TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ላይቤሪያ‼️

ላይቤሪያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች #በነጻ እንዲማሩ ወሰነች...
.
.
የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ በሀገሪቱ በየትኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ከከፍያ ነጻ ሆነው እንዲማሩ አወጁ፡፡

የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ እና የአሁኑ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ላይቬርያውያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከክፍያ ነጻ ሆነው እንዲማሩ አውጇል፡፡

ፕሬዝዳንት ዊሃ ይህን አዋጅ ያሳወቁት ሰሞኑን በላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉበት ጉብኝት ነው፡፡ ማንኛውም የሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከዚህ በኋላ ወጪው በሀገሪቱ እንዲሸፈን ለተሰበሰበው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያደረጉትም የተማሪዎች ወጪ በመንግስት በኩል መሸፈን አለበት በማለት ለአፍሪካም ፈር ቀዳጅ መሪነታቸውን አሳይተዋል ነው የተባለው፡፡

ላይቤሪያውያን ተማሪዎች ለአንድ ክሬዲት 4 የአሜሪካን ዶላር ክፍያ ይጠየቁ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የክፍያው መጨመርም በተማሪዎች ዘንድ ተቃውሞን አስከትሏል፡፡ፕሬዝዳንቱ ባልተጠበቀ መልኩ ማወጃቸው በሀገሪቱ ተማሪዎች አግራሞትን ፈጥሯል፡፡
ላይቬሪያ 9 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አሏት።

ጆርጅ ዊሃ 23ኛ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ባለፈው ዓመት መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-አፍሪካን ስታንድ(አብመድ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል፤ ዕዳ ላለባቸውም ዕዳ ሰርዟል፡፡ ለኢትዮጰያ ዐይን ባንክ ደሞ 250 ሺህ ብር መለገሱን የገለጸ ሲሆን የሚደሮክ ፕሮጄክቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶችም እንዲሁ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ የሚድሮክ ንብረት በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎችም ላንድ ወሰነ ትምህርት #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡

Via wazemaradio(walta)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ‼️

ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ፦ የሚድሮክ ንብረት በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ላንድ ወሰነ ትምህርት(1 ሴሚስተር) #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 20/2011 ዓ.ም.

የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ፍራንክ_ዋልተር_ሽቴይንሜይር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
.
.
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ አቶ #ዳዊት_ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።
.
.
ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #የደም_ስር_መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የፒሲአይ የነጻ ህክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ካሉት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
ለኢፌድሪ ፕረዝዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) የEuropean Tourism Academy Membership ሽልማት ሊሠጥ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 4 ሚሊየን 234 ሺህ 856 መቶ ተሸከርካሪዎች በማስተናገድ በአጠቃላይ ብር 124 ሚሊየን 578 ሺህ 594 መቶ ብር መሰብሰብ መቻሉ ተሰምቷል።
.
.
#አለን_ኢትዮጵያ የበጎ-አድራጎት ድርጀት የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል ህጋዊ እውቅና በማግኘት ትላንት በ19/05/01 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ሥራ ጀምሯል።
.
.
በአንድ ፒካፕ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዙ የነበረ ሦስት መትረየስ፣ 1924 የስታር እና 1856 የማካሮቭ ሽጉጥ ጥይቶች ከ37 የጥይት መያዥ ጋር #መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ቮልስዋገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
የሚድሮክ ግሩፕ የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንን ከእስር #መፈታትን ምክንያት በማድረግ ሠራተኞቹን #አንበሻብሿል
.
.
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሙስና ተጠርጣሪው የጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም #ኢሳያስ_ዳኘው ፈቅዶት የነበረውን የዋስትና መብት ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሻረው ካፒታል ዘግቧል፡፡
.
.
ጠ/ሚር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ምሽት #በብሄራዊ_ቴአትር በየሶስት ወሩ የሚካሄደውን የኪነ ጥበብና የባህል ምሽት ተካፍለዋል።
.
.
ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ፦ የሚድሮክ ንብረት በሆነው #ዩኒቲ_ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ላንድ ወሰነ ትምህርት(1 ሴሚስተር) #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡
.
.
ምንጭ፦ ዋልታ፣ ፋና፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ሬድዮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እድሜዋ ትንሽ ሀሳቧ ትልቅ---ሰላም⬆️

ሀዋሳ ከተማ ኦሲስ ሆቴል አጥገብ ፌደራል አጥሩ ስር ቡና የምታፈላና ጎን ለጎን መጽሀፎችን ለሚያነቡ #በነጻ እንዲጠቀሙ መልካም የንባብ ባህልን አስተዎጽኦ የምታደርግ ሰላም የምትባል ልጅ አለች። በዚህ ብቻ አላበቃችም ለጎዳና ልጆች እዛው አካባቢ ዘንቢልና የተለያዩ ማጌጭዎችን በመያዝ በቀላሉ እንዲሰሩ እያደረገች ትገኛለች።

አሁንም ቡናዎን እየሸጠች ባዶ ካርቶን አስቀምጣ (1ደብተር፣ 1 እስክሪብቶ፣ 1 እርሳስ፣ ለእኛ ብዙ ነው) የሚል ጽፋ ካርቶን ላይ በ4 አቅጣጫ ለጠፈችበት ሰው አልተጠራጠራትም ካርቶን ላይ የቡና መልስ ወይም ከኪስ በማውጣትና፣ ማቴሪያሉን ገዝተው በማምጣት፣ ትላንት ለፍሬ በቅቶ ብዙ ልጆችና እናቶቻቸው ጭምር በመገኘት ተረክበዎል። ለ1 ሰው ከ6 ያላነሰ እስክርቢቶና እርሳስና ደብተር ተከፉፋሏል።

ለታሰበው አላማ ከጎኗ የነበሩ ልጆችም ቲሸርት አሳትመው ለብሰው ደብተሮቹን በመቁጠርና በማስተካከል ተወጥረው ነበር። ብራቮ ሰላም ቡና በሏት "ግን ትንሽ ልጅ ነች ሀሳቧ ትልቅ ነው" ምስጋና ይገባታል።

Yared Tassew/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ትራንስፖርት ልማት ጽ/ቤት ፤ በትራንስፖርት ዘርፍ እየተፈጠረ ያለውን ጫና ለመቅረፍ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።

ጽ/ቤቱ በመንግስት ሠራተኛው ላይ የተፈጠረውን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል ሠራተኛው ለጊዜው #በነጻ_የትራንስፖረት_አገልግሎት እንዲጠቀም ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል።

የከተማ አውቶብስ አገልግሎት መጀመር በከተማ ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሚፈጥረው ጫና የለም ተብሏል።

የከተማ አውቶብስ አገልግሎት እንዲጀመር ትራንስፖረት ጽህፈት ቤት ያቀረበውን ዕቅድ የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ ኮሚቴ እና ገንዘብ መምሪያው ተቀብለው ወደ ስራ እንዲገባ መፍቀዳቸው መገለፁን ከከተማው ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#Scotland

ስኮትላንድ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በነጻ የማግኘት መብትን የሚያስከብር ሕግን ማፅደቋን ቢቢሲ አስነብቧል።

ወዲያው ተግባራዊ እንዲሆን የተደረገው ሕግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በነጻ የማግኘት መብትን ለመጠበቅ አዲስ ሕግ ያወጣች የዓለማችን የመጀመሪያዋ አገር በመሆን እንድትመዘገብ አድርጓታል።

በዚህ ሕግም ሕዝብ የሚገለገልባቸው ህንጻዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ሌሎች ተቋማት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን #በነጻ_ለማቅረብ ይገደዳሉ።

የየአካባቢው ባለሥልጣናት ማንኛውም ምርቶችን የሚፈልግ ሰው በነጻ እንዲያገኝ የማመቻቸት ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩ የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን #በነጻ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጾ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም እንዳሉት ጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና መስፈርቱን አሟልተው ለሚመረጡ የተመረጡ ተማሪዎች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን እንደሚሸፍን ገልጿል።

ተጨማሪ ይመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethmagazine/18949

@tikvahethiopia
#ቭላድሚር_ፑቲን

የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አገራቸው ሩስያ ከአፍሪካ ጋር ላላት ግንኙነት ቅድሚያ እንደምትሰጥ ተናገሩ።

ይህን ያሉት ትናንት ሰኞ ሞስኮ ውስጥ መካሄድ በጀመረውና ከ40 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን እየተካፈሉበት እንዳሆነ በተነገረው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ነው።

ፕሬዜዳንት ፑቲን ምን አሉ ?

" አገራችን ከአፍሪካ አገራት ጋር ለመተባበር ቅድሚያ እንደምትሰጥ እና በዚህም እንደምትቀጥል አጽንኦት መስጠት እፈልጋለሁ።

ከዩክሬን በሚቀርበው እህል ላይ የተደረሰው ስምምነት ካልታደሰ ሩሲያ ለተቸገሩ የአፍሪካ አገራት #በነጻ እህል ታቀርባለች።

በባለፉት ዓመታት ሲላክ የነበረውን የእህል መጠን ለአፍሪካ አገራት በተለይም ከሩሲያ ለሚፈልጉ በነጻ ለማቅረብ ዝግጁ ነን።

ሩሲያ የደረሰችባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለአፍሪካ አገራት ታካፍላለች ፤ የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያመርቱ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች።

አፍሪካ እያቆጠቆጠ ባለው የብዝኃ የዓለም ስርዓት ላይ ስልጣኗን እና ሚናዋን ማሳደግ እንደምትቀጥል አምናለሁ። "

#BBC

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ሁለት ዙር ብቻ በቀረው የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና ይሳተፉ።

ስቴም ፓወር (STEMpower) ከቪዛ (Visa) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና ላለፉት ሁለት ዓመት ከሶስት ወር ሲካሄድ ቆይቷል።

በእነዚህም ጊዜያት ሰባት ዙር ስልጠናዎች ተካሂደው ወደ 2100 የስራ ፈጠራ ፍላጎት ያላቸው እና በተለያየ የስራ ዘርፍ  ሰልጣኞች የሰለጠኑ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ከ45 በላይ የሚሆኑት ስራ ፈጣሪ Startups እንዲመሰረቱ እና እንዲጠነክሩ እገዛ ተደርጎላቸዋል።

አሁን የ9ተኛ ዙር ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን፣ እርሶም ከታች የተያያዘውን ማስፈንጠርያ በመጫን ይመዝገቡ።

ስልጠናው #በነጻ የሚሰጥ ሲሆን በዚህኛው ዙር ለ 200 ሰልጣኞች ስልጠናው ይሰጣል።

መመዝገቢያ ሊንክ፡ https://forms.office.com/r/BniiDzNp64

@tikvahethiopia
#ጥምረት . . የፊልም ፌስቲቫል . . ለሁሉም

ዩኤስኤይድ ከፕሮሎግ ማርኬቲንግ ጋር በመተባበር  ጥምረት የተሰኘ የፊልም ፌስቲቫል ከሐምሌ 25 እስከ 28 ድረስ ለዕይታ ያቀርባል።

📽 በአዲስ አበባ፦  የጣሊያን ባህል ማዕከል፣
📽 በአዳማ፦ ኦሊያድ ሲኒማ
📽 በባህር ዳር፦ ሙሏዓለም አዳራሽ ያካሂዳል።

ይኽ የፊልም ፌስቲቫል ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን የሚያንሸራሽሩበት መድረክ ጭምር በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።

📣 መግቢያው #በነጻ ነው።

ቀድመው ይመዝገቡ ፦  https://forms.gle/wjNi3Dk5ssNpsZ9s7

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉  https://t.iss.one/TimretEth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በጥምረት የፊልም ፌስቲቫል ምን ይቀርባል?

ከሐምሌ 25 እስከ 28 ድረስ የተዘጋጀው #ጥምረት የፊልም ፌስቲቫል በሀገራችን የሚገኙ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ለማሳየት የተዘጋጀ ነው። በፌስቲቫሉ ላይ፥ ዘጋቢ ፊልሞች ይታያሉ፤ የፓናል ውይይቶችም ይካሄዳሉ።

በዚህ ዝግጅት ለሚሳትፉ #ሰርተፊኬት ይሰጣል። የሚመቾትን ቀን መርጠው በፊልም ፌስቲቫሉ ይሳተፉ፤ ሀሳቦትንም ያካፍሉ!

📽 በአዲስ አበባ ለምትገኙ በጣሊያን ባህል ማዕከል፤
📽 በአዳማ ለምትገኙ በኦሊያድ ሲኒማ፤
📽 በባህር ዳር ለምትገኙ ሙሉዓለም አዳራሽ በሮች ከ10 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ።

📣 መግቢያው #በነጻ ነው።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉  https://t.iss.one/TimretEth

ቀድመው ይመዝገቡ ፦  https://forms.gle/wjNi3Dk5ssNpsZ9s7
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጥምረት የፊልም ፌስቲቫል በአዳማ እና በአዲስ አበባ በሚኖሩን መርኃግብሮች ፍጻሜውን ያገኛል።

ዛሬ በመጨረሻው ቀን፦

#በአዲስአበባ "ለዘር ጥያቄ ግሩም ምላሽ የሰጠኝ አርሶ አደር" እና "ሙስሊምና ክርስትያን ድንቅ ተዓምር ሰሩ" የተሰኙ ዶክመንተሪዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።
📍በጣሊያን ባህል ማዕከል 🕒 ከ 11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ መታየት ይጀምራሉ።

#በአዳማ "Zeyse" የተሰኘው ዶክመንተሪ ይቀርባል።
📍በኦሊያድ ሲኒማ 🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ መታየት ይጀምራል።

በፊልም ፌስቲቫሉ ለሚገኙ ተሳታፊዎች በሰርተፊኬት አዘጋጅተናል።

📣 መግቢያው #በነጻ ነው።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉  https://t.iss.one/TimretEth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

" የ2024 ESP ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል " - የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የEducation USA Scholars Program (#ESP) 2024 ማመልከቻ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ESP በአካዳሚክ ጠንካራ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ አሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች #እንዲያመለክቱ የሚረዳ የአራት ሳምንታት የሥልጠና መርሃ ግብር ነው።

ዓላማውም ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሰለጠኑ እና ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን መሪዎችን ማፍራት እንደሆነ ኤምባሲው አመልክቷል።

ከአመልካቾች 20 ከፍተኛ የአካዳሚክ ብቃት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በኤምባሲው ይለያሉ። ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ሪከርዳቸው፣ እንዲሁም በኢንተርቪው እንዲለዩ ይደረጋል።

ከጠቅላላው 20 የመጨረሻ እጩዎች መካከል፣ 15 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው፣ በኢኮኖሚ የተቸገሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ፈተናዎች፣ ከአሜሪካ ቪዛ ክፍያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በሚሸፍነው የOpportunity Program Fund (#OPF) ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመረጣሉ።

የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ስኬታማ ዕጩዎች ወደ አሜሪካ የራውንድ ትሪፕ ትኬት ያገኛሉ።

ቀሪዎቹ 5 ተማሪዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ #በነጻ ይሳተፋሉ ነገር ግን የዝግጅት ወጪን ከራሳቸው ምንጭ ይሸፍናሉ። የሞባይል ዳታ ወጪዎች ለሁለቱም የፕሮግራም ተሳታፊዎች በኤምባሲው ይሸፈናሉ።

ማመልከቻ እስከ ሚያዚያ 10/2024 (5:00 pm EAT) ማስገባት ይችላል ተብሏል።

ለማመልከት አስፈላጊ መስፈርቶች ምንድናቸው ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ትምህርታቸውንም እዚሁ ኢትዮጵያ እየተከታተሉ ያሉ።

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ/ች #ኢትዮጵያዊ ተማሪ፣

በዚህ የትምህርት አመት መጨረሻ 11ኛ ክፍልን ያጠናቅቁ እና ከመስከረም 2024 ጀምሮ 12ኛ ክፍል የሚማሩ፣

በጠቅላላ 4 ሳምንታት የESP መርሃግብር ለመሳተፍ ቃል መግባት የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ስታመለክቱ የሚያስፈልጉ ፦
1ኛ. የሁለተኛ ደረጃ ትራንስክሪፕት (9፣ 10፣ 11)
2ኛ. ከትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3ኛ. የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ለOpportunity Fund Program (OFP) የሚያመለክቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከቀበሌ የቤተሰብን #ዝቅተኛ የኢኮኖሚያ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።

የማመልከቻ ሊንክ እና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://sites.google.com/amspaceseth.net/educationusa-esp2024

@tikvahethiopia
ነጻ ትምህርት ☑️

#LG_KOICA_Hope

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቲቪቲ መግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በICT እና Electronics የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን #በነጻ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የተዘጋጀ ሲሆን የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም አካቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና መስፈርቱን ለሚያማሉ የተመረጡ ተማሪዎች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን የሚሸፍን ይሆናል።

የማመልከቻ ጊዜና ቦታ : ከጥቅምት 11 - ህዳር 06 2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 - 11፡00 ሰዓት ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር

ለተጨማሪ መረጃ - 011-6-67-75-64 011-6-66-18-29