TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ⬇️

በሀዋሳ ከተማ ስጋት ለመፍጠር ሙከራዎች እየተደረጉ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ አከባቢውን #በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በከተማዋ ከሰሞኑ የተፈጠረውን የፀጥታ ስጋት ችግር ለመቅረፍ የከተው የፀጥታ አካላት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ፖሊስ አክሎ ገልጿል።

የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ በሰጡት መግለጫ፥ በሀዋሳ ከተማ ማንነታቸውና አላማቸው ያልታወቁ አካላት የከተማውን ነዋሪ ላይ #ስጋት ለመፍጠር ያልተጨበጠ የስነ-ልቦና ጦርነት ከፍተዋል ብለዋል።

ባለፉት 3 ቀናትም ምሽትን ተገን በማድረግ የተለያዩ ቀለማትን በግለሰቦች በር እና አጥሮች ላይ በመቀባት ነዋሪው ላይ ጥርጣሬን መፍጠሩን ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ ተናግረዋል።

ተግባሩም ለውጡን በማደናቀፍ የህዝቦችን በአንድነት የመኖር እሴት ለማፍረስ ሆነ ተብሎ የተደረገ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አረጋግጧል ብለዋል።

ቀለም የሚቀቡትን አካላት ፖሊስ #በቁጥጥር ስር ለማዋል ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ ምንም የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር ግን የጸጥታው መዋቅር አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገ እንዳለም ነው የገለጹት።

የተቀቡት ቀለሞች ግን ሁሉም ቤቶች ላይ በመደረጉ #ብሄር ተኮር ባለመሆናቸው ህብረተሰቡ በዚህ ሆነ ተብሎ የከተማውን ሰላም ለማወክና በቀጣይ የሚካሄደውን የደኢህዴን ጉባኤ ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረትን ሊያወግዝና ሊያጋልጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀገር ስጋት⬇️

ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በአገር ደረጃ #ስጋት ሆኗል ተባለ፡፡ ከተለያዩ አገራት በድንበር በኩል የሚገባውን ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አስመልክቶ ጠንከር ያለ ሕጋዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በከተማዋ በስፋት እየተስተዋለ ያለውን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመግታት ጠንካራ የቁጥጥር ህግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

412 ሽጉጦችን፣ ከ12 ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶችንና ከ9 ሺ በላይ የክላሽ ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 5 ተጠርጣሪዎችን ፍ/ቤት በዋስ መልቀቁ ጥብቅ የሆነ አሰራር ላለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡

ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በተጨማሪ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋና ቤት ሰብሮ ስርቆት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ እየተበራከተ መጥቷል ብለዋል፡፡

እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጥናት የተደገፈ የክትትልና የምርመራ ቡድን ማዋቀሩን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ህብረተሰቡን ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚጥሉና የአገርን ኢኮኖሚ የሚጎዱ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ነዋሪውም የከተማውን ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ለፀጥታ አካላት #ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ‼️

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኢፌዲሪ ህገመንግስት መሰረት በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ፤ የዜጎች #ሰላምና ደህንነት #እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2011ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት #በሰለማዊ መንገድ እንዲቀጥል ከወትሮ በተለየ በሁሉም ሀገሪቱ #ዩንቨርሲቲዎች እና #ኮሌጆች በተለያዩ አከባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያካናወነ ሲሆን የመማርና ማስተማር ሂደትም እንዳይስተጓጎል ከሌሎች ጥምር ኮሚቴዎች ጋር ተቀናጅቶ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ እየሰራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተመደባችሁ አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋም በመሄድ #ያለምንም የፀጥታ #ስጋት ትምህርታችሁን መማር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ደህንነታችሁ በተመለከተ በሁሉም ዩንቨርሲቲዎችና አካባቢዎች ከወትሮ በተለየ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያደረግን እንደምንገኝ በድጋሜ እናሳውቃለን፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ቦታ ሲሆዱም ሆነ ግቢ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ስጋት እንዳይኖር አስቀድመን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት በማድረግ እየሰራን እንደምንገኝና ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦቻቸው እንገልፃለን፡፡

©የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ‼️

ማሳሰቢያ፦

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ቅበላ ከጥቅምት 10 እስከ 14/2011 ዓ.ም ድረስ ማካሄዱ ይታወሳል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የምዝገባ ስርዓቱን አጠናቆ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የገባ ሲሆን ለሠላማዊ የመማር ማስተማር መስፈን ከውጫዊና ውስጣዊ ባለድረሻ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡

ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ ምንም አይነት የፀጥታ እና የደህንነት ስጋት ሳይኖር ተማሪዎችን ሆን ብሎ ለማወክና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ #ረብሻ እንደተከሰተ ተደርጎ በማህበራዊ ድረ ገፅ #እየተወራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ይህ መሰረተ ቢስ #ወሬ እንደ ሆነ ታውቆ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች አንዳች #ስጋት እንዳይገባቸሁ ተቋሙ #ያሳስባል፡፡

መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ሳይስተጓጎል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባለድርሻ አካላት የተለመደ ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል፡፡

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 23/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የመከላከያ ሰራዊቱን #ማገት የሚለው አስቸጋሪ ነው፡፡ #መከላከያን ማንም ሊያግተው አይችልም፡፡ አማርኛው ቢቀየር ጥሩ ነው። ሰራዊቱን #የትግራይ_ህዝብ አያገትም፡፡ ነገር ግን #ስጋት እየፈጠረ መኖር የለመደ አካል አለ፡፡ በጣም ጥቂት ነው፡፡ ህዝቡን ሽፋን አድርጎ ትርምስ ለመፍጠር የሚሞክር ኃይል አለ፡፡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ እርግጠኛ ነኝ #ይጋለጣሉ፡፡ የትግራይ ህዝብም #ቢዘገይም ይገባዋል፡፡ እንዲጋለጡና ህዝቡም እንዲያውቃቸው እናደርጋለን፡፡ ይህ እስኪሆን ግን ከህዝቡ ጋር #የሚያጣላ ነገር አናደርግም፡፡ ህዝብ ቅር ከሚለው እኛ ቅር ቢለን ይሻለናል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ነገር ከክልሉ እውቅና ውጭ ነው፡፡ ክልሉ ወስኖ የተደረገ ነገር አይደለም፡፡ የክልሉ ፍላጎትም አይደለም፡፡"-የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተናገሩት፤

@tsegabwolde @tikvqhethiopia
ኦሮሚያ ክልል‼️

በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ዶክተር #ቢቂላ_ሁሪሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ ያላቸውን #አቅም#እውቀት እና #ስነ_ምግባርን መሰረት አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአዲስ መልክ በተዋቀሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥም ሁሉም ሰራተኞች በሚመጥናቸው ስራ ዘርፍ ላይ ተወዳድረው እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑንም ሀላፊው ገልፀዋል።

ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በመግለጫቸው፥ በፖለቲካው መስክ የመጣው ለውጥ ብቻ በሁሉም ደረጃ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ ስለማይችል የህዝቡ ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የመንግስትን አደረጃጃት ከመሰረቱ ማስተካከል ለአንድ ዓመት በተደረገ ጥናት የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንደ አዲስ እንዲደራጁ መደረጉን አንስተዋል።

አዲሱ አደረጃጀትም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ #መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እቅድ ተይዞበት እየተሰራ ነው ብለዋል ሀላፊው።

በዚህም የመንግስት እና የህዝብን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም እንደ አዲስ በተደራጁ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ አቅምን፣ እውቀትን ፣ ችሎታን እና ስነ ምግባርን መሰረት በማድረግ እንዲሁም ግልጽ እና ተአማኒ በሆነ መልኩ የሰራተኞች ምደባ እየተካሄደ መሆኑንም ዶክተር ቢቂላ አስታውቀዋል።

እየተካሄደ ባለው የሰራተኞች ምደባ ማንኛውም ሰራተኛ ከመንግስት ስራ ውጭ #እንደማይሆን የገለጹት ሀላፊው፥ ሰራተኞች በአግባቡ እንዲሰሩና እና ውጤታማ በሚያደርጋቸው የስራ መስክ ላይ እንደሚመደቡን ገልፀዋል።

“ማንኛውም ሰራተኛ ከስራ ውጭ ልሆን እችላለሁ የሚል #ስጋት_ሊገባው_አይገባም” ያሉት ዶክተር ቢቂላ፥ ምደባው እስኪጠናቀቅ ድረስም ባሉበት ሆነው በትእግስት እንዲጠባበቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ እስከ ጥር 30 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ገልፀዋል።

በአዲሱ ምደባ መሰረት የሚመደቡ የመንግስት ሰራተኞችም በአዲስ መንፈስ ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ቦታ ላይ አቅጣጫና ስልጠና ከተሰጠ በኋላ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ‼️

ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል። ከሪፈራል አደባባይ ጠዋት አንድ ሰዓት የሚጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ መዳረሻው ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ነው፡፡

ሰልፉ ወደ ብሉናይል የሚያወጣውን አስፓልት ይዞ ተስፋዬ ግዛው ህንጻ አደባባይ ሲደርስ ወደ ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚገባና ማጠቃለያውን እንደሚያደርግ ተናግሯል። በዚህ ምክንያት መንገዶቹ ለተሸከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ እንዲሁም በበቂ የፀጥታ ሃይል ጥበቃ ይደረጋል፡፡ የከተማው ነዋሪ በሰልፉ ምክንያት #ስጋት ውስጥ እንዳይገባ በየክፍለ ከተማው #ውይይት መደረጉ ተገልጿል፤ ህዝቡም ለሰልፉ ሰላማዊነት #የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡

በተጨማሪ፦

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ #ሀሰተኛ_መረጃዎች ራሱን እንዲያርቅ ጥሪ ቀርቧል። ነዋሪው ምንም አይነት ሰላም የማደፍረስ እንቅስቃሴ ካየ ለፀጥታ ሀይሉ #ጥቆማ እንዲያደርስ ጥሪ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከባቲ- ከሚሴ በአንድ ግለሰብ ሲዘዋወር የነበረ 880 የክላሽ ጥይት ኮምቦልቻ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ያለለት ዘገዬ ለአብመድ እንደተናሩት ዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ረፋድ ላይ 880 የክላሽ ጥይቶችንና 400 ሺህ ብር የያዘ የባንክ ደብተር ይዞ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ መናኸሪያ ባሉ ተራ አስከባሪዎች እና የትራንስፖርት ባለሙያዎች ተይዞ ለፖሊስ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡

አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ደግሞ ግለሰቡ 8 ሺ 150 ብር በካሽ፣ የሞባይል ካርድና ፓስፖርት ይዞ መገኘቱን ተናግረዋል::

በአካባቢው ሰላም የሚያውኩ ድርጊቶች እንዳይፈጠሩ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ፀረ ሽምቅ፣ ሚሊሻ እና የአካባቢው ፖሊስ ተሰማርቶ እየጠበቀ እንደሆነም ኮማንደር ያለለት ተናግረዋል፡፡ ወደ አካባቢው የሀገር መካለከያ ሠራዊት እንደገባም ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

አካባቢው #ትልልቅ ድርጅቶች የሚገኙበት በመሆኑም ጥቃት እንዳይደርስባቸው ከወጣቱ እና ከአካባቢው ማኅረሰብ ጋር በመተባበር ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሆነ ነግረውናል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ኮማንደሩ አስታውቀዋል፤ ኮምቦልቻ እና አካባቢዋ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር ባይኖርም #ስጋት ለመቅረፍ #መከላከያ በአካባቢው መኖሩን ኮማንደሩ አመልክተዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሀዋሳ ከተማ አሁን ያለምንም #ስጋት የሚሰሩባትና የሚንቀሳቀሱባት ከተማ ሆናለች። ቱሪስቶችም ሆኑ ለተለያዩ ስራዎች ወደ ከተማዋ መምጣት የሚፈልጉ ሁሉ ያለምንም ስጋት ወደ ከተማዋ መምጣት ይችላሉ። በተለይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚመጡ አካላትን ከተማ አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ለማገልገል ዝግጁ ነው።›› የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጥራቱ በየነ #HAWASSA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። መግለጫውን የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ ሲሆኑ ታንዛኒያ ውስጥ እየተካሄደ ነው ስለተባለው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ተጠይቀው ቀጥተኛ ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል። አቶ ኃይሉ ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም በክልሉ ዘላቂ ለሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ፅኑ…
" ድርድሮች መፍትሔ ይዘው የሚመጡት ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽነት የተላበሱና በአግባቡ የሚመሩ ሲሆኑ ብቻ ነው " - የ5 ፓርቲዎች የጋራ መግለጫ

መኢአድ ፣ ኢህአፓ ፣ የዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲና እናት ፓርቲ ዛሬ ከጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ፓርቲዎቹ ምን አሉ ?

- ማንኛውም የሚደረጉ ድርድሮችና ዉይይቶችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ ሊያውቃቸው ይገባል።

- ግልጽ ያልሆኑና ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ ድርድሮችና ስምምነቶች ከመድረኩ እንደተወጣ ጥያቄ የሚያስነሱ መሆናቸዉ እንዳለ ሆኖ ዉለዉ አድረዉ ወደ ከፋ ጥፋት አገርንና ሕዝብን እንደሚወስዱ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን የምንረዳዉ ጉዳይ ነዉ፡፡

ለምሳሌ ፦

* " ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ከአምስት ዓመታት በፊት አስመራ ላይ ተደረገ " የተባለዉና የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልፅ ምንነቱን ያላወቀዉ ኋላም " የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት " ብሎ ራሱን ለሚጠራዉ ታጣቂ ኃይል መፈጠር ምክንያት እንደሆነ የሚነገረዉ ድብቅ ስምምነት አንዱ ነው።

* ፕሪቶሪያ ላይ የተደረገዉና እርሱን ተከትሎ ናይሮቢ ላይ በፌደራል መንግሥት እና በሕወሃት መካከል የተደረጉ የተሸፋፈኑ ድርድሮችና ተደረሰባቸዉ የተባሉ ስምምነቶች ዛሬም ድረስ ጥያቄ የሚያስነሱና ወደፊትም ጥያቄ በማስነሳት የሚቀጥሉ ናቸዉ።

- ለፖለቲካዊ ጥያቄ ፖለቲካዊ መፍትሄ ብቻ ሊሰጥ ይገባል። ለዚህም ግልፅነት የተላበሰ ድርድር ብቸኛ አማራጭ ነው።

- ከጥቂት ቀናት ወዲህ በመንግሥትና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ድርድር እየተደረገ ነዉ " በተባለዉና የፌዴራል መንግሥት ድርድሩ ስለመታሰቡም ሆነ ስለመጀመሩ እንዲሁም የድርድሩ ተሳታፊዎችን ማንነት ባልገለፀበት ሁኔታ ላይ መረጃዎች መደመጣቸው የተደበላለቀ ስሜትና ከፍተኛ #ስጋት_አንዲሰማን አድርጓል፡፡

- አብዛኛዉ የኦሮሚያ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ በተሰነዘሩ የተለያዩ ዘግናኝ ጥቃቶች በግንባር ቀደምነት የአማራ ማኅበረሰብ ለአሰቃቂ ጅምላ ጭፍጨፋ መዳረጉ የማይታበል ሐቅ ሲሆን፤ ቀን በብልጽግና ማታ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቀንበር ሥር ወድቆ የመከራ ህይወት እየገፋ ለሚገኘዉ የኦሮሞ ማኅበረሰብም ከመከራዉ ቀንበር የሚገላገልበት የተስፋ ጭላንጭል የሚፈጥር በመሆኑ የፖለቲካ ልዩነቶች በድርድር እንዲፈቱ ዛሬም ጽኑ ፍላጎታችን ነው።

- ድርድሩ እየተካሄደበት ያለዉ መንገድ የተሸፋፈነ መሆን፣ ለድረድሩ ምክንያት የሆኑ አጀንዳዎች ይፋ አለመደረጋቸው እና ከአገራችን ሕዝብ ጀርባ እየተከናወነ የሚገኝ ድርድር መሆኑ፣ ሠላም የራቀዉ ህዝባችንን ተስፋ መልሶ የሚያጨልም የጎራ ድርድር እንዳይሆን ያለንን ስጋት እንገልጻለን።

- የአገራችን ጉዳይ በመጠነ ሰፊ ችግሮች የተሞላ ሆኖ ሳለና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ባሻገር ድርድሩ ሁሉን አቀፍ መሆን ሲገባዉ የተድበሰበሰና ቁንጽል መሆኑ ያሳስበናል።

(ከፓርቲዎቹ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

NB. ምንም እንኳን መንግሥትም ይሁን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ለሰላም ድርድር መቀመጣቸውን እስካሁን በይፋ ባያሳውቁም / ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ባይሰጡም ፤ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የዲፕሎማቲክ ሰዎች ግን የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን አሳውቀዋል። ድርድሩ እየተመራ ያለውም በጦር አዛዦች ነው።

@tikvahethiopia