TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢንተርን

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተር ሀኪሞች ከስራ ሰዓትና ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኢንተርን ሀኪሞቹ ምን አሉ ?

“ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሆስፒታሉ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር።

ነገር ግን የኮሌጁ ግለሰብ / #ዳይሬክተር ሲቀየር በራሱ ውሳኔ የራሱን መላምት በመፍጠር መልሶ ወደ 36 ሰዓታት ከፍ አድርጎታል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ የሥራ ሰዓት ከዚህ በፊት ሴኔቱ በወሰነው መሠረት ይሁንልን ብለን ጠየቅን። ይህንንም በመጠየቃችን የተበሳጨው የዲፓርትመንት አስተባባሪ ፦
• ከቀዶ ጥገና፣
• ከህፃናት፣
• ከማህፀንና የፅንስ ዲፓርትመንት ጋር መከረ። እነዚህ ዲፓርትመንቶች አስገድደውን ሥራ ጀመርን።

የሥራ ሰዓታችን እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠየቅን።

በዲፓርትመንት ደረጃ እየተሰበሰቡ ' ከዚህ በኋላ ይህን ጥያቄ የሚያየሳ ሀኪም እስከ ዲሲሚሳል ድረስ እንቀጣቸዋለን ' አሉ። ከዚህ በተጨማሪ የቀን ሥራ ሰዓታትን በአንድ ሰዓት ከፍ እንዲል ከነበረው ሕግ ውጪ ሆነብን።

ያንን ሁሉ ችለን ደመወዝ ይከፈለናል ብለን ብንጠብቅም ሳይከፈለን መጋቢት 14/2016 ዓ/ም 10ኛ ሳምንታት ጨርሰናል። ” የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክሴኩይቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አይንሸት አዳነን ጠይቀናል።

ምን አሉ ?

ዶ/ር አይንሸት ፥ “ የሰዓት ጭማሪ ለሚለው እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የተጨመረ ነገር የለም። ከድሮው የተቀየረ አሰራር የለም። እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት እነርሱን #ያስፈራራቸው_ሰው_የለም ” ብለዋል።

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ስንት ተብሎ ነው የተወሰነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ በክሬዲት ደረጃ ይህን ያህል የትርፍ  ፤ ይህን ያህል የመደበኛ ተብሎ የተቀመጠ ነገር የለም

ለበርካታ አመታት ሲሰራበት ከነበረው መንገድ የተለየ እነርሱ ጋ የተጨመረ ነገር የለም። ”

Q. ዩኒቨርሲቲው 36 ሰዓታት የነበረውን የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዳደረገ መረጃዎች ያሳያሉ ፣ ሀኪሞቹም ወደ 24 ሰዓት ዝቅ ተደርጎ የነበረ ወደ 36 ሰዓት ከፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል ፣ እርስዎ ደግሞ የተወሰነ ሰዓት እንደሌለ እየገለጹ ነው ለዚህስ ያለዎት ማብራሪያ ምንድን ነው ? ስንል ጠይቀናል።

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ የሆነ ጊዜ ጫናው ስለበዛ በኢንተርን ሀኪሞች ጥያቄ ተነሳና ዲፓርትመንቶች ራሳቸው ከኢንተርን ሀኪሞች ጋር ውይይት አድርገው (የተወሰኑ ዲፓርትመንቶች እንዲያውም ሙሉ አይደለም) አምነውበት ወደ ተግባር ተገባ። አሳማኝ ስለሆነ የሥራ ጫናው።

ይሁን እንጂ ለተወሰነ ወራት ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ አድረው በሚወጡትና ተተኪ ሆነው በሚገቡት ኢንተርን ሀኪሞች መካከል የርክክብ ክፍተት መፈጠሩ የጤና አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ ስላመጣ፣ የኢንተርን ሀኪሞች ተመርቀው ሲወጡ የተሟላ እውቀት እንዳይቀስሙ ያደርጋል በሚል ወደ ነበረበት ይመለስ ተብሎ ተመልሷል። ”

Q. ‘ደመወዝ አልተከፈለንም’ ሚለው የሀኪሞቹን ቅሬታስ?

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ ሀኪሞቹ አጠያየቃቸው ልክ አልነበረም።

ኦረንቴሽን እንዲሰጣቸው በደብዳቤ ጭምር ቢጠሩም መገኘት አልቻሉ።

‘ይህ ካልተደረገልን (ቅሬታው ምላሽ ካላገኘ) ሥራ አንገባም’ በማለታቸውና ሳምንቱን ሙሉ ከሥራና ት/ት ገበታ ባለመገኘታቸው የሕክምና ትምህርት ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ፣ የ3 ወራት ደመወዝ ነው የተቀጡት። ያለ ደመወዝ እንዲሰሩ ነው የህክምና ት/ቤቱ የወሰነው። ”

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia