TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ UNICEF የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና ግብዓቶች ትግራይ ክልል መዲና መቐለ ገብተው መሰራጨታቸው ዛሬ አሳውቋል።

UNICEF የአስቸኳይ ጊዜ መድሃኒት፣ ምግብና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ የህክምና ግብዓቶች ናቸው መቐለ ደርሰው መሰራጨታቸውን በይፋዊ የትዊተር ገፁ ላይ ገልጿል።

የህክምና ግብዓቶቹ ኣይደር ሆስፒታልን ጨምሮ በክልሉ ተደራሽ ለሆኑ 40 የጤና ተቋማት መሰራጨታቸው ተገልጿል።

በዚህም 100 ሺህ ህፃናት እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም 3,333 የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ህፃናትን ህይወት ለመታደግ ያስችላል ብሏል።

#UNICEFEthiopia

@tikvahethiopia
#MoH

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ፥ በሚኒስቴሩ ስፖንሰርነት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሕክምና ኮሌጆች የስፔሻሊቲ ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች በያሉበት ተቋም የትምህርት ውል የሚገቡ መሆኑን ገለፀ።

የጤና ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ተማሪዎቹን የትምህርት ውል እያስገባ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ የትምህርት ውል ማዋዋሉ በመደበኛ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና ከመፍጠሩ በተጨማሪ በተማሪዎች ላይም ከፍተኛ እንግልት እየፈጠረ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በመሆኑም ተማሪዎቹ በያሉበት ተቋም ውል የሚገቡ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳው ወደፊት ይፋ ይደረጋል ብሏል።

@tikvahuniversity
#የእሳት_አደጋ

ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከአሁን የተከሰቱ የእሳት አደጋዎች፦

#AddisAbaba📍

- በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ሂርቱ ሞጆ ተብሎ በሚጠራው የጥብቅ ደን ውስጥ ለቆሻሻ ተብሎ የተለኮሰ እሳት ባስከተለው አደጋ 200 ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጎማ ተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ አነስተኛ ሆቴል በተከሰተ አደጋ 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት መውድሟል።

- በጉለሌ ክፍለ ከተማ በእፅዋት ማእከል በተነሳ የሰደድ እሳት 10ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት ለውድመት ተዳርጓል።

- በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታ ኮልፌ እፎይታ ገበያ ማዕከል ፊትለፊት በአራት የንግድ ሱቆቸ በሆኑ የጫማ ማምረቻ እና መሸጫ እንዲሁም ጨርቃ ጨርቅ መሸጫ ላይ በደረሰ ድገተኛ የእሳት አደጋ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

- በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል በተባለ አከባቢ በዶልፊን ኢትዮጲያ የሳሙናና ሻምፖ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ1 ሚሊዮን 85 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

- በአዲስ ከ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መሳለሚያ አከባቢ አራት የንግድ ሱቆች ላይ እና ወረዳ 1 መርካቶ አከባቢ 3 ንግድ ሱቆች በተጨማሪም የካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዘፍነሽ ህንፃ አከባቢ በሶስት ንግድ ሱቆች ላይ በደረሱ የእሳት አደጋዎች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወደመ።

- በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ገረጂ ኖክ ማደያ 40/60 ኮንዶሚኒየም 13ኛ ፎቅ ላይ ለኮንስትራክሽን ግብዓት የሚውሉ በደረሰ የእሳት አደጋ የ200 ሺህ ብር ንብረት ወድሟል።

ይቀጥላል👇
TIKVAH-ETHIOPIA
#የእሳት_አደጋ ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከአሁን የተከሰቱ የእሳት አደጋዎች፦ #AddisAbaba📍 - በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ሂርቱ ሞጆ ተብሎ በሚጠራው የጥብቅ ደን ውስጥ ለቆሻሻ ተብሎ የተለኮሰ እሳት ባስከተለው አደጋ 200 ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። - በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጎማ ተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ አነስተኛ ሆቴል በተከሰተ አደጋ 300…
የቀጠለ👇

ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከአሁን የተከሰቱ የእሳት አደጋዎች፦

#AmharaRegion 📍

- በወልድያ በ06 ቀበሌ " ጎልጎታ " ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸው ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ 3 ሰዎችን በቃጠሎ ለቁስለት ዳርጓል።

- በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ በ016 ቀበሌ ልዩ ቦታው ሸንቦቆ ጉጥ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በ29/6/2014 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ላይ በጥንቃቄ ጉድለት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 52 ቤቶችና 1 መስጅድ ሙሉ በሙሉ ከነበራቸው አዘመራጋ በቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ቆለድባ ከተማ 01 ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በመኖርያ ቤቶች እና የንግድ ቦታዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

- በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የሚገኘው የቤላ ተራራ ላይ ከአምስት ቀን በፊት የተነሳ ሰደድ እሳት ከአንድ መቶ ሔክተታር በላይ የሚሸፍን ብዝሐ ህይወት እና የተፈጥሮ ጥብቅ ደን ወድሟል።

ይቀጥላል👇
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለ👇 ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከአሁን የተከሰቱ የእሳት አደጋዎች፦ #AmharaRegion 📍 - በወልድያ በ06 ቀበሌ " ጎልጎታ " ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸው ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ 3 ሰዎችን በቃጠሎ ለቁስለት ዳርጓል። - በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ በ016 ቀበሌ ልዩ ቦታው ሸንቦቆ…
የቀጠለ👇

#SNNPRS📍

- በስልጤ ዞን በ " ዳሎቻ ወረዳ " ውስጥ መንስዔው ባልታወቀ ምክያት በተከሰተ አደጋ የሳር ክዳን ቤቶች ሙሉ በቃጠሎ ወድመዋል፡፡

- በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ " ግርንዚላ ሸፎዴ " ቀበሌ ምክንያቱ ባልታወቀ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ ሶስት ህፃናት ህይወታቸው ስያልፍ ሁለት የሳር ክዳን ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።

- በስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ውስጥ "በጅገና ላሾ ቀበሌ" ቀጠና-2 ጃፈር-1 ልማት ቡድን ምክንያቱ ያልታወቀ የእሳት አደጋ ከ1ሚሊየን 320ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድሟል፡፡ 18 የቤተሰብ አባላትም ተፈናቅለዋል።

- በሀዲያ ዞን በምሻ ወረዳ ኤራ ጌሜዶ ቀበሌ መጋቢት 4 ቀን ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ምክንያት 22 ቤቶች ከነሙሉ ቁሳቁሳቸዉ ወድመዋል። በቃጠሎዉም 11 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል።

- በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ከ1 ቀን በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

#OromiaRegion📍

- በባሌ ብሔራዊ ፓርክ የተነሳ እሳት ለአራት ቀናት ከቆየ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። የእሳቱ መነሻና የደረሰው ጉዳት በግልጽ አልተቀመጠም።

- ትላንት ማታ በጅማ ከተማ 'ቢሺሼ' እየተባለ በሚጠራ አከባቢ በተነሳው የእሳት አደጋ በአከባቢው የሚገኙ የልብስና የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ወድመዋል። የእሳቱ መነሻና ያደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን በውል አልታወቀም።

NB : ከላይ የተዘረዘሩት የእሳት አደጋዎች በ ቲክቫህ ኢትዮጵያ @tikvahethmagazine በኩል ከመላው ሀገሪቱ ክፍል ከየካቲት ወር 2014 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬ ለቤተሰቦቻች የተላኩ መረጃዎች ብቻ ናቸው፤ መረጃዎቹ በመንግስት ተቋማት በኩል አልፈው ሪፖርት የተደረጉ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Russia #Poland #Germany አዲስ አበባ ያለው የሩስያ ኤምባሲ ያሰራጨው መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል፤ በኤምባሲዎች መካከልም ውዝግብ ፈጥሯል። የሩስያ ኤምባሲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጿል። ይህ መልዕክት እየደረሰው ያለው ከገፁ ተከታዮች መሆኑን አመልክቷል። ኤምባሲው " ሀገሮቻችን…
#Ukraine

በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፥ ሩስያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው ወረራ ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍን እና አብሮነት የገለፁትን ተከታዮቹን አንደሚያደንቅ ገልጿል።

" ወዳጆቻችን እናመሰግናለን " ያለው የዩክሬን ኤምባሲ ወረራውን የፈፀመችው ሩስያ በሁሉም ዩክሬናውያን ከተሸነፈች በኃላ ኤምባሲው ቁርጠኛ ለሆኑ የፌስቡክ ወዳጆቹ በሎተሪ ወደ ዩክሬን ከክፍያ ነፃ የመግቢያ ቪዛ ሊሰጥ እያሰበ መሆኑን አሳውቋል።

ኤምባሲው እስከዛሬ ንቁ የሆኑ የፌስቡክ አክቲቪስቶች ብሎ የ38 ሰዎችን (ኢትዮጵያውያን) ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጾ ፤ " ሀገሮቻችን በችግር ጊዜ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደዚህ አይነት ጠንካራ ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፣ ወዳጃዊ ግንኙነት ስላላቸው ኩራት ይሰማናል " ማለቱ አይዘነጋም።

ኢትዮጵያውያን ተከታዮቹ እያሳዩት ላለው ድጋፍና ከሩስያ ጎን እንደሚቆሙ መምረጣቸውን በእጅጉ እንደሚያደንቅ መግለፁ ይታወሳል።

ይህን የሩስያ ኤምባሲ መልዕክት ተከትሎ በአዲስ አበባ የፖላንድ እና የጀርመን ኤምባሲዎች የሩስያን ኤምባሲ የሚቃወም ጠንካራ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
" ዩክሬን በቅርቡ NATOን የምትቀላቀልበት ምንም መንገድ የለም " - ቦሪስ ጆንሰን

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ሀገራቸው ዩክሬን የNATO ወታደራዊ ጥምረትን ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ልታቋርጥ እንደምትችል ሀሳብ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ይህንን ሃሳባቸውን ተከትሎም የብሪታንያው ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ለሚዲያዎች እንደተናገሩት ዩክሬን በቅርቡ NATOን የምትቀላቀልበት ምንም መንገድ እንደሌለ እና ይህም ለሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ግልፅ እንደተደረገ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ወደፊት ግን ውሳኔው ለዩክሬን ዜጎች እና ለተመረጠው መሪዋ (ቮድሚር ዜሌኒስኪ) የተተወ ነው ፤ እኛ ግኝ እንደግፋቸዋለን " ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ዜሌኒስኪ ከሩስያ ጋር የተኩስ አቁም እና ሩስያ ጦሯን ከዩክሬን እንድታስወጣ ለማድረግ ድርድር እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ሩስያ በዩክሬን ላይ ምታካሂደው ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም ከተፈለገ በዋነኝነት ካስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ዩክሬን NATOን እቀላቀላለሁ የምትለውን ሀሳቧን እርግፍ አድርጋ እንድትተው እና ገለልተኝነቷን እድታረጋግጥ የሚል ነው።

ሩስያ፤ ዩክሬን ለሀገሯና ለህዝቧ በምንም መልኩ ስጋት እንደማትሆን እስካላረጋገጠች ጊዜ ድረስ እርምጃዋን እንደምትቀጥል ነው እየገለፀች የምትገኘው።

ዩክሬን የNATO ጥምረትን ለመቀላቀል ለዓመታት ስትታገል ቆይታለች፤ ነገር ግን ይህ እርምጃዋ ሩሲያን በእጅጉ አስቆጥቷታል፤ ሩስያ በአጠገቧ ሌላ የNATO አባል ሀገር ፈፅሞ ማየት አትፈልግም።

[ በሌላ መረጃ ፦ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ነዳጅ ፍለጋ የገልፍ ሃገራትን ጎብኝተዋል። እንደ ስካይ ኒውስ መረጃ ዛሬ በዩኤኡ እና ሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል። ]

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ትላንትና ህ/ተ/ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አሳስቧል። ማሳሰቢያው ከተሰጣቸው ፓርቲዎች መካከል ፦ ብልፅግና፣ ኦፌኮ፣ አብን ፣ ኦነግ ፣ ነእፓ፣ ኦብነግ፣ መኢአድ ይገኙበታል።…
#NEBE

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚህም እስካሁን ጠቅላላ ጉባኤ ያካሄዱ ፓርቲዎች ብልጽግና ፣ ህዳሴ ፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ፣ ጋህነን መሆናቸውን አመልክቷል።

እንደ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ በጊዜ ገደቡ መሰረት ቀን ያሳወቁ 3 ፓርቲዎች አሉ።

ቦርድ 12 ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ ጠይቀው ምላሽ የሰጣቸው መሆኑንም አሳውቋል።

ከእነዚህ መካከል ፦ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ አንዱ ሲሆን ለጉባኤው አስፈላጊ የሆኑ የፋይናንስና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች አስቻይ ባለመሆናቸው ገልጾ መጋቢት 18 ቀን 2014 እንዲያካሂድ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፓርቲው አባላቶች በእስር ላይ ስለሚገኙ፣ የፓርቲው የክልል ጽህፈት ቤቶች ተዘግተው ስለሚገኙ፣ በግጭቶች ምክንያት በበርካታ የኦሮምያ ዞኖች እና ሌሎ ች ክልሎች ውስጥ ያለው ሁኔታ ያልተረጋጋ ስለሆነ በሚል አቤቱታ አቅርቦ መጋቢት 17 እና 18/2014 ዓ/ም እንዲያካሂድ ቦርዱ ፈቅዶለታል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ/ም እንዲያካሂድ ጠይቆ ቦርዱ ፈቅዶለታል።

4 ፓርቲዎች ደግሞ በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ባለው ከፍተኛ የጸጥታ ችግር የተነሳ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እንደማይችሉ ጠቅሰው ቦርዱ ፈቅዶላቸዋል ከእነዚህም መካከል ዓረና ፓርቲ ይገኝበታል።

3 ፓርቲዎች ደግሞ ለቦርዱ የማራዘም ጥያቄ አቅርበው ውሳኔ ያልተሰጠባቸው እና ምክንያታቸው እየታየ ያለ ሲሆን ፓርቲዎቹ ፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ናቸው።

ሙሉውን ያንብቡ telegra.ph/NEBE-03-16

@tikvahethiopia
#MoE

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የተባለ ሲሆን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሚኒስቴሩ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia