TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WaraJarso

የወረ ጃርሶ ወረዳ ነዋሪዎች በታጣቂዎች እንቅስቃሴ ሰላማቸውን እንዳጡ መግለፅ ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ የተነገረላቸው በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ።

ከወረዳ እስከ ዞን ከፍ ሲል እስከ ክልሉ መንግስት ድረስ ለአካባቢው መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ አቤቱታ ቢቀርብም ተጨባጭ ለውጥ ሊመጣ አልቻለም።

ከሳምንታት በፊትም አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት የፌዴራል መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው አቤቱታቸውን አሰምተዋል።

አርሶ አደሮች በነፃነት ለመግባትና ለመውጣት ስጋት አለን ፤ ሰዎች ይታፈናሉ፣ ደክመን የዘራነው እህል በግፍ ይቃጠላል ፣ ሌሎችም ህገወጥ እንቅስቃሴ ይደረጋል ከዚህ አለፍ ሲል የወረዳው ከተማ ጎሃፅዮን/ቀሬጎዋ/ውስጥ ቀን ቀን የመንግስት አካላት እንደሚያስተዳር ማታ ደግሞ ታጣቂ ቡድኑ እንደሚንቀሳቀስ ቀን ላይ ግን እንደማይታይ ይገልፃሉ፤ ሁኔታው ግራ የሚያጋባ እና እጅግ ትልቅ ችግር መሆኑንም አመልክተዋል።

በዚህ ወርም የወረጃርሶ ወረዳ የአርሶ አደሮች እህል ሲቃጠሉ የሚያስዩ ፎቶዎች በማጋራት፣ በአካባቢው ዝርፊያ፣የንብረት ማውደም እየደረሰና ለዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ሸኔ መሆኑን ገልጾ ነበር።

ከሳምንታት በፊት በብሄራዊ ቴሌቪዥ ጣቢያ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ቢሮ የሸኔ እንቅስቃሴ ከክልሉ በላይ እንዳልሆነ በቡድኑ ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በወረ ጃርሶ አካባቢ የቀሩ ካሉ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ ተናግሮ ነበር።

በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ሞት፣ ለዓመታት ያህል አንዳች ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሄ ሳይገኝ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል።

@tikvahethiopia