TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ መንግሥት ከተወሰኑ የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች አመራሮች ጋር ድርድር ጀምሯል። ግንኙነቱ የተጀመረው በኢትዮጵያ መንግሥት አደራዳሪነት ነው።

Via #Eshet_Bekele
🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ግብፅ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር #ገዱ_አንዳርጋቸው ወደ ግብፅ አቅንተው ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ተገናኝተዋል። ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ፕሬዝዳንቱን ሲያገኙ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና የጠቅላይ ምኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ ግርማ ብሩ አብረዋቸው ነበሩ።

Via #Eshet_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደኢ01

ደኢሕዴን ለሰባት ወራት በልሒቃን ያሰራው የተባለ ጥናት የመጀመሪያ ክፍል በ-ዘፊንፊኔ ኢንተርሰፕት በኩል ይፋ ሆኗል። ይፋ የሆነው የሰነዱ ክፍል 59 ገፆች ያሉት ሲሆን የደቡብን ፖለቲካ ለሚከታተሉ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ጠቃሚ መረጃዎች ይገኙበታል። የደቡብ ክልል እና የዛሬው ደኢሕዴን እንዴት ተፈጠሩ የሚለው ታሪካዊ ዳራ በመግቢያው ላይ ይገኛል።

በመግቢያው የጥናቱ አከናዋኞች «የአደረጃጀት ጥያቄዎች ለምን እንደተበራከቱ፤ ከዚህ በፊት በተሰጡ መልሶች የአደረጃጀት ጥያቄዎች መልስ ለምን ዘላቂ መሆን እንዳልቻለ፤ ከሀገራት ተሞክሮ አንጻር ዘላቂ የሆነ አደረጃጀት እንዴት እንደሚፈጠር፤ ከአደረጃጀት መስፋት ወይም መጥበብ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ፤ አደረጃጀት ኅብረ-ብሔራዊ ብዝኃነት ባላቸው ሀገሮች እንዴት እንደተተገበረ ወዘተ በማሰስ ለውሳኔ ሰጪው አካል ምክረ-ሀሳብ እናቀርባለን» ሲሉ ቃል ይገባሉ። ይሁንና በፌስቡክ በኩል በተሰራጨው ሰነድ ባለሙያዎቹ የደረሱበትን ድምዳሜ የያዘው ክፍል አይገኝም።

ባለሙያዎቹ የደቡብ አፍሪካን፣ የኬንያን፣ የናይጄሪያን እና ያደጉ አገራትን የፌድራላዊ መንግሥት አወቃቀር ለመፈተሽ መሞከራቸውን የሚያሳይ ክፍል አለው። በሰነዱ መሠረት በቃለ-መጠይቅ፤ በቡድን ውይይት እና ሰነዶችን በመፈተሽ ጥናቱ ተከናውኗል። ጥናቱ ከክልሉ 21 ሚሊዮን ነዋሪዎች በሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ያዳረሰ መሆኑን ቢጠቁምም ከጥቂት ቀናት በፊት ባለሙያዎቹ ካሉት ይጋጫል። ባለሙያዎቹ የሲዳማ ዞን እና የሐዋሳ ከተማ አለመካተታቸውን ገልጸው ነበር።

(PS፦የሰነዱ ትክክለኛነት አሊያም በጊዜ ሒደት የተቀየረ ነገር ይኑረው አይኑረው የተረጋገጠ አይደለም፤ በፌስቡክ በኩል ሲሰራጭ የክልሉ መንግሥት እና የደኢሕዴን ይሁንታን ስለማግኘቱም የታወቀ ነገር የለም)

Via #ESHET_BEKELE
#ሶዴፓ

የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ «ከአጋርነት ወደ ሀገራዊ ፓርቲ የሚያሸጋግረውን» የኢሕአዴግ ጥናት ገምገሞ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል። የማዕከላዊ፣ የክትትልና ኦዲት ኮሚቴዎችና አባላቱ ውይይት አድርገው የሚጨመርና የሚቀነስ ይለያሉ ብሏል።

Via #Eshet_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia