TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️መድሀኒአለም አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ውጥረቱን #ለማርገብ እና ህዝቡን #ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ ይገኛል።

ፎቶ፦ አንተነህ እና Xo (TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል⬇️

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች #የጸጥታ ችግር መከሰቱ ተገለጸ።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞንና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች በተከሰተው የጸጥታ ችግር በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡

አሁን ለተከሰተው የጸጥታ ችግር መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች በምዕራብ ወለጋ ዞን ቢላ አሙማ አገሎ በተባለው ስፍራ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የከማሺ ዞን አመራሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት 4 የከማሺ ዞን አመራሮች #መገደላቸውን ተከትሎ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡

በእነዚህ ታጣቂዎች ግድያ የተፈጸመባቸው የከማሺ ዞን አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ከተላኩ አመራሮች ጋር ከዚህ ቀደም ከክልሉ #ተፈናቅለው የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ወደነበሩበት #በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ በአሶሳ ከተማ ተወያይተው ወደ ከማሺ ዞን በመመለስ ላይ እያሉ ነበር ተብሏል፡፡

በከማሺ ዞንና እንዲሁም በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞን ስር በሚገኙት የሳስጋ፣ ድጋ፣ ሐሮ ሊሙ፣ ሊሙ፣ ቦጂ ብርመጂ ወረዳዎችና በሌሎች አከባቢዎች በተከሰተው በዚህ ግጭት ከነቀምቴ ሆስፒታል በተገኘው መረጃ መሰረት እስከ አሁን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል፣ በርካቶች ቆስለዋል፣ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል፡፡

በተከሰተው ችግር ሳቢያ በቤንሻንጉል ክልል ሲኖሩ የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ተፈናቅለው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ወሰን አካባቢ ወደሚገኙት የኦሮሚያ ወረዳዎችና ወደ ነቀምቴ ከተማ መሰደዳቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡

በአከባቢው የተከሰተውን ችግር #ለማረጋጋት የጸጥታ ኃይሎችና የአስተዳደር አካላት፣ የፌዴራል መንግስትና ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም የኮሙኒኬሽን ቢሮው ገልጿል፡፡

በዜጎች ላይ ለደረሰው ጉዳት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ገልጿል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላላም ጃለታ በበኩላቸው፣ በአከባቢው የጸጥታ ችግር መከሰቱን አምነው፣ በከማሺ ዞን የሚገኙት ነዋሪዎች ጥቃት ይደርስብናል በሚል ፍርሃት የጉሙዝ ተወላጆች ቤታቸውንና ንብረታቸውን ትተው ወደ ጫካ #እየተሰደዱ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ደግሞ ወደ አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች እየተሰደዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር በርካታ የኦሮሞ ማህበረሰብና የጉሙዝ ተወላጆች ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰመጉ⬇️

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው #ጅምላ እስር በመንግሥት ሙሉ ማብራሪያ ሊሰጥበት እንደሚገባ፣ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ጥያቄ አቀረበ፡፡ #ሰመጉ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

ሰመጉ በመግለጫው ምንም እንኳን ፖሊስ ከተማዋን #ለማረጋጋት ዕርምጃ መውሰዱ #ተገቢ እንደሆነ ቢያምንም፣ ‹‹ከሕግ አግባብ ውጪ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጠነ ሰፊ እስራት መፈጸሙ፣ የጅምላ እስራቱ ሰላማዊ ዜጎችንም ጭምር ዒላማ ማድረጉ፣ ጥቂት የማይባሉ ታሳሪዎች ላይ ፖሊስ ድብደባ መፈጸሙ፣ በሕግ ወንጀል  እንዳልሆነ በግልጽ ባልተደነገጉ ሥፍራዎች ያገኛቸውን ዜጎች ማሰሩ፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እስራቶቹ መፈጸማቸው፣ እንዲሁም ሰላማዊውን ሕዝብ ጭንቀት ውስጥ በከተተና ግልጽነት በጎደለው ሁኔታ የጅምላ እስሩን መነሻ ምክንያትና የታሳሪዎችን ዕጣ ፈንታ በፍጥነት ለሕዝብ ይፋ አለማድረጉ››፣ የፖሊስን ዕርምጃ ሕጋዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የእስሩን ገፈት የቀመሱ ግለሰቦች፣ ‹‹የተቀናቃኝ ፓርቲዎች አመራሮች ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የአቀባበል ዝግጅቱን ለምን #አስተባበራችሁ? ለምን የፓርቲዎች ደጋፊዎች ሆናችሁ? የሚሉና ተመሳሳይ የምርመራ ጥያቄዎች እንደቀረበላቸው›› ሰመጉ ከታሳሪዎች ባገኘው መረጃ መሠረት ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ታሳሪዎቹን በመደበኛ ፖሊስ ጣቢያዎች ለማቆየት ያልቻለበትን ምክንያት ግልጽ አላደረገም የሚለው ሰመጉ፣ ይህ የፖሊስ ድርጊት ‹‹የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በግልጽ የጣሰ በመሆኑ፣ ከሕግ አግባብ ውጪ የተያዙ፣ ክስ ሳይቀርብባቸው ወይም ሳፈረድባቸው የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱ፤›› በማለት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

አገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በነበረችበት ወቅት በተለያዩ ወታደራዊ ካምፖች ታስረው የነበሩ ዜጎች ይደርስባቸው የነበራት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ትውስታ ከአዕምሮ ባልጠፋበት በዚህ ወቅት፣ ለሥልጠና በሚል ሰበብ መንግሥት ዜጎችን ወደ ወታደራዊ ካምፕ በማጋዙ ለሌላ ዙር መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳያጋልጣቸው የሚል ሥጋቱንም ሰመጉ ገልጿል፡፡

‹‹በሁከትና በግርግር ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል በሕግ ሥር የሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸውን ተጠብቆ የመያዝ መብታቸው እንዲከበር፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በወዳጆቻቸውና በሕግ አማካሪዎቻቸው የመጎብኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው፣ እንዲሁም #ክስ ያልተመሠረተባቸው ዜጎች በፍጥነት እንዲለቀቁ፤›› ሲል ሰመጉ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update ጋምቤላ⬆️

በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረውን ሁከት #ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ የከተማዋ ወጣቶች ተናግረዋል። በከተማይቱ ህዝባዊ ሰልፍ ተደርጓል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በአንድ ግለሰብ #በተተኮስ ጥይት የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ በላሊበላ ከተማ ቀበሌ 01 ዛሬ ጠዋት በሁለት ሰዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ጉዳዩን #ለማረጋጋት በሞከሩ ሰዎች ላይ ግለሰቡ ጥይት ተኩሷል፤ ይላል የፖሊስ መረጃ፡፡
በተተኮሰው ጥይትም የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 6 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡

የቆሰሉት ሰዎች አሁን ሆስፒታል ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ አስተባበሪ ምክትል ኮማንደር መሠረት ላቀ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አስታውቀዋል፡፡ ምክትል ኮማንደሩ እንደገለጹልን ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሸዋሮቢት~መንገዶች ተከፍተዋል‼️

በሸዋሮቢት ከተማ የተከስቶ የነበረው #አለመረጋጋት በአሁኑ ሰዓት ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ #አካሉ_ወንድሙ ተናገሩ።

እንደ ከንቲባው ገለጻ በአሁኑ ሰዓት የተዘጉ መንገዶች #ተከፍተው የጸጥታ ሀያሉ እና የአካባቢው ማህበረሰብ መንገደኞችን #በመሸኘት ላይ መሆናቸውን ተናግረው የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ #መቻቻልና #መረዳዳት ባህሉና ወጉ የሆነው ህዝባችን ድርቶችን ሁሉ በተለመደውን የችግር መፍቻ መንገዶችን፣ ህግን በማክበርና በማስከበር ስራ ላይ #ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የጸጥታ ሀይሉ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሀገር ሽማግሌዎች ከተማውን #ለማረጋጋት ላያደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። በአሁኑ ሰዓት ሽዋሮቢት ወደነበረችበት #ሰላምና መረጋጋት እየተመለሰች መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።

Via Shewa Robit City Administration Kentiba office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዘመን መለወጫ በዓል ገበያን #ለማረጋጋት በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዛ የፍጆታ ምርት ለሸማቾች መቅረቡን በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለጸ። ሸማቾች በበኩላቸው የገበያ ማረጋጋት ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia