TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን⬇️

በቡራዩና በመዲናዋ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የተከሰቱ #ግጭቶች ላይ የደረሱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ቡድን #ከዛሬ ጀምሮ መሰማራቱን የኢትዮጰያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ይህንን ያለው በዛሬው ዕለት ግጭቱን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኀን በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።

በመግለጫው ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር እንደተናገሩት በደረሰው ግጭት በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን አንስተዋል።

ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለ #ለከፋ ጉዳት ያደርሳል ያሉት ኮሚሽነሩ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም እና ተዘዋውሮ የመስራት እንዲሁም በሰላም የመኖር መብቶችን ለማስከበር ጠንከር ብሎ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ እስከ አሁን የደረሰውን ጉዳት መንስዔ፣ ጉዳት እና ስፋት አጣርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሪፖርት በማድረግ ያጠፉ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋልም ተብሏል።

በተለያዩ ቦታዎችም የተከሰተውን ግጭት እንዲረጋጋ ከመንግስት ጋር እየሰራ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በመግለጫው የፌደራል እና የክልል #ጸጥታ አካላትም ሚናቸውን #በአግባቡ እንዲወጡ አሳስቧል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ🔝

ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች #የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አሕመድ ተናግረዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ትልልቅ #ሐሳብ ላላቸው ሳይሆን ትልልቀቅ #ሀብት ላላቸው ብቻ ከፍተኛ የብድር አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች፤ በዚህም የሚፈለገው ለውጥ ሳይመዘገብ ቀርቷል፡፡ ይህንን ችግር በመረዳትም ለተማሩ ዜጎች ሐሳባቸውን በማዬት ብድር ለመስጠት እንዲቻል ፖሊሲዎች እንደሚመቻቹና አነስተኛና መካከለኛ ባለሀብቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በዓለም ባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ መለኪያ መሠረት ኢትዮጵያ 159ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ 5 ዓመታት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ #በማሻሻል በመለኪያው ከ100 በታች ለማድረግ በእርሳቸው የሚመሩ 10 ተቋማት ተለይተው ወደ ለውጥ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የአሠራር ፖሊሲዎች፣ የሕግ ማዕቀፎች እና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት በተቃርኖ የተሞላ አሠራርን መከተላቸው ኢትዮጵያ በቀላሉ ሥራ (ቢዝነስ) የማይሠራባት ሀገር እንድትሆን ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ወር ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ #የሚመራው እና 10 ተቋትን ያካተተው ልዩ ኮሚቴ (ስትሪንግ ኮሚቴ) አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግ የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች በየወሩ የውጤት ግምገማ እያደረገ ይገኛል፡፡

ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ዕድገት እንዲመዘገብ ‹‹ያለንን የተፈጥሮ ሀብት #በአግባቡ መጠቀምና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ አዳዲስ ሐሳብ፣ ዕውቀትና ክሕሎትን በተቀናጀ መልኩ አሟጦ መጠቀም ይጠይቃል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

እስካሁን ያለው አካሄድ በተቃርኖ የተሞላ፣ ዘመናዊ አሠራርን ያልተከተለ፣ ተወዳዳሪነት የሌለውና በአነስተኛ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎችን በቀላሉ የማይጠቅም በመሆኑ ውጤት ማምጣት እንዳልቻለም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት፡፡ ለዚህ ደግሞ ውስብስብ የሆነ አካሄድን መጠቀምና የገንዘብ አቅርቦት ችግር ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከችግሩ ለመውጣት የአሠራር ሥርዓትን ማቅለል፣ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ማድረግና ምቹ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ ነው ያብራሩት፡፡

ለሥራዎች ገንዘብ የማቅረብ ሂደቱን ቀላል ማድረግ፤ እስካሁን ቋሚ ንብረት ይያዝ የነበረበትን የባንኮች አሠራር በቀጣይ ሐሳብን በማስያዝ ወጣቶች ብድር የሚወስዱበት ሁኔታ እንዲፈጥር ማድረግና የግል ተቋማት ውስጥ በቀላሉ ወደ ሥራ ተገብቶ ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡

