TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Dr. Tilaye...

"Congratulations to all Grade 12 students on your big academic achievement. As we are receiving complains on your Scholastic Aptitude Test result, #NEAEA will give it a second look and get back to you. Thank you for your patience. Wishing all the best!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEAEA

ትላንት የ2012 ዓ/ም ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

የፈተናው ውጤት በተመለከተ አንዳንድ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ቅሬታ እንዳላቸው እየገለፁ ሲሆን ይህንን ቅሬታም የሚመለከተው አካላ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

ቅሬታ ማስተናገጃ መድረክም እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም በክልል ያሉ ነዋሪዎች።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን አስመልክቶ ቅሬታ ካላቸው/አቤቱታ ካላቸው ከሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ አሳውቋል።

በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት ደጃፍ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ ግን በክልል ያሉ ነዋሪዎች እንዴት ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ያለው ነገር የለም ፤ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEAEA

የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አይደለም ተብሏል።

ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ ገና #አለመወሰኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity አረጋግጧል።

የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን አሁንም ገና እንዳልተወሰነ ገልፀዋል።

ኤጀንሲው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ሲደረስ ይፋዊ የሆነ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

Tikvah-University t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#NEAEA

" ... አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ( የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ) ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም፤ የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም " - አቶ ተፈራ ፈይሳ

በሁለተኛው ዙር የሀገር አቀፍ ፈተና በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተና ላይ መቀመጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ፈተናቸውን ወስደዋል።

በአጠቃላይ በአማራ፣ አፋር፣ኦሮሙያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከ60 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና ወስደዋል።

ፈተናውም የወሰዱ ተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች " ተፈታኞች ያሳለፉትን የስነልቦ ጫና እና አስቸጋሪ ሁኔታ ከግምት ያስገባ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ሊኖር " ይገባል እያሉ ይገኛሉ።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክታ ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ይህንን የመወሰን ስልጣን የኤጀንሲው እንዳልሆነ ገልፀዋል።

አቶ ተፈራ ፈይሳ ፥ " ... ያሉ ጥያቄዎች አሉ፤ ይሄን ኤጀንሲው አሁን ላይ የሚለውም ምንም ነገር የለም። በዚህ ደረጃ ኤጀንሲው አይወስንም ፤ ይህ ትልቅ ጉዳይ ስለሆነ። ዞሮ ዞሮ ችግሩ እንዳለ እንረዳለን። ችግሩን ለመፍታት እኛ የተወሰነ ጊዜ ከመስጠት ባሻገር አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም። ...ይሄን የሚወስነው መንግስት ነው "

በሌላ በኩል ፤ ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ካሉ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ የታሰበ ነገር ያለ እንደሆነ ከሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት አቶ ተፈራ ፥ " በእኛ በኩል የሚፈታ አይደለም። ከአጠቃላይ ከሀገራዊ ፀጥታ ጋር የሚታይ ስለሆነ ሀገራዊ ፀጥታው ሲረጋገጥ ፣ ትግራይም እንደማንኛውም ክልል ሰላም ሲሆን ፈተና የምንፈትነው " ሲሉ መልሰዋል።

#MesfinArageVOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NEAEA

" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " - አቶ ተፈራ ፈይሳ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ ሰዓት ጀምሮ ከተማሪ ወላጆች እንዲሁም ከተማሪዎች በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውን ተመልክተናል።

ከጥያቄዎቹ መካከል ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብቶ ለመማር የተላለፈው 50% ማስመዝገብ ውሳኔ ከነበርንበት ሁኔታ አንፃር፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጦርነቱ ጫና ተዳምሮ ትክልል አይደልም ይህ ሊታይ ይገባል የሚል ነበር።

የተላኩትን ቅሬታዎች በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አቅርቦ ምላሽ አግኝቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ " ማንኛውም ተማሪ ብሔራዊ ፈተናውን ለማለፍ ቢያንስ 50 በመቶ ውጤት ሊያመጣ እንደሚገባ " ገልጸውልናል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች አጠቃላይ አማካይ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። " ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ " ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " ብለዋል።

ከተማሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እየተቀበሉ መሆኑን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ፤ አጠቃላይ አማካይ ውጤታቸው ከ300 በታች ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር ገና አለመታወቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ የመግቢያ ነጥብ ወደፊት በትምህርት ሚኒስቴር የሚገለጽ መሆኑም ታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity