#Ukraine #Russia
የሩስያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ ሁለት የዩክሬን ጦር ሂሊኮፕተሮች የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ተሰማ።
ሁለት የዩክሬን ሄሊኮፕተሮች የሩሲያን ድንበር ጥሰው በሀገሪቱ ምዕራባዊ ከተማ ቤልጎሮድ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአከባቢው አስተዳዳር ዛሬ አስታውቋል።
የአካባቢው አስተዳዳሪ የሆኑት ቫያቼስላቭ ግላድኮቭ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ ሁለት የዩክሬን ጦር ሄሊኮፕተሮች በፈፀሙት የአየር ጥቃት በሚያስተዳድሩት አካባቢ ባለ የነዳጅ ማከማቻ ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ጽፈዋል።
በቃጠሎው ምክንያት በነዳጅ ማከማቻው ውስጥ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች መቁሰላቸው ተገልጿል።
የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አብስቶ ሩስያ ፤ ዩክሬን ድንበሯን አልፋ ጥቃት ፈፀመችብኝ ብላ ሪፖርት ስታደርግ ይህ የመጀመሪያ ነው።
የ2ቱ ሀገራት ጦርነት እስካሁን ድረስ ይህን ነው የሚባል መፍትሄ ሳይገኝለት ከወር በላይ ተቆጥሯል።
አሁንም ጦርነቱ እንዲቆም ለማድረግ ንግግሮች ቢኖሩም ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ግጭት እንዲቀጥል የሚያደርጉ ወታደራዊ ሁኔታዎች እንደሚስተዋሉ እየተነገረ ነው።
በሀገራቱ ጦርነት ምክንያት ከሚጠፋው የሰው ህይወት ፣ ከሚሰደደው ሰው ባለፈ በዓለም ኢኮኖሚ እና በሀገራት የኑሮ ውድነት ላይ በየዕለቱ እያሳደረ ያለው ግልፅ ተፅእኖ እየከፋ ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Ukraine #Russia የሩስያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ ሁለት የዩክሬን ጦር ሂሊኮፕተሮች የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ተሰማ። ሁለት የዩክሬን ሄሊኮፕተሮች የሩሲያን ድንበር ጥሰው በሀገሪቱ ምዕራባዊ ከተማ ቤልጎሮድ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአከባቢው አስተዳዳር ዛሬ አስታውቋል። የአካባቢው አስተዳዳሪ የሆኑት ቫያቼስላቭ ግላድኮቭ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ ሁለት የዩክሬን…
" በድርድሩ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል " - ዴሚትሪ ፔስኮቭ
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የዩክሬን ጦር ሄሊኮፕተሮች ፈፀሙት በተባለው ጥቃት ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል።
ፔስኮቭ ፤ በሩሲያ ቤልጎሮድ የነዳጅ ማከማቻ ላይ የዩክሬን ሂሊኮፕተሮች ፈጸሙ የተባለው ጥቃት በኪየቭ እና በሞስኮ መካከል በሚደረገው ድርድር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ብለዋል።
የሩስያ ቤልጎሮድ አስተዳደር ድንበር ጥሰው የገቡ የዩክሬን ሂሊኮፕተሮች በአካባቢው ባለ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ፤ በተነሳው ቃጠሎም ውስጥ በነበሩ ሁለት ሰራተኞች ላይ የመቁሰል አደጋ ማጋጠሙን ዛሬ መግለፁ ይታወቃል።
በዩክሬን በኩል እስካሁን የተሰጠ አሰተያየት የለም።

#HoPR #MoE
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2013 ዓ.ም አገር ዐቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አቅም መገንባት እና ተዓማኒነትን ማሳደግ ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው የትምህርት ተቋማትን ተዓማኒነት ለመሸርሸር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተገቢ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ አባላት የፈተና አሰጣጥ እና እርማት ሂደት እንዲሁም በፈተናዎች ደህንነት ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርበዋል።
በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እርማትና ውጤት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ያለበት ማንኛውም አካል ሂደቱን ለመፈተሽና ለማረጋገጥ ከፈለገ ማስተናገድና ግልጽነት መፍጠር እንደሚቻል የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በመጀመሪያው ዙር ከተሰጡት የትምህርት አይነቶች የሲቪክስ ትምህርት ፈተና እንደተሰረቀ የሚያሳዩ አሳማኝ መረጃዎች መቅረባቸውን ተከትሎ የሲቪክስ ውጤት ከዩኒቨርሲቲ መቁረጫ ነጥብ እንዲሰረዝ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙዔል ክፍሌ (ዶ/ር) አስታውሰዋል።
ከክልሎች የተውጣጡ የፖለቲካ አመራሮች እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ትንተና እና የአስተራረም ሂደት ታይቶ የተፈጠረ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበር የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈሪ ፈይሳ ጠቁመዋል።
ምንጭ፦ የህ/ተ/ም/ቤት
More @tikvahuniversity

#Update 21 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል " አብኣላ " መንገድ ወደ ትግራይ ክልል መጓዝ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ከሰዓት አስታውቋል። ተሽከርካሪዎቹ የእህል እርዳታ የጫኑ ሲሆን በዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) አማካኝነት ነው በአፋር አብዓላ በኩል በየብስ ወደ ትግራይ እየሄዱ የሚገኙት። መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ…
#Tigray #Afar #WFP
ወደ ትግራይ ጉዞ እንደጀመሩ የተገለፀላቸው የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት መጀመራቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) አስታውቋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹ ኢሬብቲ ደርሰው ወደ ትግራይ ማቋረጥ መጀመራቸውን የገለጸው ድርጅቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መቐለ ይገባሉ ብሏል፡፡
ከ500 ሜትሪክ ቶን በላይ የተመጣጠነ ምግብ በርሃብ አፋፍ ላይ ለሚገኙ የእርዳታው ፈላጊዎች ይከፋፈላል ተብሏል።
በተጨማሪ ፤ ከ1000 ሜትሪክ ቶን በላይ የተመጣጠነ ምግብ የጫኑ ሌሎች የእርዳታ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ከሰዓት ሰሜናዊ አፋር መድረሳቸውንም የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡
የሰብዓዊ እርዳታው ፦
👉 ዳሎል፣
👉 በራህሌ
👉 ኮነባ አካባቢዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚደርስ ገልጿል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲያልፉ የአፋር ክልላዊ መንግስት እና ህዝብ ትልቅ ድጋፍ እንዳደረገ ገልጿል።
መረጃው የዓለም ምግብ ፕሮግራም የትዊተር ገፅ ነው።
ፎቶ ፦ ወደ ትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ ጭነው እየተጓዙ የነበሩት ተሽከርካሪዎች (ከአፋር ክልል ቲክቫህ አባላት)

የረመዳን ፆም ነገ ይጀምራል።
1443ኛው የረመዳን ፆም ነገ መጋቢት 24 ይጀምራል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን በመታየቷ ፆሙ ነገ ቅዳሜ እንደሚጀምር አረጋግጧል።
@tikvahethiopia
1443ኛው የረመዳን ፆም ነገ መጋቢት 24 ይጀምራል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን በመታየቷ ፆሙ ነገ ቅዳሜ እንደሚጀምር አረጋግጧል።
@tikvahethiopia
#KonssoZone📍
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ የወረዳው የገቢዎች ኃላፊ ምግብ ቤት ውስጥ በጥይት መገደሉ ከተገለጸ በኋላ በተከታታይ 4 ሰዎች መሞታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ ያሳያል።
ህይወታቸው ያለፈው የ ' ሰገን ገነት ቀበሌ ' ሊቀመንበር አቶ ኩሴ ጦኔ እንዲሁም አንድ የሚሊሻ አባል እና 2 ነዋሪዎች ናቸው።
የወረዳው የመንግስት ተጠሪ አቶ ገመይዳ ጉዴኖ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት መጋቢት 18 ቀን 2014 የአከባቢው ሚሊሻ ከደራሼ ልዩ ወረዳ ሀይቤና ቀበሌ በኩል የመጡ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመውበት መገደሉን ገልጸዋል። አቶ ገመይዳ ፥ " ጥቃቱ ሲፈጸምም ሽፋን የሰጠ አካል የለም " ሲሉ ነው የገለጹት።
በመቀጠልም ፤ መጋቢት 22 በግምት ከቀኑ 8:30 አከባቢ የሰገን ገነት ቀበሌ ሊቀመንበር ኩሴ ጦኔ በታጣቂዎቹ ታፍኖ መሳሪያውን ተቀምቶ ተገድሏል ብለዋል። ''ትላንት ማታ ነው ሬሳ ያወጣነው'' ሲሉም ተናግረዋል።
በዚያው ቀን 5:30 አከባቢም በመጓዝ ላይ በነበሩ 3 ሰዎች ላይ በተከፈተ ጥቃት ሁለቱ ህይወታቸው ሲያልፍ አንደኛው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት መረጃ ይድረስንልን ያሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ፤ ጥቃቱን የሚፈጽሙት " በትጥቅ የተደራጁና መሳሪያ የታጠቁ አካላት " መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከአካካቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያሰባሰብነው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ የክልሉ ልዩ ኃይል ከነበረበት ካንፕ ለቆ በወጣበት ቅጽበት የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ኮሴ ጡኔ በታጣቂዎቹ መገደላቸውን ይጠቁማል።
አቶ ገመይዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሉት የጸጥታ መዋቅሩ ከየቀጠናው ተሰብስቦ በመውጣቱ ጥቃቱን ሚሊሻ ብቻውን መከላከል እንዳልቻለ ጠቁመዋል።
የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በርሻ ኦላታ ፤ " ፅንፈኛው " ሲሉ የጠሩት ኃይል እየፈጠረ ባለው ሁከትና ብጥብጥ ህዝቡ ዳግም መፈናቀሉንና ለእንግልት መዳረጉን ገልፀዋል።
አቶ በርሻ ፤ የመለጋ እና ዱጋያ ቀበሌ ህብረተሰብ መንግስት የሰጣቸውን ጊዜያዊ መጠለያ ሸራ ቤት በመወጠር ቤት ንብረቱ በተቃጠለበት ቦታ ቀልሰው መኖር በጀመሩበት ወቅት ጥቃት መፈጸሙን አንስተዋል። በዱጋያ ትም/ት ቤት እና ለሰራዊት ማረፊያ የተገነባው ሁለት ካምፕ ላይም ጥቃት ደርሷል ሲሉ ነው የገለፁት።
በተመሳሳይ ከትላንትና መጋቢት 22 ቀን 2014 ማታ ጀምሮ " ጋርጨ " በሚባል ቀበሌ ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለው ሸራ ወጥረው በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መከፈቱን የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን መልዕክት ጠቁመዋል።
ጥቃት አድራሾቹ ሸራውን ሙሉ ለሙሉ ማቃጠላቸውን እና ለመቋቋሚያ የተሰጣቸውን ቆርቆሮም መዘረፉ ተጠቅሷል።
በአጠቃላይ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች በ7ቱ ላይ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን አምስቱ ሙሉ ለሙሉ መቃጠላቸውን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡ ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት የአካባቢው ቤተሰቦቻችን ሶስት አመት ሙሉ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ መሰቃየታቸውን ይናገራሉ።
ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ የክልልና የፌደራል መንግስት አካላት እንዲያውቁት ቢደረግም እዚህ ግባ የሚባል ምላሽ እንዳላገኙና ይበልጡኑ ይህ ችግር ባለበት ሁኔታ ያሉትን የጸጥታ ኃይሎች ማንቀሳቀስ ለችግሩ መስፋፋት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

Photo
🤲 ረመዳን 🤲
ነገ ቅድሜ ታላቁ የረመዳን ፆም አንድ ብሎ ይጀምራል።
ቤተሰቦቻችን እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም አደረሳችሁ።
ረመዳን የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የሰላም ፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ወር ነው።
በዚህ ታላቁ ወራችን በስቃይና መከራ ፣ በሰላም እጦት ፣ በግጭት እና በጦርነት ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ወድቀው የሚገኙ፣ በረሃብ እና ጥማት የሚሰቃዩ፣ በድርቅ የተጎዱ ፣ በህመም እና በጭንቀት፣ በተለያየ የኑሮ ፈተና ላይ ያሉትን ወገኖቻችን ሁሉ እድናስብ አደራ እንላለን።
እንዲሁም ለዓለም፣ ለሰው ልጅ ሁሉ ሰላም እና ደህንነት ፈጣሪያችንን አጥብቀን የምንማፀንበት ፤ ፈጣሪያችንም ተማጽኗችንን የሚሰማበት እንዲሆንልን እንመኛለን።
رمضان مبارك
#TikvahFamily❤️

#ZOnlineShopping
የጀርባና የወገብ ችግር አለቦት?
ሙሉ የጀርባ አና የወገብ ቀበቶ 950 ብር
የትከሻ ቀበቶ 650 ብር
የመቀመጫ (Cushion) 850 ብር
የጀርባ መደገፊያ (Pillow) 750 ብር
የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣ የጀርባ ዲስክ መንሸራተት በእድሜ መግፋት የሚመጡ የጀርባ ችግሮች የሚከላከልና ቀጥያል እና ማራኪ ቁመና የሚያላብስ
ስልክ ፦ 0989055551 ፡ ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን።
አድራሻ ፦ ቦሌ አቢሲንያ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

#Tigray #Afar #WFP ወደ ትግራይ ጉዞ እንደጀመሩ የተገለፀላቸው የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት መጀመራቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) አስታውቋል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ ኢሬብቲ ደርሰው ወደ ትግራይ ማቋረጥ መጀመራቸውን የገለጸው ድርጅቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መቐለ ይገባሉ ብሏል፡፡ ከ500 ሜትሪክ ቶን በላይ የተመጣጠነ ምግብ በርሃብ አፋፍ ላይ ለሚገኙ የእርዳታው…
ፎቶ ፦ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 13 ተሸከርካሪዎች በሰላም የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በፎቶ አስደግፎ አስታውቋል።
ይህ ከታህሳስ 2014 ዓ.ም. አጋማሽ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በየብስ ትግራይ ክልል የደረሰ የሰብዓዊ ድጋፍ ነው።
እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ ተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ ዛሬ ይገባል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትላንትና ከወራት በኋላ የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ ማድረሱን "እጅግ አስፈላጊ የሆነ መልካም እርምጃ ነው" ብሎታል።
ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑት ተሽከርካሪዎች የደህንነት ስጋት ሳያጋጥማቸው በሰላም ትግራይ መድረስ በመቻላቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና አጋሮቹ የፌደራል መንግስትን ፣ የአፋር ክልል መንግሥት እንዲሁም የአፋር ማሕብረሰብ አባላትን አመስግነዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 5 ሚሊዮን ሰዎች ለመድረስ የእርዳታ መጠኑን እና ፍጥነቱን በመጨመር የአቅርቦት ስራውን ማስቀጠል አለብንም ብሏል።