TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SpecialOlympics

የሚዲያና የኮምንኬሽን ባለሙያዎች ስፔሻል ኦሎምፒክስን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።

የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ተሳታፊ የሚያደርገው ስፔሻል ኦሎምፒክስን የሚድያ ባለሙያዎች እንዲያዙ ጥሪ የቀረበው ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አዳራሽ ለሚድያና ኮምንኬሽን ባለሙያዎች በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ነው።

የስፔሻል ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ እንደገለፁት በሀገራችን ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር የሚኖሩ በርካታ ልጆች ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እንዳይቀሩና ያላቸውን ልዩ ተሰጥኦ በአደባባይ እንዲያሳዩ ስፔሻል ኦሎምፒክስ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ስለሆነ የሚድያና የኮምንኬሽን ባለሙያዎች ለጉዳዩ ሰፊ የሚድያ ሽፋን በመስጠት አጋር እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

በቀዳማዊት እመቤት ክብርት ዝናሽ ታያቸውና አጋር አካላት አነሳሽነት በቅርቡ የተመሰረተው ስፔሻል ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ ፤ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች ኢትዮጵያን በመወከል በዱባይና ግብፅ በተደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች የወርቅና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ እንዲሆኑ አስችሏል ።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ

@tikvahethiopia