TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወደቦችን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን መልሶ ለመገንባት የ20 ሚሊዮን ዩሮ #ድጋፍ ማድረጉን የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ሁለቱን ሀገራት ለመደገፍ #ቁርጠኛ መሆኑን የህብረቱ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኔቨን ሚምካ ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት በማጠናከርና ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ለሁለቱ ሀገራት ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ20 ዓመታት በኋላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አሜሪካ ለኢትዮጵያ የ40 ሚሊየን ዶላር #ድጋፍ ይፋ አደረገች፡፡ ድጋፉ ለሀገሪቱ የጤና ዘርፍ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ድጋፉ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡

Via Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስነ- ህዝብ ፈንድ ለ4ኛው ዙር አገር አቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤታማነት #ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በነገራችን ላይ...

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ቆጠራውን አስመልክቶ ለክልል፣ ለከተማ አስተደደር፣ ለዞንና ለወረዳ የቆጠራ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ያዘጋጀውን ስልጠና ትላንት መስጠት ጀምሯል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዴኦ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አቶ ነጉሱ ጥላሁን #በጌዴኦ ላሉ ተፈናቃዮች የዕለት ምግብ ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት #ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መንግሥት የዕለት ደራሽ ምግብ ለሚያስፈልጋቸው #ድጋፍ ለማድረግ ከፌደራል እና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከዚህ ቀደምም ሲሰራ ቆይቷል፤ በዚህም እንዲቋቋሙ የተደረጉ እንዳሉም ገልጸዋል።

ነገር ግን አሁንም #የዕለት_ደራሽ_ምግብ ያልደረሳቸው ዜጎች እንዳሉ እና ችግር ላይ እንደወደቁ መንግሥት ተረድቶ የዕለት ምግብ ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶት ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ዜጎችን በማቋቋም፣ #የህግ_የበላይነትን በማረጋገጥ የሚደርሱ ማፈናቀሎችን ማስቆም መቻል ላይ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ሆስፒታል‼️

ዲላ ሆስፒታል በጌድዮ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች #ድጋፍ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚልክ አስታወቀ።

የዲላ ሆስፒታል ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በመሆን በጌድዮ ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ህክምና በሚሰጥባቸው ሆስፒታሎች የጤና ድጋፍ እና እገዛ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው እንደሚልክ የሆስታሉ የህክምናና ተግባር ስልጠና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሰላማዊት_አየነ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

ከሀኪሞችና ነርሶች የተውጣጣው የባለሞያዎች ቡድን መድሀኒት፣ የህክምና ቁሳቁሶችንና ሌሎች ግብዓቶችን በመያዝ የህክምና እርዳታ ስራ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ገደብ እና ይርጋ ጨፌ ሆስፒታሎች ለተፈናቃዮች ህክምና እየተሰጡ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፎቶዋ ሲዘዋወር የነበረችው እናት በዲላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት መሆኑም ታውቋል፡፡

ታካሚዋ ላጋጠማት የምግብ እጥረት የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ሲሆን መንቀሳቀስ እንድትችልም የፊዝዮ ቴራፒ ህክምና እያገኘች መሆኗ ተጠቅሷል፡፡

ለእናቲቱ ሌሎች የጤና ምርመራዎችም እየተደረጉላት እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ከአዲስ አበባ ህዝብ የተሰበሰበውን #ድጋፍ ለማስረከብ #ጌዴኦ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ #የተፈናቀሉ ዜጎች በናተው በኩል በተሰበሰበ ገንዘብ #ድጋፍ ለማድረግ የተደረገ ጉዞ። #TIKVAH_ETH #ጌዴኦ #ኢትዮጵያ

ዝርዝር መረጃዎች ይኖሩኛል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም ግቡ...

የአርባ ምንጭ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ከ571,000 ብር በላይ የሚያወጣ #ድጋፍ በጎፋ ዞን ተፈናቃዮች በሚገኙበት አካባቢዎች ላሉ ለአስተባባሪዎች አስረክበው ወደየመጡበት እየተመለሱ ነው። ሰላም ግቡ!

Via ፋሪስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እየተሳተፉ የሚገኝበት የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቲካድ የመሪዎች ስብሰባ ተጀምሯል፡፡ በመክፈቻው ላይ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ ጃፓን ለአፍሪካ በጤና እና በትምህርት መሰረት ልማት እያደረገች ያለውን #ድጋፍ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ልማት ዙሪያ ምክክር የሚያደርገው የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቲካድ አፍሪካ ከድህነትና ኃላቀርነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ በጃፓን ጠንሳሽነትና አመራር ለአፍሪካ ልማት የሚካሄድ ኮንፈረንስ ነው፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፖሊስ የዘፈቀደ እስር በአስቸኳይ ሊቆም እና የታሰሩትም ሊለቀቁ ይገባል! (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን) በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች በፖሊስ እየታሰሩ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ በሚዲያዎች የወጡ ዘገባዎችንና ለኮሚሽኑ የቀረቡ አቤቱታዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚከተለውን ብለዋል ፦ …
ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ታስረዋል!

(በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተላላፉ ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች የአፍና የአፍንጫ መከለያ ባለመጠቀማቸው ለእስር መዳረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንደተናገሩት የታሳሩ ሰዎች ምን እርምጃ ይወሰድባቸዋል የሚለውን በቀጣይ ማብራሪያ እንሰጣለን ብለዋል፡፡

ህግ አስከባሪ የፖሊስ አባላት እራሳቸው የፊት መሸፈኛ ሳያደርጉ እና ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል ፣ ለምን ሆኑ ተብለው ከሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት ኮማንደር ፋሲካ ለእነሱም አንደ ህዝቡ የግንዛቤ ትምህርት ይሰጣል ተላልፎ የሚገኝ የፖሊስ አባል ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

እየወሰድን ባለው እርምጃ ከህዝቡ #ድጋፍ እያገኘን ነው ፣ እየታሰሩ ያሉትም ብዙ ህዝብ ከሚበዛባቸው አካባቢዎች የተያዙ ናቸውም ብለዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia