TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Alert‼️

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል #መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት #አልፏል። መንግስት ለአካባቢው ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ እና በአስቸኳይ የሰላም ማስከበር ስራዎችን እንዲያከናውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የTIKVAH-ETH አባል ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #መተከል አካባቢ ለሚገኙ የሀገራችን ዜጎች‼️ #ኢትዮጵያ #ETHIOPIA #ቤንሻንጉል

#መከላከያ_ሰራዊት
#ፌደራል_ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንሰማለን ወይ

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በመላው ሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ ይገኛሉ። የቤተሰቡ አባላትም ከሁሉም ብሄር እና ሀይማኖት የተውጣጡ ናቸው። ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያን ለመገንባትም ትልቅ መስዕዋትነት እየከፈሉ ያሉ ሀገር ወዳድ ወጣቶችንም በውስጡ ያቀፈ ነው። TIKVAH-ETH በሚሰራው ስራ ሁሉ ማንም አካልና ድጋፍ አያደርግለትም፤ ከትኛውም መንግስት አካል ድጋፍ የለውም እንዲሁም አይታገዝም። ሁሉም ስራ የሚሰራው በቤተሰቡ ጠንካራ ድጋፍ ነው።

ጥያቄያችን...

በዚህ ቻናል ውስጥ በርካታ ሰዎች አለን፤ በመንግስት ተቋማት ህዝብ የምናገለግል ሰዎች አለን፤ በስልጣን ላይ የምንገኝም አንጠፋም ለምን የህዝብ ጥቆማ አይሰማም??

ከዚህ በፊት፦ ቡራዩ እና አከባቢው ችግር ሲፈጠር የቤተሰባችን አባላት ስጋታቸውን ሲገልፁ ነበር። "Alert" እያልን ስንጮህ ነበር። የፖሊስ ስልኮችም ስንለጥፍ ነበር። ነገር ግን ሼር ያደረገው እና ለጉዳዩ ምላሽ የሰጠውም አልነበረም። ከ2 ቀን በኃላ ግን ፌስቡክን በሙሉ ጥቁር አለበስነው።

በተመሳሳይ፦ ከቀናት በፊት በቤንሻንጉል #መተከል ችግር እንዳለ ዜጎቻችን ህይወታቸው አደጋ ላይ እንዳለ ሲነግሩን እኛም #በAlert አሳውቀን ነበር። ነገር ግን ከ1 ቀን በኃላ ሆኖ የሰማነው የሰዎችን ህልፈት ነው። የሰላም መደፍረስን ነው።
.
.
ሁሉንም ባይሆን ለሚሰጡት ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ የምትሰጡ አካላትን በዚህ አጋጣሚ ሳናመሰግን አናልፍም።

አሁንም የቤተሰባችን አባላት ስቃያችሁን፣ ስጋታችሁን የሚደርስባችሁን ሁሉ እርስ በእርስ እንጋራዋለን!!

በኢትዮጵያ ተስፋ እንቆርጥም!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia