#WaraJarso
የወረ ጃርሶ ወረዳ ነዋሪዎች በታጣቂዎች እንቅስቃሴ ሰላማቸውን እንዳጡ መግለፅ ከጀመሩ ሰነባብተዋል።
በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ የተነገረላቸው በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ።
ከወረዳ እስከ ዞን ከፍ ሲል እስከ ክልሉ መንግስት ድረስ ለአካባቢው መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ አቤቱታ ቢቀርብም ተጨባጭ ለውጥ ሊመጣ አልቻለም።
ከሳምንታት በፊትም አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት የፌዴራል መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው አቤቱታቸውን አሰምተዋል።
አርሶ አደሮች በነፃነት ለመግባትና ለመውጣት ስጋት አለን ፤ ሰዎች ይታፈናሉ፣ ደክመን የዘራነው እህል በግፍ ይቃጠላል ፣ ሌሎችም ህገወጥ እንቅስቃሴ ይደረጋል ከዚህ አለፍ ሲል የወረዳው ከተማ ጎሃፅዮን/ቀሬጎዋ/ውስጥ ቀን ቀን የመንግስት አካላት እንደሚያስተዳር ማታ ደግሞ ታጣቂ ቡድኑ እንደሚንቀሳቀስ ቀን ላይ ግን እንደማይታይ ይገልፃሉ፤ ሁኔታው ግራ የሚያጋባ እና እጅግ ትልቅ ችግር መሆኑንም አመልክተዋል።
በዚህ ወርም የወረጃርሶ ወረዳ የአርሶ አደሮች እህል ሲቃጠሉ የሚያስዩ ፎቶዎች በማጋራት፣ በአካባቢው ዝርፊያ፣የንብረት ማውደም እየደረሰና ለዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ሸኔ መሆኑን ገልጾ ነበር።
ከሳምንታት በፊት በብሄራዊ ቴሌቪዥ ጣቢያ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ቢሮ የሸኔ እንቅስቃሴ ከክልሉ በላይ እንዳልሆነ በቡድኑ ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በወረ ጃርሶ አካባቢ የቀሩ ካሉ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ ተናግሮ ነበር።
በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ሞት፣ ለዓመታት ያህል አንዳች ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሄ ሳይገኝ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል።
@tikvahethiopia

#PLAZAPREMIUM #NHY
ብፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕ እና ኤን.ኤች.ዋይ የሽርክና አጋርነት ስምምነት አደረጉ፡፡
ስምምነቱ በአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዋና መዳረሻ በሆነው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያለውን የተጓዦች አቀባበል እና የላውንጅ አገልግሎት ደረጃን እንደሚያሳድግ እምነት የተጣለበት ነው።
ፕላዛ ፕሪሚየም ላውንጅ ኢትዮጵያ ፤ በያዝነው አመት መጋቢት ወር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተርሚናል 2 የሚከፈት ይሆናል፡፡
በአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ቀዳሚ መዳረሻ የሆነው አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በየአመቱ ከ12 ሚሊዮን በላይ ተሳፋሪዎችን ያስተናገዳል፡፡
ይህ አዲስ የተመሰረተ የሽርክና አጋርነት የፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕን የ24 ዓመታት የላቀ ልምድ እና የኤን.ኤች.ዋይን የሀገር ውስጥ የእንግዳ መስተንግዶ ልምድ በማዋሃድ በአየር ማረፊያ ውስጥ ያለውን የመንገደኞች አቀባበል እና የላውንጅ አገልግሎት ደረጃን የበለጠ ለማዘመን ያለመ ነው፡፡
በ1000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ፕላዛ ፕሪሚየም ላውንጅ ኢትዮጵያ፤ በአንድ ጊዜ ለ325 እንግዶች አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ መስተንግዶ ለመስጠት እንዲያስችል ታልሞ የተደራጀ ነው።
* ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USAIDEthiopia
የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር የሆኑት ሼን ጆንስ በባህር ዳር ከተማ ተዘጋጅቶ በነበረ ዝግጅት ላይ በአማራ ክልል ከ500,000 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ነዋይ ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርገዋል።
ለዚሁ ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበ ሲሆን ሁለቱም የመማዕለ ነዋይ ፕሮጀክቶች በቀጥታ በገንዘብ ሚኒስቴር የሚመራውን PSNP5 ይደግፋሉ ተብሏል።
የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ከጥቂት ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል ከ400ሺ በላይ ሰዎችን ኑሮ ሊያሻሽል የሚችል በ10.2 ቢሊዮን ብር ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።

#Oromia #Borana📍
" የድርቁ ሁኔታ ምንም መሻሻል አላሳየም " - የቦረና ዞን የግብርና ፅ/ቤት
• በድርቁ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ከብቶች አልቀዋል።
• ወደ 262 ሺ ከብቶች ሞተዋል።
• 280 ሺህ በላይ ከብቶች በሰው ጉልበት ነው የሚነሱት።
የቦረና ዞን የግብርና ፅ/ቤት የእንሳት ሃብት ልማት አስተባባሪ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ በቦረና ያለው የድርቅ ሁኔታ ምንም መሻሻል እንዳላሳየ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ፥ " የተለያየ ድጋፍ ቢደረግም ሁኔታው እንደዛው ነው እየቀጠለ ያለው። ስለዚህ የድርቁ ሁኔታ ሄዶ ሄዶ መሃሉንም አልፎ ወደ መጨረሻ አካባቢ ነው ያለነው " ብለዋል።
በድርቁ ምክንያት ወደ 262 ሺ ከብቶች የሞቱ ሲሆን ወደ 280 ሺህ በላይ ከብቶች በሰው ጉልበት ነው ከመሬት የሚነሱት ሲሉ አክለዋል።
በግምት ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ከብቶችን ቦረና ዞን አጥቷል።
ዶክተር ቃሲም ጉዮ በድርቁ ምክንያት የምግብ እጥረት ማጋጠሙን የገለፁ ሲሆን ለህበረተሰቡ ሆነ ለእንስሳት ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እየተደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በድርቅ ከብቶቻቸው ያለቁባቸው የዞኑ ነዋሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አሁንም በቂ ባለመሆኑ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ግለሰቦች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

" ... እንስሳት የሚበሉትን አጥተው አብዛኛዎቹ አልቀዋል፤ ከእንስሳትም አልፎ ለሰው ህይወትም እየሰጋን ነው " - አቶ ጎዳና ሎራ #NakorMelkaVoA በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የድሬ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎዳና ሎራ ባለፈው ዓመት መዝነብ የነበረበት የመኸር እና ክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀው ፤ ተጨማሪ ጉዳት ለመከላከል ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።…
#Oromia , #Borana📍
በድርቅ ምክንያት 30 ከብቶቻቸውን ያጡት የድሬ ወረዳ ነዋሪው ጎዳና ሎራ (ለቪኦኤ የሰጡት ቃል) ፦
" እኛ የቦረና ህዝብ ከከብት ውጪ ሌላ ምንም ነገር የለንም። ያሉን ከብቶች በድርቅ ምክንያት አልቀውብናል።
አሁን በነፍስ ያሉት ሞተው ካለቁብን ህይወታችን በጨለማ ተጋረደ ማለት ነው። አሁን ባለው ሁኔታ በህይወት ያሉ ከብቶች እንኳን ዋጋ የላቸውም።
ድሮ በ10 ሺህ ብር የሚሸጥ ከብት 2 ሺህ ብር እያወጣ አይደለም። በችግር ላይ ነን። ህዝቡ ምንም የለውም። በፊት ፍየል ነበር አሁን ህዝቡ እሱን እየሸጠ ከብቶቹን ለማዳን እየተረባረበ ስለሆነ እነሱም አልቀዋል።
መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሁሉ በመተባበር ከቦረና ህዝብ ጎን መቆም ያስፈልጋል አለበለዚያ አሁን የተከሰተው ድርቅ ለሰው ህይወትም አስጊ ነው። "

#AU2022Summit
የአፍሪካ ህብረት (AU) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ተግባር እንደሚደግፍ የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፤ ሰላምና ጸጥታ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽነሩ አምባሳደር ባንኮሊ አዲኦይ በሰጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተውን የጸጥታ ችግር አፍሪካዊ በሆነ መፍትሔ ለመፍታት ሲያደርጋቸው የነበሩ ጥረቶችን ዘርዝረዋል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት አካታች ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ የወሰደውን ተነሳሽነት አድንቀው ህብረቱ ለምክክሩ ስኬት የሚጠበቅበትን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ህብረቱ ምክክር ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት በሃብት፤ በሙያና በሌሎች ተመሳሳይ መስኮች እንደሚደግፍ ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በግጭቱ ሳቢያ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ጠ/ ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ማረጋገጣቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
#ENA

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጉባኤው በስኬት መጠናቀቁን አሳውቀዋል።
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " የዘንድሮው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ እንዲደረግ የአባል ሀገራት መሪዎች መወሰናቸውን ተከትሎ ወንድማዊ አጋርነት የታየበት የኅብረቱ ጉባኤ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት ተካሂዶ በስኬት ተጠናቅቋል " ብለዋን።
የኅብረቱ ጉባኤ ፍሬያማ ውይይት የተካሄደበት፣ ለአህጉሪቱ የሚጠቅሙ ውሳኔዎች የተላለፉበት፣ ከምንም በላይ ወንድማዊ አጋርነት የታየበት ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቀ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

