TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ወለጋ‼️

በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረት #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።

የኮማንድ ፖስቱ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ #ደጀኔ_ገብረማርያም እንደገለጹት በዞኑ በነበረው የፀጥታ ችግር የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት ተመልሰዋል። ከነዚህም 110 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 41ሽጉጦችና 20 የእጅ ቦምቦች ይገኙበታል። እንዲሁም 326 ኋላ ቀር ጠመንጃዎችና ከአራት ሺህ የሚበልጡ ጥይቶች መመለሳቸውን አስረድተዋል።

በተጨማሪም 50 በርሜል ነዳጅ፣ 14 የመንግሥትና የግል ተሽከርካሪዎችና 28 የሞተር ቢስክሌቶች መመለሳቸውን አቶ ደጀኔ ተናግረዋል።

የዞኑ ሕዝብ የተዘረፉትን የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት ለማስመለስ በተደረገው ጥረት ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው መንቀሳቀሱን ገልጸዋል።

በዞኑ በ20 የገጠር ወረዳዎችና ሦስት ከተሞች በተካሄዱት የሰላም ኮንፈረንሶች አንፃራዊ #ሠላም በመስፈኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ በካማሺና የምዕራብ ወለጋ ዞኖች መካከል የሕዝብ ለሕዝብ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡

የመነ ሲቡ ወረዳ የአስተዳደርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ #ለታ_አባተ በሰጡት አስተያየት ሕዝቡና ኮማንድ ፖስቱ ባደረጉት ክትትልና ቁጥጥር የጦር መሣሪያዎቹ መመለሳቸው ለዞኑ ሰላምና ጸጥታ መከበር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡ አሁንም ያልተመለሱትን የጦር መሣሪያዎች ለማስመለስ ተቀናጅቶ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

የመንዲ ከተማ የአስተዳርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ #ዳኖ_ኢተፋ በበኩላቸው የተዘረፉት የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት መመለሳቸው ለሰላም ያላቸው ፋይዳው ጉልህ ነው ብለዋል። የምዕራብ ኢትዮጵያ ከዚህ ዓመት መግቢያ ጀምሮ በተከሰተው ግጭት ሰላምና ጸጥታው ታውኮ መቆየቱ ይታወሳል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia