#TsehaiFamiles
ለወላጆች 'ፀሐይ ለቤተሰብ' የተሰኘ የኦላይን ትምህርት መስጫ ፕላትፎርም ይፋ ሆነ።
ዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ ፀሐይ ለቤተሰብ https://www.t4f.et የተሰኘ አዲስ የቤተሰብ የኦላይን ትምህርት መስጫ ፕላትፎርም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ አስተዋውቋል።
ፀሐይ መማር ትወዳለች በተሰኘው የሕጻናት ፕሮግራሙ የሚታወቀው ዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ በኢትዮጵያዊቷ እንስት በብሩክታዊት ጥጋቡ ከ17 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ነው።
በዛሬው ዕለት አዲስ የተዋወቀው ፕሮግራም ቤተሰቦች ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው ትምህርት የሚያገኙበት ሲሆን በፕላትፎርሙ ከሚሰጠው ትምህርት በተጨማሪ ምዘናዎችንም ያካተተ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
በተለይ እድሜያቸው ከዜሮ ዓመት እስከ 7 ዓመት ለሆኑ ህጻናት የቤተሰቦች አስተዳደግ ላይ ሥልጠና ይሰጣል የተባለው ይህ ፕላትፎርም በነጻ እንዲሁም በክፍያ ያሉ ሥልጠናዎችን አካቷል።
ዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ ከዚህ በተጨማሪ ጥበብ ለሴቶች እንዲሁም ወጣቶቹ ተመራማሪዎች የተሰኙ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ያካተተ ሲሆን በመሰረታዊነት ሕጻናትና ቤተሰብ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይሰራል።
@tikvahethiopia