#AU2022Summit የአፍሪካ ህብረት (AU) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ተግባር እንደሚደግፍ የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፤ ሰላምና ጸጥታ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽነሩ አምባሳደር ባንኮሊ አዲኦይ በሰጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተውን የጸጥታ ችግር አፍሪካዊ በሆነ መፍትሔ ለመፍታት ሲያደርጋቸው የነበሩ ጥረቶችን ዘርዝረዋል። በአሁኑ ወቅት…
#AU2022Summit
" ... ህብረቱ የኢትዮጵያ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል " - አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ
የአፍሪካ ህብረት ለኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ከአህጉሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተጨማሪ ባለሙያዎችን ወደ ስራ እንደሚያስገባ አስታውቋል።
የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ ፤ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።
በዚህ ሳምንት የህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በአማራ እና አፋር ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

#Update
የጉባኤው ተሳታፊዎች እየተሸኙ ነው።
የ35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ የተሳታፊ ሀገራት መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖች ወደ የሀገራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

#Update ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የመስቀል አደባባይ፣ የጃንሜዳና ልሎች የቤተክርስቲያን ይዞታዎች ጉዳይ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ ዙሪያ ባካሔደው ስብሰባ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚደረገው ውይይት…
#Update
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር ተወያዩ።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " ዛሬ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል " ብለዋል።
ከንቲባዋ ከቅድስት ቤተክርስቲያን በኩል የሚነሱትን ጉዳዮችን ህጋዊ ሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት እንደሚቻል ተግባብተናል ሲሉም አሳውቀዋል።
ወ/ሮ አዳነች ፥ " ስለነበረን መልካምና ገንቢ ቆይታም ብፁዕነታቸውን ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ " ሲሉም ፅፈዋል።

#Tigray , #Mekelle 📍
አሚና መሐመድ ትግራይ ክልልን ጎብኝተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሐመድ የተመራ ልዑክ ዛሬ በትግራይ ክልል መቐለ ጉብኝት አድርጓል።
የልዑካን ቡድኑ በመቐለ ከተማ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ፤ የጤና ባለሞያዎችን አነጋግሯል።
ከዚህ በተጨማሪም በመቐለ የሚገኙ በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙባቸውን ካምፖች ተመልክቷል ፤ የጦርነት ተጎጂዎችንም አነጋግሯል።
በአሚና መሐመድ የተመራው ልዑክ ዛሬ ጥዋት አማራ ክልል የኮምቦልቻ ከተማ ተገኝቶ ጉብኝት ማድረጉን መግለፃችን ይታወሳል።
ስለ ዛሬው የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ጉብኝት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሐመድ / በተመድ የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#AFCON
የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።
የውድድሩ ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች #ሴኔጋል እና #ግብፅ ሲሆኑ ጨዋታው ተጀምሯል።
ይህ ጨዋታ በመላው አፍሪካ እንዲሁም በዓለም አቅፍ ደረጃ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ነው።
የዋንጫው 🏆 ባለቤት ማን ይሆናል ?
@tikvahethiopia
የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።
የውድድሩ ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች #ሴኔጋል እና #ግብፅ ሲሆኑ ጨዋታው ተጀምሯል።
ይህ ጨዋታ በመላው አፍሪካ እንዲሁም በዓለም አቅፍ ደረጃ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ነው።
የዋንጫው 🏆 ባለቤት ማን ይሆናል ?
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Senegal🏆 ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆነች። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AFCON
ከፍተኛው ተጋድሎ በሴኔጋል አሸናፊነት ተደምድሟል።
በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ሰኢዶ ማኔ የፍፁም ቅጣት ምት መሳቱ የሴኔጋሉን ፕሬዜዳንት ማኪ ሳል በድንጋጤ አስጩሆ ከመቀመጫቸው ያስነሳ ፤ የጨዋታው ፍልሚያ ከቴሌቪዥን ስክሪን ላይ ለአፍታ አይንን የማያስነቅል፤ እጅግ አጓጊ ተጋድሎ የተደረገበት ነበር።
የግብፁ ግብ ጠባቂ ጋባስኪ በፍልሚያው ያሳየው ተጋድሎ በርካቶችን ያስጨበጨበ ነበር።
ሁለት አሸናፊ አይኖርምና ፍልሚያው በመለያ ምት ሲለይ ግብፅ 4 - 2 ሽንፈትን ስትቀምስ ሴኔጋል በታሪኳ የመጀመሪያ ዋንጫውን አግኝታለች።
በዘንድሮው ውድድር እስከመጨረሻው የደረሱት ግብፃውያን ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኞች፣ ደጋፊዎች አነቡ ፤ ዋንጫውን በመነጠቃቸው አዘኑ ፤ በውድድሩ ግን 2ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።