TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሚዲያ የምናፍንበት ፤ ኢንተርኔት የምንዘጋበት ዘመን ድሮ አልፏል፤ ኬንያ ብዙ ርቀት ተጉዛለች " - ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ

በኬንያ የኑሮ ውድነት መባባስን እንዲሁም የምርጫ ኮሚሽን በአዲስ መልክ የማዋቀር ሂደትን ተከትሎ በኬንያ ባለፉት ሳምንታት ተቃውሞ መነሳቱ ይታወሳል።

በዚህም የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ራይላ ኦዲንጋ በሳምንት ሁለት ቀን ሰኞ እና ሐሙስ በመላው አገሪቱ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈው ነበር።

ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ መራዘሙ ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ይደረጋል የተባለው ተቃውሞው እንዲቀርና ለውይይት በር እንዲከፈት ከጠየቁ በኋላ የተቃዋሚ መሪው ኦዲንጋ በሰጡት መግለጫ ፥ " ተቃውሞውን የሰረዝነው የፕሬዝዳንቱን ጥሪ ተከትሎ ‘ለንግግር ቦታ እንስጥ’ በሚል ነው " ብለዋል።

የሀገሪቱ የሚዲያ ማኅበራት ጥምረት ምን አለ ?

ከ17 የሚዲያ ማኅበራት የተወጣጣው የሚዲያ ማኅበራት ጥምረት ቀደም ብሎ ዛሬ ይደረጋል ተብሎ የታቀደውን ተቃውሞ ተከትሎ ሚዲያዎችን የመዝጋትና ኢንተርኔትን የማቋረጥ እቅድ መኖሩን ገልጾ ነበር።

የኬንያ አርታኢዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ቸርችል ኦቲኖ ፖሊስ ሰልፉን በሚዘግቡ ጋዜጠኞች ላይ ጥቃት ካደረሰ እና መሳሪያዎቻቸውን ካወደመ በሚመጣው ረቡዕ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ገልጿል።

አክሎም ሁሉም ተዋናዮች ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

ባለፈው ሐሙስ በነበረ ተቃውሞ ወደ 20 የሚሆኑ ጥቃቶች ሪፖርት መደረጋቸውን ያስታወቀው ጥምረቱ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቋል።

በሂደቱ ላይ መግለጫ እንዲሰጥ የ7 ቀን ቀነ ቀጠሮ አስቀምጧል።

ጉዳት የደረሰባቸው የሚዲያ ተቀማትና ጋዜጠኞች የህክምና ወጪያቸው እንዲሸፈን፤ ካሳ እንዲከፈላቸው ጥምረቱ መንግስትን ጠይቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሚዲያዎች ጋዜጠኞችን ከማሰማራታቸው በፊት ግልጽ የደህንነት እና የጥበቃ ፕሮቶኮሎች መኖራቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቋል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ትላንት በነበራቸው መግለጫ ከሚዲያ ጋር ተያይዞ ምን አሉ?

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በምሽቱ መግለጫቸው መንግስታቸው ሚዲያዎችን እንደማይዘጋና #የሚዲያ_ነጻነትን እንደሚያከብር ተናግረዋል።

" ሚዲያ የምናፍንበት ኢንተርኔት የምንዘጋበት ዘመን ድሮ አልፏል፤ ኬንያ ብዙ ርቀት ተጉዛለች። ተግባሩን እንዲፈጽም የሚዲያ ነጻነትን እናከብራለን፤ ምንም በኛ ላይ የተዛባ ምልከታ ቢኖራችሁም የእኛ ፍጹም ድጋፍ አላችሁ። እናንተ ግን እኔ በቆምኩበት ቦታ ብትቆሙ ሚዲያዎችን ትዘጉ ነበር፤ ይህ ግን አይሆንም " ብለዋል።

Credit : The Standard

More 👉 @tikvahethmagazine