TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... ሁሉም ወገን ቀውስን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅቦ ግጭቱን ለመፍታት ሁልንተናዊ የሰላም መንገዶችን ሊጠቀም ይገባል " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ 🇪🇹 ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዩክሬን ቀውስ ውስጥ ሁሉም ወገኖች ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዩክሬን ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት " ኢትዮጵያ በቅርቡ ካለፈችበት ጦርነት ተነስታ ስለ ጦርነት ጉዳት የምታካፍለው ሰፊ ልምድ አላት " ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥ " የኢትዮጵያ ልምድ ጦርነት ቤተሰብን ፣ ማህበረሰብ ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚን ክፉኛ የሚጎዳ፣ አጥፊ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ጦርነት የሚያደርሰውን ቁሳዊ ጉዳት መጠገን ቢቻልም በማህበረሰብ ላይ ጥሎት የሚያልፈውን ጠባሳ ግን ለማከም ከባድ መሆኑን አመልክተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " ኢትዮጵያ #የዩክሬን ወቅታዊ ቀውስ በቅርበት እየተከታተለች ነው " ያሉ ሲሆን ግጭቱን የሚያባብሱ ሁኔታዎች እንደሚያሳስባት ገልፀዋል።

ሁሉም ወገኖች ቀውስን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅበው ግጭቱን ለመፍታት ሁልንተናዊ የሰላም መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።

በአካባቢው ላይ #ሰላም እንዲሰፍን ያላቸውን ምኞት መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia