TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
June 21, 2019
December 5, 2020
February 22, 2021
TIKVAH-ETHIOPIA
The_Massacre_of_Axum_-_AFR_25.3730.2021.pdf
ትግራይ አክሱም ፅዮን ቅድት ማሪያም ቤተ ክስርቲያን ውስጥ 750 ሰዎች ተገድለዋል ?

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማህበራዊ ሚዲያ በአክሱም ጽዮን ያለውን ጽላት የኤርትራ ወታደሮች ለመውሰድ ሲሞክሩ በተፈጠረ ግርግር የሰው ህይወት ጠፍቷል በሚል ሲሰራጭ የነበረውን መረጃ የሚያረጋግጥ መረጃ እንዳላገኘ ለቢቢሲ አሳውቋል።

ነገር ግን ኅዳር 19 እና 20 ቀን 2013 ዓ/ም በአክሱም አስከፊ የተባለ ጭፍጨፋ መካሄዱን አረጋግጫለሁ ብሏል።

እንደ አምነስቲ ገለፃ ኅዳር 19 የተወሰኑ የህወሓት ሚሊሻዎች አክሱም ጽዮን ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ካለች አንድ ተራራ ወይም ጉብታ ላይ ወደ ኤርትራ ወታደሮች ላይ በከፈቱት ተኩስ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር።

ይህ ካበቃ በኋላ እዛው የነበረው የኤርትራ ሠራዊት ሌላ ተጨማሪ ኃይል እና የጦር መሳሪያ ተጨምሮ (ታንኮችን ጭምር) ጥቃት ሰነዘሩ። በመንገድ ላይ ያገኙትን እና በየቤቱ እያገቡ ያገኙትን ጎረምሳ ወንዶች ሲገድሉ እደነበረ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ብሏል ተቋሙ።

በማግስቱ ህዳር 20 ይህ ድርጊት ቀጥሎ ነበር የሚለው አምነስቲ አስከሬን ማንሳንትም አይቻልም ነበር ፤ ኅዳር 21 2013 ዓ.ም. በአክሱም ጽዮን ክብረ በዓል ዕለት ነው እንዲቀበሩ የተደፈቀደው ብሏል።

አምነስቲ በ21 ትልቅ ግድያ እንደነበረ የሚያስረዳ ነገር የለም ፤ ይልቁንም አስከሬን መቅበር የተጀመረውም በእዛው ዕለት ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎችን ውድቅ የሚያደርግ መረጃ ሰጥቷል።

#AmnestyInternational #Ethiopia #Tigray #Axum

https://telegra.ph/Amnesty-International-02-26-2
February 26, 2021
October 3, 2023
October 12, 2023
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum #EthiopianAirlines የአክሱም ኤርፖርትን ለመጠገን የእቃዎች ግዥ መጀመሩ ተነግሯል። ትግራይ ባስተናገደችው አስከፊው ጦርነት ወቅት ክፉኛ የወደመው የአክሱም ኤርፖርት እስካሁን ተጠግኖ ወደስራ አልተመለሰም። የአክሱም ህዝብ ኤርፖርቱ ባለመጠገኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ነው። በተለይም የተለያዩ አልባሳትን፣ ባህላዊ ጌጦችን እያዘጋጁ የሚሸጡ፣ ከቱሪዝም ገቢ የሚያገኙ ወገኖች ኤርፖርቱ…
November 28, 2023
December 2, 2023
February 24, 2024
April 1, 2024
TIKVAH-ETHIOPIA
#አክሱምኤርፖርት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ ለማደስ በጨረታ ላሸነፈው የኮንስትራክሽን ድርጅት ይፋዊ የርክክብ ስነ-ሰርዓት አላካሄደም ተብሏል። ይህ ሁኔታ ደግሞ የእድሳት ሰራው በፍጥነት በሙሉ አቅም እንዳይሰራና እንዲዘገይ ምክንያት እየሆነ ነው በሚል ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል። መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር…
May 9, 2024
May 18, 2024
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰኔ 2016 ዓ/ም ወደ ትግራይ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀመር መግለጹን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በትግራይ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በደረሰበት ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። በቅርቡ ግን አውሮፕላን ማረፊያው መልሶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ…
May 25, 2024
June 3, 2024