪሎች በኢራን ዋና ከተማ የሚገኝ የሰነዶች ማከማቻን ሰብረው በመግባት ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የኑክሌር መረሃ ግብርን ሰነዶች መዝረፋቸውን እስራኤል አሳውቃ ነበር።

ኢራን ምን አለች ? 👉 telegra.ph/MOSAD-07-01

(BBC, NuR)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከትላንት ምሽት አንስቶ በኢትዮጵያ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ  እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዲገደቡ መደረጉ ታውቋል። አገልግሎቶቹ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ማለትም በኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በሳፋሪኮም በኩል እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል። ከማህበራዊ መገናኛዎቹ አገልግሎት መገደብ ጋር በተያያዘ በሌሎች ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ውስጥ እስካሁን የታየ መቆራረጥ…
#ETHIOPIA

ማህበራዊ ሚዲያዎች ያለ VPN መስራት ጀመሩ።

ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ለማረጋገጥ ችሏል።

#ቴሌግራም ፣ ዩትዩብ ፣ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ መሰል የማህበራዊ ሚዲያዎች ከወራት በፊት (የካቲት ወር 2015 ዓ/ም) በተጣለባቸው ገደብ ያለ VPN መስራት እንዳቆሙ ይታወቃል።

ዛሬ ሰኞ ከሰዓታት በፊት ግን እነዚህ የማህበራዊ ሚዲያዎች #ያለ_VPN_እየሰሩ እንደሚገኙ እና ገደቡም መነሳቱን #ማረጋገጥ ችለናል።

@tikvahethiopia
#Amhara

በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን በአድርቃይ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት 15 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳደር አሳውቀዋል።

ይህ አካባቢ የትግራይ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ነው።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

- ባለፈው ማክሰኞ ግንቦት 27 ከንጋቱ በ11፡00 ሰዓት አሊጣራ ቀበሌ አንካቶ በተባለ ጎጥ የቡድን መሳሪያ #ከትግራይ_በኩል በመጡ የታጠቁ ኃይሎች ከባድ ጥቃት ተከፍቶ ነበር።

- ጥቃቱ ከንጋቱ 11፡00 ጀምሮ እስከ ጠዋት 2፡30 ገደማ ነበር የዘለቀው።

- አንድ የአካባቢው ነዋሪ ፥ " #በአንድ_ቤት 5 ነበርን፣ ከአምስታችን እኔ ነኝ በአጋጣሚ የተረፍኩት፤ ሌሎቹ ሞቱ። አሰልፈው ነው የተኮሱብን።...እኔንም ሞቷል ብለው ነው ትተውኝ የሄዱት። በፈጣሪ ፈቃድ ነው የተረፍኩት ፤ ጀርባዬን በጥይት ተመትቼ ሆስፒታል ነው ያለሁት " ብለዋል።

- ሌላ ነዋሪ ፤ " በጥቃቱ 15 ሠዎች መገደላቸውን በዐይኔ ተመልክቻለሁ። ሁለት የ16 እና የ19 ዓመት የእህት ልጆቼም ተገድለዋል። " ሲሉ ተናግረዋል።

- ሌላኛው ነዋሪ ፥ " በእሳት እና በጥይት 3 ታዳጊዎችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል። ህጻናትን ጨምሮ 15 ሠዎች መገደላቸውን አይቻለሁ " ብለዋል።

- የአካባቢው #የሚሊሻ አባል ፤ " ከጥቃት ፈጻሚዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ነበር። አብሮኝ የነበረው ታናሽ ወንድሜ በጥቃቱ ተገድሏል። ቦምብ ጉዳት አድርሷል፤ ጥይቱ፤ መሳሪያውም ብዙ ስለሆነ፤ ድሽቃ፣ ስናይፐር፣ ብሬን አላቸው። በእርቀት እየተኮሱ ነው ጉዳት ያደረሱት " ብለዋል።

-  ታጣቂዎቹ አካባቢውን ለቀው ሲወጡ 3 ሰዎችን ወስደዋል። 500 ከብቶችን ዘርፈወል። ቤቶችም ተቃጥለዋል።

ወረዳው ምን አለ ?

ዋና አስታዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ታደሰ ጥቃቱን የፈጸሙት በዋልድባ ገዳም በኩል አድርገው የገቡ የትግራይ ኃይሎች ናቸው ብለዋል።

ቀብራቸው መፈጸሙን #ማረጋገጥ የቻሉት የስምንት ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከ8ቱ ሟቾች መካከል 6ቱ #ንጹሃን_ነዋሪዎች እንደሆኑ 2ቱ የአካባቢው ሚሊሻ አባላት እንደነበሩ ገልጸዋል።

ጥቃተ የፈጸሙት የትግራይ ኃይሎች ስለመሆናቸው በምን እንዳወቁ ተጠይቀው ፥ ነዋሪዎች በሚናገሩት ቋንቋ እንደለይዋቸውና በተለያዩ ጊዜያትም ትንኮሳዎችን ይፈጽሙ እንደነበር ገልጸዋል።

" የትግራይ ታጣቂዎች ናቸው። ከእነሱ ውጪ የሚመጣብን ሌላ እንደሌለ ነው የተረዳነው " ብለዋል።

" ቡድኑን የሚመራውን ግለሰብ ጭምር እናውቃለን ፤ የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ቦታው ይገባኛል የሚነሳባቸውን አካባቢዎችን ለመያዝ " ስልታዊ " መሆኑን ተንተርሶ ጥቃቱ ሳይፈጸም አልቀረም ብለዋል።

" የማንነት ጉዳይ ሚነሳባቸውን አካባቢዎች በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የግድ የእኛን አካባቢ ማጥቃት አለባቸው። በ2013ም የተመለከትነው ይህን ነው። ስለዚህ ይህን አካባቢ የመቁረጥ፤ ቆርጦ መሀል ላይ ያለን የመንግሥትን መዋቅር የማጥቃት ፍላጎት አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምን ምላሽ ሰጠ ?

የትግራይ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ባልደረባ አቶ አማረ ኃይሌ ፤ የትግራይ ኃይሎች ጥቃት አልፈጸሙም ብለዋል።

" እስካሁን ድረስ ወደዚያ አካባቢ ያደረግነው ምንም እንቅስቃሴ የለም " ብለዋል።

" እኛ ያለንበት ቦታና አሁን እየተባለ ባለው ቦታ በጣም ሰፊ ርቀት ነው ያለው። በቀጥታ የሚዋሰን ቦታም አይደለም " በማለት ጥቃቱን እንዳላደረሱ ገልጸዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " ያሉ ችግሮችን ግጭት አልባ በሆነ መንገድ ለመፍታት ነው የሚያስበው ወደ ግጭት የመግባት ሁኔታ የለንም " ብለዋል።

Credit - BBC AMHARIC

@tikvahethiopia