TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የከፍተኛ ትምህርት መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ፦

#ለመጀመሪያ_ዙር_ተፈታኞች !

👉 በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351

• በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ 300

• በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 380

🔹በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254

• በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250

• ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች 250

• በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ ነጥብ 280

🔹በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250

#ለሁለተኛ_ዙር_ተፈታኞች !

👉 በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409

🔹 በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች በመንግስት ዩኒቨርሲቲ ለመማር የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305

🔹 በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ300 በላይ

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል - ያንብቡ)

@tikvahethiopia
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#AAU

" ... የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆኑ ግለሰቦች በግቢው ረብሻ ለመቀስቀስ ሞክረዋል። በአሁኑ ሰዓት አንድም የታሰረ ተማሪ የለም " - የአ.አ.ዩ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አማካሪ

@tikvahuniversity በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትላንትና እሁድ ስለተከሰተው ነገር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የኮሚዩኒኬሽን አማካሪ ኢንጂነር ውባየሁ ማሞን ጠይቋል።

ኢጂነር ውባየሁ ማሞ ፦ " ላለፉት ስድስት ቀናት የተለያዩ ነገሮች በግቢው አስተውለናል። ከተማሪዎቻችን ጋር ስንወያይ ቆይተናል። በመጨረሻ ከተማሪዎች አጀንዳ ውጪ የሆነ ነገር እንዳለ ስናውቅ እርምጃ ወስደናል " ብለዋል።

አማካሪው ፤ " ትላንት የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆኑ አልፈው ገብተው ረብሻ ለመቀስቀስ የሞከሩ ስምንት ግለሰቦች ተይዘው በሕግ ክትትል ስር ይገኛሉ " ሲሉም ገልፀዋል።

" ግለሰቦቹ የፖለቲካ አጀንዳ ይኖራቸዋል። " ያሉት ኢ/ር ውባየሁ " ንጹሀን ተማሪዎች ላይ ያልተገባ ነገር ለመፈጸም እንደገቡ ስላወቅን ግለሰቦቹን ለይተን ይዘናል " ሲሉ አስረድተውናል።

" በአሁኑ ሰዓት አንድም የታሰረ ተማሪ የለም። አንድም ከትምህርት ገበታው ያቋረጠ ተማሪ የለም። የመማር ማስተማር ሂደቱ ሙሉ በሙሉ እየሄደ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

ኢ/ር ውባየሁ ፥ " በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን እየተወራ ያለው ሀሰት ነው። ትክክለኛ መረጃ እየወጣ አይደለም። ተማሪዎችንና ቤተሰብን የሚረብሽ ነገር ነው እየወጣ ያለው። " ብለዋል።

አማካሪው ፤ ትላንትና ግለሰቦቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ ለመያዝ የተሰራ ነገር ነበር ያሉ ሲሆን በዚህም ምክንያት የተፈጠረው ችግር ወዲያው ከመንግስት አካላት ጋር በመሆን ተፈቷል ሲሉ ገልፀዋል።
 
@tikvahethiopia
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን መጋቢት 18 እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

የጉባኤው ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጿል።

1ኛ መደበኛ ጉባኤ ፓርቲውን ወደአዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነእፓ አሳውቋል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እና አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ከሰጣቸው 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አንዱ ነው።

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ስንዴ፣ በቆሎ፣ አጃ፣ እና ስኳር ወደ ውጭ እንዳይላክ አገደች።

ሩስያ እህል ለቀድሞ የሶቪየት ሀገራት እንዳይላክ እና በአብዛኛው የስኳር ምርት ወደሌሎች ሀገራት እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ ተሰምቷል።

እገዳው እኤአ እስከ ሰኔ 30 ይቆያል ተብሏል።

ነገር ግን በልዩ የኤክስፖርት ፈቃድ አሁን ባለው የኮታ ሥርዓት ለነጋዴዎች መከፋፈሉ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ሩስያ እህል እና ስኳር እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ መሰማቱን ተከትሎ ከወዲሁ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ መሆኑ ተነግሯል።

ሩስያ በዓለማች ላይ ከፍተኛ እህል ላኪ ሀገር ስትሆን ቱርክ እና ግብፅ ደግሞ ከሩስያ በመግዛት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

@tikvahethiopia
" በዚህ አመት 152 ሺህ ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ይቀላቀላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152 ሺህ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 ፐርሰንት ያህል መሆኑ ተነግሯል።

በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63ሺ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135ሺ209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ፈተናን በሁለቱም ዙር የወሰዱ 598ሺ 679 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 287 ሺ 223 ናቸው ።

የትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤትን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑን አስታወቀ።

በሁለት ዙር በተሰጠው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት 623 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑ ነው የተነገረው።

ከፍተኛ ውጤቱ በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑ ታውቋል።

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ነው የተያዘው።

በአጠቃላይ ፈተናውን በሁለት ዙር 598 ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 287 ሺ223 ተማሪዎች 50% እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
የነዳጅ ዋጋ አሽቆለቆለ።

በዩክሬንና ሩስያ ጦርነት ምክንያት ባለፉት ሳምንታት የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ ማሻቀቡ ፤ በበርሜልም እስከ 140 ዶላር ድረስ ደርሶ ነበር።

በዚህ ሳምንት ግን የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ መቀነሱ ተነግሯል።

አሁን ላይ ፤ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል 98.50 ዶላር ሲሆን በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት 1 በርሜል ነዳጅ 96.14 ዶላር በሆነ ዋጋ እየተሸጠ ነው።

ይህም ባለፉት 2 ሳምንታት የታየ ከፍተኛ ቅናሽ ነው።

@tikvahethiopia
" በአፍሪካ የስንዴ እጥረት ሊከሰት ይችላል " - ተመድ

በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በአፍሪካ የስንዴ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሩዝ በጦርነቱ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ "የረሃብ ወጀብ" እና የምግብ ዋስትና እጦት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በርካታ የአፍሪካ አገራት እና ድሃ አገራት በሩሲያ እና በዩክሬን የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መሆናቸውን የገለፁት ዋና ፀሐፊው አሁን ግን በጦርነቱ ምክንያት ስጋት ውስጥ ወድቀዋል ብለዋል።

ከእነዚህ አገራት መካከል ቀድሞውኑም ሕዝባቸውን ለመመገብ የሚታገሉት ቡርኪና ፋሶ፣ ሶማሊያ እና የመን ይገኙበታል።

የተመድ ዋና ፀሀፊ ጉተሬዝ የዓለም የምግብ አቅርቦት ሥርዓትን ከመንኮታኮት ለመታደግ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጉተሬዝ እየተካሄደ ባለድ ጦርነት ሳቢያ ረሃብ፣ የውሃና የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው ላሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን ለመርዳት 40 ሚሊየን ዶላር እርዳታ እንደሚያስፈልግ ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#RUSSIA #USA

ሩስያ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት #ጆ_ባይደንን ጨምሮ ሌሎች የአሁን እና የቀድሞ ባለስልጣናት ወደ ሀገሬ ድርሽ እንዳትሉ ስትል ማዕቀብ ጣለች።

የሩሲያ መንግስት ወደ ሩስያ እንዳይገቡ እገዳ ከጣለባቸው መካከል ፦

👉 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

👉 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን

👉 የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን

👉 የCIA ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ

👉 የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጀን ሳኪ፣

👉 የመከላከያ ሚኒስትር ሊዮይድ አውስቲን

👉 የቀድሞዋ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ይገኙበታል።

በተጨማሪ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

ቀደም ሲል አሜሪካ በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ላይ ማዕቀብ ጥላ ነበር።

መረጃው የአርቲ ኒውስ እና የአልዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ በቴ ኡርጌሳ ታሰሩ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ቡራዩ ከተማ መታሰራቸውን ከኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አቶ በቴ የታሰሩት ቡራዩ ፖሊስ ጣቢያ ነው። ወደቡራዩ የሄዱት የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ነበር ተብሏል። አብረዋቸው ወደ ቡራዩ የሄዱት ሹፌራቸውም ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል። @tikvahethiopia
#OLF

" ... በእጃችን ከሚሞት ብለው ነው የሰጡን " - ሚሎ ኡርጌሳ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ በቴ ኡርጌሳ ከ1 ዓመት እስር በኋላ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር ተለቀዋል።

ምንም እንኳን አሁን አቶ በቴ ከእስር ቢለቀቁም በከፋ ህመም ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

በቅርቡ እስር ላይ እያሉ ከሌሎች የታሰሩ ባልደረቦቻቸው ጋር የርሀብ አድማ አድርገው እንደነበር ተነግሯል፤ ከዚህ በኃላ ነው የጤናቸው ሁኔታ የከፋው።

የአቶ በቴ ወንድም ሚሎ ኡርጌሳ " በእስር ቤቱ ህመሙ ሲጠናበት ነው የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ቤተሰብ መጥተው እንዲወስዱ ያለው፡፡ " ያሉ ሲሆን አቶ ባቴ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ አዳራ በተባለ ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ በቴ ህመሙ የጠናባቸው አስቀድሞ ህክምና ባለማግኘታቸው እንደሆነ ወንድማቸው አስረድተዋል።

አቶ በቴ ከዚህ በፊት ታስረው ለፍርድ ቤት እንደቀረቡ በሁለተኛው ቀጠሮ የዋስትና መብት የተጠበቀላቸው ቢሆንም ፖሊስ ግን ከቤተሰብም ሰውሮ በተለያዩ እስር ቤትና ማዕከላት እንዳቆዩት ወንድማቸው ተናግረዋል።

ቡራዩ፣ አዋሽ እና ገላን የታሰሩባቸው ስፍራዎች ናቸው።

በዚህ ሁሉ ሂደት ላይ በመጨረሻ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ሆነው የርሃብ አድማ በማድረጋቸው ለህመም መዳረጋቸውን የሚገልፁት ወንድማቸው ሚሎ የርሃብ አድማውን ተከትሎ ከገላን ወደ ቡራዩ ከተወሰዱ በኋላ ከቤተሰብ ጋር ተገናኝተው ምርመራ ሲያደርጉ ለከፋ ህመም የዳረጋቸው በሽታ እንደተገኘባቸው ገልፀዋል።

" ከዚህም በኋላም ቢሆን መልሰው አስረዋቸው ነበረ ቢሆንም በመጨረሻ በእጃችን ከሚሞት ብለው ነው የሰጡን " ሲሉ ወንድማቸው ሚሎ ኡርጌሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/DW-03-15

@tikvahethiopia
ሩስያ በይፋ ከአውሮፓ ምክር ቤት ጋር ተፋታች።

ሩስያ ከድርጅቱ መውጣቷን ለአውሮፓ ምክር ቤት በይፋ አሳውቃለች።

የሩስያ ዱማ ምክትል አፈጉባዔ ፒዮትር ቶልስቶይ ዛሬ ማክሰኞ እንዳስታወቁት ከሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ደብዳቤ ለድርጅቱ ዋና ፀሃፊ ተላልፏል።

" ከአውሮፓ ምክር ቤት ጋር የሚደረገውን ውይይት ለማቋረጡ ሁሉም ሃላፊነት በNATO አባል ሀገራት ላይ ነው " ያሉት ቶልስቶይ " ይህን ሁሉ ጊዜ በሰብአዊ መብቶች ርዕስ የራሳቸውን ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎቶች ለማሟላት እና በሀገራችን ላይ ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሲጠቀሙበት ቆይተዋል " ብለዋል።

አክለውም ፤ " ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በተጣለው ማዕቀብና በፖለቲካዊ ጫናዎች " ምክንያት ሩስያ ዓመታዊውን ክፍያ ለአውሮፓ ም/ቤት አትከፍልም ሲሉ አሳውቀዋል።

ቶልስቶይ ሩሲያ ድርጅቱን ለቃ የምትወጣው " በራሷ ፈቃድ " እንደሆነ ገልፀው ውሳኔው ሚዛናዊ እና የታሰበት ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ። የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች…
" በትምህርት ሚኒስቴር የተቆረጠው ማለፊያ ነጥብ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ እና ችግር ታሳቢ ያላደረገ ነው " - አቶ አለሙ ደባሽ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 229 ተማሪዎች 30 ተማሪዎች ወይም 13 በመቶ ብቻ ማለፋቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቋል።

በወረዳው ቤላ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፈተናው ከተቀመጡ 44 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሁለት ተማሪዎች ብቻ ያለፉ ሲሆን ፈተናውን ከወሰዱ 139 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች 28 ተማሪዎች ብቻ አልፈዋል።

በተመሳሳይ በወረዳው በመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፈተናው ከተቀመጡ 10 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 36 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምንም ተማሪ ማለፍ አለመቻላቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አለሙ ደባሽ ገልጸዋል።

አካባቢው ከአንድ ዓመት በላይ በጦርነት ቀጠና ውስጥ መቆየቱ እና ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ተማሪዎቹ ሙሉ ጊዜያቸውን እና ህይወታቸውን ለጦርነት አሳልፈው በመስጠት ላይ የነበሩ በመሆኑ ለፈተናው ያለበቂ ዝግጅት መቀመጣቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የነበሩበት ሁኔታ እየታወቀ በትምህርት ሚኒስትር ውሳኔ ካሉበት እና ተፈናቅለው ከተሰደዱበት እንዲመጡ በማድረግ ያለምንም ዝግጅት ለፈተና መቀመጣቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የተቆረጠው ማለፊያ ነጥብ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ እና ችግር ታሳቢ ያላደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሚኒስቴር ለአካባቢው የተወሰነውን የከፍተኛ ትምህርት ማለፊያ ነጥብ #በድጋሜ_በማጤን ማስተካከያ እንዲያደርግ ሲሉ ጠይቀዋል።

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የቤት ውስጥ የመታሰር ጉዳይን አስመልክቶ ለፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤቶች ደብዳቤ ፅፏል። የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቤቱታ የሚያጣሩ ቡድኖች ወደ አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም በመሄድ አቶ ዳውድ ያሉበትን ሁኔታ አጣርተዋል። አጣሪዎቹ በሪፖርታቸው እንዳቀረቡት…
#NewsAlert

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸው ተሰምቷል።

አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ላይ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።

ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር።

ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ መሆኑን በመጥቀስ በሊቀ መንበሩ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል።

ከአቶ ዳውድ የቁም እስር በተጨማሪ በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ።

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ሚካኤል ቦረን እና አዮ ኬነሳ አያና ጭምሮ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አቶ ዳዊት አብደታ እና አቶ ለሚ ቤኛ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ቢቢሲ በዘግባው አመላክቷል።

@tikvahethiopia