TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቴዲ ማንጁስ‼️

በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት አቶ #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ላይ ዐቃቤ ህግ የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ጠየቀ።

መርማሪ ፖሊስ በአቶ ቴዎድሮስ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ምርምራ አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ትላንት ለዐቃቤ ህግ አስረክቧል።

ዐቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት እንደገለጸው፤ ተጠርጣሪው አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ ባላቸው የህትመት ድርጅት ከኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና ከሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር የመማሪያ መጻህፍትን ለማተም ውል ፈጽመው እንደነበረ ገልጿል።

ሆኖም ተጠርጣሪው ከኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጋር በመመሳጠር በውሉ መሰረት መጽሐፉን ሳያስረክቡ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ቅድሚያ ክፍያ እንደተከፈላቸው ዐቃቤ ህግ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዚህ መሠረት አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ በመንግስትና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ዐቃቤ ህግ አስረድቷል። 

የተፈጸመው ወንጀል ውስብስብና ከባድ ከመሆኑም በላይ የተፈጸመው ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ስለሆነ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎችን አሳባስቦ በማጠናቀቅ በቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ክስ ለመመስረት  የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ግለሰቡ የተጠረጠሩብት ወንጀል ከባድ የሙስና ወንጀል ሲሆን የዋስትና መብት የሚያስከለክል በመሆኑ የተጠርጣሪው የዋስትና መብት ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግለት ዐቃቤ ህግ ችሎቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ የህትመት ድርጅታቸው ለሰባት ወራት መታገዱንና ድርጅቱ መዘረፉን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

የፍርድ ቤት እገዳ ሳይኖር ድርጅታቸው መታገድ እንደሌለበት ያመለከቱት አቶ ቴዎድሮስ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የህትመት ስራ አሰርቷቸው 7 ሚሊዮን ብር እንዳልተከፈላቸውም ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል ፍርድ ቤት የታገደው የአቶ ቴዎድሮስ የህትመት ድርጅት ፖሊስ ለተጠርጣሪው ማሳወቅ እንደነበረበት የገለጸው ችሎቱ ከዚህ በኋላም ተጠርጣሪው ማወቅ የሚገባቸውን መረጃዎች ፖሊስ በወቅቱ እንዲያሳውቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በተጠየቀው የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ በሌላ መዝገብ  ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በጅግጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ የተጠርጣሪው ጠበቃ የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አመዛዝኖ የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ መጠየቁ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም ከተጠርጣሪው ጠበቃ የቀረበውን የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪው በ80 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ አቶ ቴዎድሮስ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው በመሆኑ ከእስር #አልተፈቱም

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

በተለያዩ የምርመራ መዝገቦች በሽብር ትጠረጠራላችሁ በሚል ለወራት በእስር ላይ ሆነው ምርመራ ሲደረግባቸው የቆዩ ሰዎች ዛሬ ከእስር ተፈተዋል፡፡ እስረኞቹ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አባላት፣ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አመራሮች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ከሰኔ 15 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተያያዘ ተጠርጥራችኋል በሚል ታስረው የነበሩ ይገኙበታል፡፡

ከተፈቱት መካከል፦

1ኛ) አንተነህ ስለሺ
2ኛ) ንጉሡ ይልቃል
3ኛ) ዮናስ አሰፋ
4ኛ) ሽገዛ ሙሉጌታ
5ኛ) በዕውቀቱ በላቸው
6ኛ) ኤልያስ ገብሩ
7ኛ) መርከቡ ኃይሌ
8ኛ) ስንታየሁ ቸኮል
9ኛ) ወ/ሮ ደስታ አሰፋ
10ኛ) ምስጋና ጌታቸው
11ኛ) ጌታቸው አምባቸው
12ኛ) ሲያምር ጌቴ

እና ሌሎችም እንደሚገኙበት የታወቀ ሲሆን፣ የአብን ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ በለጠ ካሳ #አልተፈቱም

Via #ASRATTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia