#MinjarShenkora📍
በምንጃር ሸንኮራ በተፈፀመ ጥቃት የሰው ህይወት አለፈ።
በወረዳው " አሞራ ቤት ቀበሌ " ላይ ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለው ጥቃት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ጥቃቱ ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ " አዉራ ጎዳና መንደር ትናንት ከሰዓት የተፈፀመ ሲሆን የሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ከሚል መረጃ ውጭ ምን ያህል የሚለው አልታወቀም።
ወረዳው ጥቃቱን ያደረሱ ታጣቂዎች ምናልባት ማንነታቸው ያልታወቁ " የፀረ ሰላም ኃይሎች " ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።
የምንጃር ሸብኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት ጥቃቱን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ፦
" ትላንትና መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ ልዩ ቦታዉ አዉራ ጎዳና ተብሎ በሚጠራ መንደር ላይ ታጣቂዎች በተደራጀ እንዱሁም በቡድንና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ባደረሱት ጥቃት የሰዉ ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል " ብለዋል፡፡
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ግለሰቦች በአረርቲ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተልከዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
" አካባቢዉ ለዓመታት የተለያዩ ትንኮሳዎች ይስተዋልበት ነበር ያሉት " አቶ ታደሰ ፤ " የትናንቱ ግጭት ግን መነሻዉ በግልፅ የማይታወቅ ፤ ምናልባትም ማንነታቸዉ በግልፅ ያልታወቁ ፀረ ሰላም ኃይሎች አቅደዉበት እና አካባቢዉን በማዉደም ነዋሪዎችን ለማፈናቀል አልመዉ የመጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል " ብለዋል፡፡
አቶ ታደሰ ቦሰት " ለጊዜዉ ማንነታቸዉ ያልታወቁ ታጣቂዎቹ ጥቃት ማድረሳቸዉን ተከትሎ ንፁሀን እንዳይጎዱ በተለይ ሴቶችን ህፃናትንና ነፍሰጡሮቹን ከስፍራዉ የማዉጣት ስራ ተሰርቷል " ያሉ ሲሆን " ቤት ንብረታቸዉን ትተዉ ወደ ጫካ የሸሹ በመኖራቸዉና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ተጨማሪ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
" ትናንትና አመሻሽ ከ12፡00 በኋላ በአካባቢዉ የፌደራል ፖሊስ በመግባቱና የማረጋጋት ስራ በመሰራቱ አሁን ጥቃቱ በቁጥጥር ስሮ ዉሏል " ብለዋል።
" የአካባቢዉን ሰላም ለማናጋት ከሁሉም ወገን የፀረ ሰላም ኃይሎች ሊኖሩ ይችላሉ " ያሉት አቶ ታደሰ ፤ " በማጥራት እና የጋራ ምክክር በማድረግ የአካባቢዉን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ የሚገባ ጉዳይ ነዉ " ብለዋል።
ወረዳው በትላንትናው ጥቃት አድራሾቹ " የማይታወቁ ፤ ፀረ ሰላም ኃይሎች " እያለ መጥራቱ ቅሬታ ያሳደረባቸው አካላት እንዲህ ያለው መሸፋፈን ይበልጥ ችግሩን ከማወሳሰብ በዘለለ ምንም አይነት ፋይዳ እንደሌለው አስገንዘበዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች ለሚፈፀሙ ጥቃቶች " ማንነታቸው ያልተረጋገጠ፣ ፀረ ሰላም ኃይሎች " የሚሉ ቃላትን መጠቀም የተለመደ ነው።
@tikvahethiopia