‹‹በአዲስ ዕውቀትና ሐሳብ ዕድገታችን ማስቀጠል አለብን፤ ለዚህ መንግሥት ማድረግ የሚገባውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለግል ዘርፍ መስጠት አለበት፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ቀላልና ሳይንሳዊ የሆነ የአሠራር ሥርዓትን መዘርጋት ይገባል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር ዐብይ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹አይቻልም›› ወይም ‹‹ሕጉ አይፈቅድም›› የሚሉ አመለካከቶችን በመስበር ሁሉም ተቋማት ለሀገር ሲሉ ቀና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ጅምሮቹ ወደ ውጤት እንዲያድጉ አሁንም ተቋማት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸውም መክረዋል፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያለፈው አንድ ወር አፈጻጸም ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔹" ችግር ላይ ላለዉ መምህር ተገቢ ያልሆነ መልስ ነው የተሰጠን " - መምህራን 🔸 " ችግሩን ለመፍታት መግባባት ላይ ተደርሶ ወደስራ የሚያስገቡ እንቅስቃሴዎች አሉ ፤  ከሰኞ ጀምሮ ወደአካባቢዉ እናቀናለን " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሃዲያ ዞን የባዳዋቾ ወረዳና የሾኔ ከተማ ትምህርት ቤቶች አሁንም አለመከፈታቸዉ ተሰምቷል። በባዳቾች ወረዳና ሾኔ ከተማ…
" ቃል የተገባልን ውዝፍ ደመወዛችን ስላልተከፈለን እዳችን መክፈል አልቻልንም " -  የባድዋቾ ወረዳና የሾኔ  መምህራንና የጤና ባለሙያዎች

በሀድያ ዞን ባድዋቾ ወረዳና ሾኔ ከተማ በደሞዝ ምክኒያት ተቋርጦ የነበረዉ የትምህርትና ህክምና አገልግሎት ቢጀምርም መንግስት ቃል የገባልን ውዝፍ የደሞዝና የዱቲ ክፍያዎች አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

በመምህራን በኩል " ከዞኑ የትምህርት አመራሮች ጋር በተደረሰ መግባባት ያልተከፈሉ ወራቶች ቀስ በቀስ ሊከፈለን ተስማምተን ብንጀምርም እየተከፈለን ያለዉ ስራ ከጀመርንበት ወዲህ ያለዉ ብቻ  በመሆኑ ደሞዝ በቆመባቸው ወራት የገባነዉን እዳ መክፈል አልቻልነም " ሲሉ መምህራን ያለቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸዉን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሾኔ ከተማ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር አቶ ከበደ መሊሶ የመማር ማስተማር ስራዉ አሁን ላይ #በአግባቡ እየተካሄደና ደሞዝ እየተከፈለ ቢሆንም የመምህራን የተጠራቀመ ደሞዝ ከተለያዩ ገቢዎች ተሰብስቦ እንደሚከፈል ቃል በተገባዉ መሰረት አልተከፈለም በማለት የመምህራኑ ቅሬታ ትክክል መሆኑን አረጋግጠዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም።

በሌላ በኩል " ቀሪ ደሞዛችንና የዲውቲ ክፍያዎች አልተከፈለንም  " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

" መንግስት ቀሪ ያልተከፈለ ደመወዛችንን ከ2012 ዓ/ም  ጀምሮ የተሰበሰቡ ዱቲዎች ድረስ ሊከፍለን ይገባል " ሲሉም ጠይቀዋል።

በዚህም ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሾኔ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ተድላ አካሉን ጠይቋን።

ዶክተር ተድላ ፤ የህክምና ባለሙያዎች ቅሬታ ተገቢ መሆኑንና ችግሩ መኖሩን አረጋግጠዋል።

በበኩላቸዉ ከ2012 ጀምሮ የተጓተተ የዱቲ ክፍያን ጨምሮ የሰራተኛ ማትጊያ ተጨማሪ ክፍያዎችን ለመክፈል ከሀድያ ልማት ማህበር ጋር እየተመካከሩ መሆኑን ገልጸዉ የዘገየዉ የዚህ ወር ደሞዝም በፍጥነት እንዲከፈል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia