TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UK

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ መጥተው ስለሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እና ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ከከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሰልጣናት ጋር ውይይት አድርገው የነበሩት የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ፤ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም እና ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እንዲደርስ ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነት አጥብቀው እንደሚደግፉ አሳውቀዋል።

ቪኪ ፎርድ ፥ የትግራይ ባለስልጣናት ተኩስ በማቆም እና ከአፋር በመውጣት ምላሽ መስጠት አለባቸው ብለዋል።

የታየው ቁርጠኝነት በተግባር ሰብዓዊ እርዳታ ወደመላክ መተርጎም አለበት ያሉት ሚኒስትሯ ይህንንም የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለመደገፍ ዝግጁ ነው ሲሉ አብስረዋል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም ዝግጁ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ከያዛቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች ለቆ ስለመውጣት ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ38 ዓመታት ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ትላንት አዲሱን…
#Update

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ ከተሾሙት የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ግርማ ዋቄ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳ አዲስ ለተሾሙት የቦርድ ሰብሳቢ እንኳን ወደ ቤቶ በደህና ተመልሰው መጡ የሚል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትን አስተላለፈው የሰራተኛ ማህበሩ እንደከዚህ ቀደሙ ሰራተኞችን አስተባብሮ ለድርጅቱና ለሰራተኛው ጥቅም በርትቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄም በአዲስ መንፈስ ለተሻለ ለውጥና ዕድገት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አስተባብረው ለመስራት ቁርጠኝነት እንዳላቸው አስታውቀው የሰራተኛ ማህበሩ ሚና ትልቅ በመሆኑ ለተሻለ ለውጥና እድገት በጋራ ለመስራት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።

Via Abdi Kuma

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
#AU #IGAD

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳፋቂ መሃመት የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የበትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማድረስ የወሰነው ውሳኔ ይደነቃል ብለዋል።

በተጨማሪ ፤ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለሰብዓዊነት ተብሎ ግጭት ለማቆም የተላለፈውን ውሳኔ ለመመልከት እና በአስቸኳይ ግጭት ለማቆም ማወጁን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

ለጋሾች እና የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርጉትን ድጋፍ በእጥፍ እንዲያሳድጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ ሁሉን አቀፍና በድርድር በሚመጣ የተኩስ አቁም ላይ ሁሉም ወገን እንዲደርስ ህብረቱ ጥረቱን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከሁሉም ወገን እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ግጭቱን በፍጥነት ለመቋጨት የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሊቀመንበሩ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ማቆሙን አድንቀዋል ፤ የትግራይ ክልል መንግስትም ውሳኔው ንለማክበር እና ግጭት ለማቆም በመወሰን ምላሽ በመስጠቱ አድንቀዋል።

ለትግራይ ክልል እና ሌሎች በድርቅና በምግብ እጦት ለተጎዱ ክልሎች ሰብዓዊ እርዳታ በተጠናከረ መልኩ እንዲደረግ ዓለም አቀፍ አጋሮች የቻሉትን ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ብሄራዊ ውይይት ጨምሮ ለዘላቂ ሰላም መስፈን ሁሉንም የሰላም አማራጮችን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#ሹመት

አቶ ደሳለኝ ጣሰው የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ሆነው ተሾሙ።

አቶ ደሳለኝ ሹመቱ የተሰጣቸው የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ነው።

በተጨማሪም ዶ/ር አማረ ብርሃኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል።

መረጃው የአሚኮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ukraine #Russia

ሩሲያ የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍት ገለፀች።

ሀገሪቱ ይህን የገለፀችው በዩክሬን እያካሄድኩ ነው ያለችውን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” የመጀመሪያውን ምዕራፍ ማጠናቀቋን ባሳወቀችበት ወቅት ነው።

ሀገሪቱ ተጠናቋል ባለችው የመጀመሪያ ምዕራፍ ያስቀመጠችው ግቦች እንደተሳኩ የገለጸች ሲሆን ብዙ የዩክሬን ግዛቶችን መቆጣጠሯን አሳውቃለች።

ሩስያ ጦሯ የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪቭን ጨምሮ ካርኪቭ፣ ቼርኒሂቭመ ሱሚ እና ሚኮላይቭ የተባሉ አካባቢዎችን መክበቡን ገልፃለች። በተጨማሪ ኬርሶን እና ዛፖሮዚ የተባሉ የዩክሬን ግዛቶች አሁን ላይ በእጇ ላይ መውደቁን አሳውቃለች።

በዩክሬን የተገንጣዮች ግዛት የሆነችውን ሉሃንስክን ደግሞ 93 በመቶ መቆጣጠሯን አሳውቃለች።

የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍትም ዝታለች።

4 ሳምንታት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ሲያልቁ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ተሰደዋል።

መረጃው የአልዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ 160 እጩ የወረዳ ፍ/ቤት ዳኞችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 💵🛢️ እ.ኤ.አ. ህዳር አንድ 👉 68 ዶላር 🛢️ እ.ኤ.አ. ታህሳስ አንድ 👉 77 ዶላር 🛢️ እ.ኤ.አ. ጥር አንድ 👉 89 ዶላር 🛢️ እ.ኤ.አ. የካቲት አንድ 👉 97 ዶላር 🛢️ ዛሬ ላይ የአንድ በርሜል የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 👉 108 ዶላር ደርሷል። የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከቀናት በፊት ባለፉት ሳምንታት ከታየው ከፍተኛ ጭማሪ (እስከ 140…
#Update

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 120 ዶላር ደርሷል።

ከ5 ቀን በፊት በተለዋወጥነው መረጃ የ1 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 108 ዶላር ሲሸጥ የነበር ሲሆን ዛሬ ላይ 120 ዶላር ደርሷል።

ከሳምንታት በፊት ከፍተኛ የሆነ ቅናሽን አሳይቶ ከአንድ መቶ ዶላር በታችም ወርዶ የነበረው የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ዳግም በከፍተኛ ፍጥነት አሻቅቧል።

ሩስያና ዩክሬን የገቡበት ጦርነት አራት ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን በነዳጅ ዋጋ ላይ እያሳደረ የሚገኘው ተፅእኖ እጅጉን በርትቷል።

@tikvahethiopia
#SuperSport

ዓለም አቀፍ የሆኑ የስፖርት ውድድሮች በሱፐር ስፖርት በአማርኛ ቋንቋ መቅረብ ጀመሩ።

በመልቲቾይስ አፍሪካ እህት ኩባንያ " ሱፐርስፖርት " አማካኝነት በDSTV ቻናል 240 አዲሱ ቻናል ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ የስፖርት ክንውኖችን በአማርኛ ቋንቋ ከመጋቢት 9 ጀምሮ ማስተላለፍ መጀመሩን ዛሬ ባዘጋጀው ይፋዊ የማሳወቂያ መርሐግብር ላይ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዋናነት በዚህ የሱፐር ስፖርት ልዩ ቻናል 240 ይተላለፋል ነው የተባለው።

ሱፐርስፖርት ልዩ በአማርኛ ቋንቋ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ቻምፒየንስ ሊግ፣ ኤፍ ኤካፕና ሌሎች የስፖርት ውድድሮችን የሚያቀርብ ሲሆን የአትሌቲክስ፣ UFC & Boxing፣ WWE እንዲሁም የቴኒስ፣ ጎልፍ፣ የሞተር ውድድር፣ ራግቢና ክሪኬት በአማርኛ ቋንቋ ይተላለፋሉ ተብሏል።

በዕለቱም የ " አቦል ቴሌቪዥን " አንደኛ ዓመት የተከበረ ሲሆን የቴሌቪዥን ቻናሉ በተለይ በፊልም ኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረው ጉልህ ድርሻ ተነስቷል።

በመድረኩ የአማርኛ ይዘቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የግርጌ የትርጉም ጹሑፍ (Subtitles) ታክሎባቸው ለዕይታ ይበቃሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NewsAlert

" አራምኮ " የነዳጅ አምራች የሚሳኤል ጥቃት ደረሰበት።

በጅዳ ከተማ ሚገኘው አራምኮ የተሰኘው የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ አምራች ድርጅት ዛሬ በሚሳኤል ጥቃት ተፈፀመበት።

ጥቃቱን ሁቲዎች እንደፈፀሙት የተገለፀ ሲሆን ቡድኑም ኃላፊነት ወስዷል።

በሳዑዲ የሚመራው የአረብ ሀገሮች ጥምረት በ " ኢራን " የሚደገፈው የየመኑ ሁቲ ሚሊሻ በአራምኮ የነዳጅ ማምረቻ ላይ ጥቃት ማድረሱን አሳውቋል።

ጥቃቱ በ 'ነዳጅ ምርቶች የማከፋፈያ ጣቢያ' ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የገለፀው ጥምረቱ በጥቃቱ በሁለት ታንኮች ላይ የእሳት ቃጠሎ መድረሱን እና እሳቱን መቆጣጠር መቻሉን ገልጿል።

በሰው ላይ ሞት ሆነ የአካል ጉዳት አልደረሰም።

@tikvahethiopia
#Sport

ግብፅ እና ሴኔጋል ዳግም ተገናኝተዋል።

ግብፅ እና ሴኔጋል ለኳታሩ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ በግብፅ መዲና ካይሮ እያደረጉ ይገኛሉ።

በደርሶ መልስ (መጋቢት 15 እና 19) ከሚደረገው ጨዋታ በኃላ ግብፅ ወይም ሴኔጋል / ሞሀመድ ሳላህ ወይም ሳድዮ ማኔን በ2022 ዓለም ዋንጫው የምንመለከታቸው ይሆናል።

ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ አድርገው ሴኔጋል ድል በማድረግ ዋንጫውን ማንሳቷ ይታወሳል።

ዛሬስ ወደ ኳታሩ ዓለም ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታ ማን ድል ያደርጋል ? ግብፅ ወይስ ሴኔጋል ?

የጨዋታውን መረጃዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x በኩል ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia
#ZHAddis

እጆላይ ያለው ካሜራ ጊዜ በሄደ ቁጥር የሚሰጠው ጥቅም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ዝቅ እንደሚል ያቃሉ ከማይፈለግ እቃጋ ሳይመደብ አሁኑኑ እኛ ዘንድ ይዘው ይምጡ እንዳይቆጩ አርገን በጥሩ ዋጋ እንገዞታለን።

ይደውሉልን : 0911156257 ከታች ያለውንlink በመጫን የቴሌግራም አባል ይሁኑ https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEUTeB3LSYVFukiuQw

ቦሌ ወሎሰፈር HMM ህንፃ 2ኛ ፍቅ205
#ማኪ_ፋሽን

👉 በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ ይዘንጡ ብዙ አማራጮች ስላሉ ሱቃችንን ይጎብኙ ባሉበትም እናደርሳለን።

ስልክ ፦ 0991212121

👉የጫማ ዝርዝሮችን ከነዋጋቸዉ ለማየት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/makkifashionethiopia

እንዲሁም Facebook ፔጃችንን_ይከተሉ
https://www.facebook.com/makkifashionethiopia

📍አድራሻ ቦሌ መድሐኒያለም ሰላም ሲቲ ሞል ምድር ላይ
👉የስራ ሰአት ከሰኞ-እሁድ ከጠዋቱ 3:00- ምሽት 1:30
#SpecialOlympics

የሚዲያና የኮምንኬሽን ባለሙያዎች ስፔሻል ኦሎምፒክስን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።

የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ተሳታፊ የሚያደርገው ስፔሻል ኦሎምፒክስን የሚድያ ባለሙያዎች እንዲያዙ ጥሪ የቀረበው ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አዳራሽ ለሚድያና ኮምንኬሽን ባለሙያዎች በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ነው።

የስፔሻል ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ እንደገለፁት በሀገራችን ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር የሚኖሩ በርካታ ልጆች ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እንዳይቀሩና ያላቸውን ልዩ ተሰጥኦ በአደባባይ እንዲያሳዩ ስፔሻል ኦሎምፒክስ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ስለሆነ የሚድያና የኮምንኬሽን ባለሙያዎች ለጉዳዩ ሰፊ የሚድያ ሽፋን በመስጠት አጋር እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

በቀዳማዊት እመቤት ክብርት ዝናሽ ታያቸውና አጋር አካላት አነሳሽነት በቅርቡ የተመሰረተው ስፔሻል ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ ፤ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች ኢትዮጵያን በመወከል በዱባይና ግብፅ በተደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች የወርቅና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ እንዲሆኑ አስችሏል ።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ

@tikvahethiopia