#እንኳን_ለዐቢይ_ጾም_አደረሳችሁ !
ቅዱስ ፓትርያርኩ ዐቢይ ጾምን በማስመልከት ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን አባታዊ መልዕክት አስተላለፉ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖት የዐቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው ዛሬ የካቲት 18/2014 ዓ.ም ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልዕክታቸው ፥ " በመዋዕለ ጾሙ ስለ ሀገርና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ፣ ስለ ሕዝባችን ዘላቂ ፍቅርና ስምምነት አጥብቀን እንድንጸልይ ፣ እንደዚሁም በግጭቱና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖቻችን ካለን በማካፈል የችግሮቻቸው ተካፋይ እንድንሆን ከዚህም ጋር ለሀገራዊ ሰላም እና ፍቅር መሳካት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ መዋዕለ ጾሙን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን " ብለዋል።
* የመልዕክቱ ሙሉ ቃል ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia