TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አውስትራሊያና ቻይና በኮሮና ቫይረስ መነሻ አስባብ ብርቱ ወደ ሆነ ውዝግብ እያመሩ ነው!

(በSBS የቀረበ)

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መነሻን አስመልክቶ ሉላዊ ምርመራ እንዲካሄድ እየገፋ ሲሆን፤ ቻይና በበኩሏ የአውስትራሊያ መንግሥት በዚህ አቋሙ ከርሮ ከገፋ ከአውስትራሊያ ዋነኛ የውጭ አቅርቦት ላኪዎችን ምርቶች መቀበሏን ልትገታ እንደምትችል #ማስጠንቀቂያ አዘል አቋሟን አደባባይ አውላለች።

በአውስትራሊያ የቻይና አምባሳደር አውስትራሊያ ወረርሽኙን አስመልክታ ለምትገፋው የምርመራ አጀንዳ ቻይና በአውስትራሊያ ቱሪዝም፣ ግብርናና ትምህርት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል አስጠንቅቀዋል።

ይሁንና የአውስትራሊያ የንግድ ሚኒስትር የሆኑት ሳይመን በርሚንግሃም አውስትራሊያ ለቻይና ዛቻ እንደማትበጅ ጠቅሰው ተናግረዋል። አክለውም፦

"እዚህ ላይ ግልጽ እንሁን። ኮቪድ-19 በዓለም ላይ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል፤ ሚሊዮኖችን ለሥራ አጥነት ዳርጓል፤ በቢሊየን የሚቆጠሩቱ አዘቦታዊ ሕይወታቸው ተስተጓጉሏል። ዓለም የመጨረሻ ሊያነሳ የሚገደው ነገር ቢኖር በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ ለወደፊቱ ዳግም ተመሳሳይ ክስተት እንዳይከሰት ቅድመ መከላከል ለማድረግ ይበጅ ዘንድ የኮሮና ቫይረስ መነሾን አስመልክቶ ግልጽ ምርመራ እንዲካሄድ መጠየቅ ነው" ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
ሂሩት ክፍሌ በእስር እንዲቆዩ ተደረገ! የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የፖሊስን አቤቱታ የሚያይ ዳኛ ስላልተገኘ ሂሩት ክፍሌ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ያስጠበቀላቸውን መብት ፖሊስ ጥሶ በእስር እንዲቆዩ አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ/ አስታውቋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፍርድ ቤቱ ሂሩት ክፍሌ ከእስር እንዲፈቱ አዘዘ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

የፖሊስን የይግባኝ አቤቱታ የሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ትላንት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ሂሩት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፖሊስ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝን ሳይፈጸም ተጠርጣሪዎችን በእስር አቆይቶ ይግባኝ መጠየቁ ወንጀል ነው ሲል ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ #ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

"የቡሬ ከተማና አካባቢው በሙሉ በአሁኑ ሰዓት መንግስት ብር ኖት መቀየሩ ይታወቃል።

ይህን ብር አመሳስለው የሚሰሩ ህገወጦች በከተማችን ይዘው እየተዘዋወሩ ሲሆን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦችም ተይዘው በህግ ጥላ ስር ይገኛሉ።

በመሆኑም ሁሉም ሰው መጠንቀቅ ይገባዋል። የአዲሱ ብር ምልክቶች ለማወቅ ከላይ ያለውን ምስል ይመልከቱ!" - ቡሬ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ታሽጎ የሚሄድበትን ሳጥን ፦
- መክፈት
- ማንቀሳቀስ
- መቁረጥ
- ውስጡን ማየት ከፍተኛ የሆነ #ወንጀል ነው።

ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ወረዳ ላይ ያሉ ዝቅተኛ እርከን ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት (ይከፈት እንየው የሚሉ) በሙሉ ከፍተኛ #ማስጠንቀቂያ ሠጥቷል።

በማንኛውም ሁኔታ በምርጫ ክልሎች ላይ ችግር ተፈጥሮ ከተገኘ ወደድጋሚ ምርጫ እንደሚሄድ መታወቅ አለበት ብሏል ቦርዱ ፤ አክሎም የድጋሚ ምርጫ ለሀገር ሃብት ጠቃሚ ስላልሆነ፣ ቦርዱም ብዙ ገንዘብ ስለሚያባክን ከድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ጋር በተገናኘ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

#TikvahEthiopia #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲያበር የተገኘ በሕግ እንደሚጠየቅ አስጠንቅቋል።

ለዜጎች ሰላም መረጋገጥ እንዲሁም የቁልፍ መሰረት ልማቶችን ደህንነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመጠበቅና ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ ለቀረፃ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ለቀረፃ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ መሆኑን የገለፀው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ በጥብቅ አስጠንቅቋል።

ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀምና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ ይጠየቃልም ብሏል።

Credit : የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

@tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

" ሲሪስ አፕል ጁይስ " 100% የተሰኘው ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ማሳሰቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በሲሪስ አፕል ጁይስ ውስጥ 100% ስለተገኘ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

ምርቱ የዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል ባለስልጣን መ/ቤቱ ያስጠነቀቀ ሲሆን፥ በተመሳሳይ የሲሪስ አፕል ጁይስ አምራች የሆነው የደቡብ አፍሪካ የምግብና የመጠጥ አምራች ምርቱ ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በውስጡ በእንዳለ በመግለጽ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ነው ያሳሰበው፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ፥ ህብረተሰቡ የሲሪስ አፕል ጁይስ 100% ምርት በሀገራች ገበያ ውስጥ እንዳለ በመገንዘብ ምርቱን እንዳይጠቀም አስጠንቅቆ ÷ ምርቱን በማንኛውም አጋጣሚ ገበያ ላይ ሲገኝ በፌዴራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 እንዲሁም በአቅራቢያ ለሚገኙ የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት ማስተላልፏል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

በሀረሪ ክልል የህክምና ቁሳቁሶችን ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሚሸጡ መድሃኒት መደብሮችን ከእኩይ ተግባራቸድ እንዲቆጠቡ የክልሉ ጤና ቢሮ አሥጠንቅቋል።

ቢሮው ፥ በጤና ባለሞያዎች የታዘዙ የመድሃኒት ምርቱ እያለ የለም በማለት እና ለህብረተሰቡ በተጋነነ ዋጋ በማቅረብ የግል ጥቅማቸውን የሚያሯሩጡ መድሀኒት መደብሮች ከዚህ እኩይ ተግባር ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል።

በተያያዘ በጤና ባለሞያዎች ያልታዘዙ መድሃኒቶችን በግድ የለሽነት የሚሸጡ የግል መድሃኒት መደብሮች ህጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ቢሮው አሳውቋል።

መድሀኒት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሚሸጡ መድሃኒት መደብሮችን ህብረተሰቡ በማጋለጥ የበኩሉን እንዲወጣ ሲል የክልሉ ጤና ቢሮ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ ፦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻውን ተሰብስቦ፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተመለከቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ገምግሟል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተያዘለት ዓላማ አኳያ አፈጻጸሙ በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን አረጋግጧል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከርና ዕንቅፋት የሚሆኑትን ችግሮች ለማስወገድ የሚከተሉትን 4 ትእዛዞች አስተላልፏል። #1…
#ማስጠንቀቂያ

ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው።

በየግንባሩ የሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከተሰጣቸው ሥምሪትና ተልእኮ ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እንዲሁም ውጤቶችን የሚመለከቱ መግለጫዎች መስጠት የተከለከለ ነው።

የጸጥታ አካላትም ይሄን ተላልለፈው በሚገኙት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ ፦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻውን ተሰብስቦ፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተመለከቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ገምግሟል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተያዘለት ዓላማ አኳያ አፈጻጸሙ በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን አረጋግጧል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከርና ዕንቅፋት የሚሆኑትን ችግሮች ለማስወገድ የሚከተሉትን 4 ትእዛዞች አስተላልፏል። #1…
#ማስጠንቀቂያ

በማንኛውም ሁኔታ፣ ቦታና ጊዜ የመከላከያ ሠራዊትን፣ የፌዴራል ፖሊስን፤ የክልል ልዩ ኃይሎችንና የመደበኛ ፖሊስን ዩኒፎርሞች፣ የጸጥታ አካላት አባል ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለብሶ መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

የተቋማቱ አባል ሳይሆንና የታደሰ መታወቂያ ሳይዝ ዩኒፎርሙን ለብሶ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ፣ የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል።

(አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። ታህሳስ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ (የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ) በጥር ወር ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

አንዳንድ ኩባንያዎችና የነዳጅ ማደያዎች ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር እያደረጉ ካለው ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጥር 26/2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2014 ዓ.ም ድረስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲሸጥ ወስኗል፡፡

ሚኒስቴሩ መንግስት ምንም እንኳን ነባራዊ የዓለም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በመጨመር ላይ ቢሆንም የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል ውሳኔውን ማሳለፉን ገልጿል።

በዘርፉ በየተሰማሩ ተዋንያን ከህገወጥ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ሚኒስቴሩ የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት ያልተገባና ህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኩባንያዎችና ማደያዎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እግድ " የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ጣቢያ " በመንግስት #በጊዜያዊነት ታገደ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ እሁድ በፃፈው ደብዳቤ " ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ " ን በጊዜያዊነት እንዳገደ አሳውቋል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም " ሰበር ዜና " በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን…
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ በላከው መግለጫ ፤ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ህጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው ሲል ገልጿል።

ኢዜማ ፤ " የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ከተልዕኳቸው ውጪ የገዢው ፓርቲ ልሳን ሆነው የህዝብን በደል እና የመንግሥትን ብልሹ አሰራር ጆሯቸውን ደፍነው ዘወትር የውዳሴ ዘገባ ለገዢው ፓርቲ እና መንግሥት በማቅረብ ለተጠመዱት የህዝብ መገናኛ ብዙኋን ምንም አይነት #ተግሳጽ እንኳ ሳያቀርብ ባለፈው እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም ለማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት በፃፈው የእግድ ደብዳቤ ብሮድካስት ባለፍቃዱን በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል " ብሏል።

" ይህ የእግድ ውሳኔ ምክንያቱ ሕጋዊ ሆነም አልሆነ በመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2021 አንቀጽ 73 ፣ 76 እና 81(2) የተጠቀሱትን በቅድሚያ #ማስጠንቀቂያ የመስጠትም ሆነ የሚዲያ ተቋሙ #ራሱን_እንዲከላከል ቀድሞ እድል የመስጠት ሕጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው " ሲል ኢዜማ ገልጿል።

" ተቋማት የሚወስዷቸው እርምጃዎች በእርግጥም ሕግን ከማስከበር መነሻነት ይልቅ በማን አለብኝነት ድርጅታዊ ፍላጎትን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነው " ያለው ኢዜማ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ላይ የወሰደው እርምጃ ይህን በግልፅ ያስረዳል ብሏል።

ተቋማት ከእንደዚህ አይነት ወጥነትና ገለልተኝነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲወጡም አሳስቧል።

ፓርቲው ፦

- የመገናኛ ብዙኀንን ጨምሮ ገለልተኛ ሊሆኑ የሚገባቸው ተቋማት ከገዢው ፓርቲ አባላት ተጽዕኖ ነፃ ማውጣት፤

- የመንግሥት እና የፓርቲ አሠራር የተለያዩ መሆናቸውን በሕግም በተግባርም ማረጋገጥ፤

- የሚወሰዱ እርምጃዎች ሕግ እና ሕግ ላይ ብቻ መሠረት ያደረጉ ብቻ ሊሆኑ ይገባል ብሏል።

ኢዜማ ፤ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን የወሰደው እርምጃ " በአዋጅ ከተሰጠው ሥልጣን ወሰን ተላልፎ የወሰደው " ነው ያለ ሲሆን ፓርቲው ሕገ ወጥ ነው ያለው ውሳኔ እንዲሽር፤ ባለስልጣኑ ይህን ውሳኔ ያሳለፉትን አካላት ተጠያቂ በማድረግ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama " ... እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቻችሁን ከማስተማር ተቆጠቡ " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በአብዛኛዉ ከደረጃ በታች መሆናቸዉ ተከትሎ 17 ኮሌጆች #መዘጋታቸዉ ተገለጸ። የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ባካሄደዉ…
በሲዳማ ክልል የተዘጉ ኮሌጆች ዉስጥ እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች ዕጣፋንታ ምንድን ነዉ ?

በሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በኩል 17 ያክል ኮሌጆች መዘጋታቸዉን ተከትሎ በተማሪዎችና ወላጆች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል።

ወደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎች እና ወላጆች ከተላኩ ጥያቄዎች መካከል ዋነኛው " በኮሌጆች ዉስጥ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች እጣፋንታ ምንድን ነዉ ? " የሚል ነበር።

ለዚህ ጥያቄ ምላሻቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሀላፊው አቶ ፍስሀ ፍቶላ ፤ በነዚህ የተዘጉ ኮሌጆች የነበሩ ተማሪዎች መረጃ ተጠናቅሮ በቅርብ ወዳሉ ኮሌጆች እንደሚዘዋወሩ ገልጸዋል።

ለነዚህ ኮሌጆች ከ1 አመት በፊት #ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ መቆየቱን የገለፁት አቶ ፍስሀ ይህ ቆይታ የተማሪዎችን ጉዳይ ለመጨረስ እና ያለምንም ጉዳት ለማዘዋወር በቂ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ በክልሉ ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ዉሳኔ የተዘጉ  ኮሌጆች ቅሬታቸዉን እያቀረቡ ስለመሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተረዳ ሲሆን ይህን ጉዳይ የምንከታተል ይሆናል።

የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ፦
* በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በህገወጥ ስራ መሰማራታቸዉን፤
* 17 ኮሌጆች ስራ እንዲያቆሙ ሲወሰን ኮሌጆቹ በመላዉ ሲዳማ የጀመሯቸዉን የማስተማር ስራዎች አቁመዉ ፈቃዳቸዉን እንዲመልሱ እንደተናገራቸው፤
* ያላግባብ #ሳያስተምሩ_አስመርቀዉ ስራ ፈላጊና የሀገር ሸክም በማድረጋቸዉም በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉ፤ ቢሮዉ እጁ ላይ ያለዉን መረጃ ባፋጣኝ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ እንደሚልክ፡
* ማህበረሰቡ እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቹን ከማስተማር እንዲቆጠብ፤
* ከዚህ በኋላ በመላዉ ሲዳማ ክልል ከገበያዉ በላይ የተማረ ሰዉ በመኖሩ የአካዉንቲንግ ማርኬቲንግና የሰዉ ሀይል አስተዳደር ትምህርቶችን መማርም ሆነ ማስተማር የተከለከለ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

መረጃው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰጠው የዕውቅና ፍቃድ ታገደበት። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ባገኘው መረጃ ትምህርት ቤቱ ፦ - በሀገር አቀፍ እና በከተማ አስተዳደሩ የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ባለማድረጉ ተማሪዎች ከአማርኛ ትምህርት ውጭ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች በእንግሊዝኛ…
#Update

የጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዕውቅና ፍቃድ ታግዷል።

ይህን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆነ ወላጆች " ግልፅ አይደለም " ያሉትን ጥያቄ አንስተው ምላሽ እንዲሰጥባቸው መልዕክት ልከዋል።

የወላጆች ጥያቄ ...

- ይፋ የሆነው ደብዳቤ የዋናው የባለስልጣን መ/ቤቱ ሳይሆን " የጉለሌ ቅርጫፍ ፅ/ቤት " ነው ለዋናው ባለስልጣን መ/ቤት በግልባጭ እንዲደርስ ነው የሚለው ፤ ውሳኔው ከላይ ጀምሮ የመጣ ነው ? ዋናው መ/ቤት በዚህ ጉዳይ ምንድነው የሚለው ? ውሳኔውን ያውቀዋል ?

- ይህ ውሳኔ አሁን በተማሪዎች ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ አለ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላጆችን ጥያቄ ይዞ ይመለከታቸዋል ያላቸውን የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መ/ቤት አካላትን አነጋግሯል።

በዚህም ፤ በጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተወሰነው የዕውቅና ፍቃድ እገዳ ፦
* የዋናው የባለስልጣን መ/ቤቱ
* የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ... ሌሎችም የተለያየ #ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኃላ ውሳኔያቸው ያረፈበት ነው ብለውናል።

ምንም እንኳን የጉለሌ ቅንጫፍ ፅ/ቤት ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያ ተለቆ ቢታይም የዕውቅና እገዳው ውሳኔ በአራት ክ/ከተሞች ማለትም ለሚኩራ፣ ንፋስ ስልክ፣ ቦሌ ፣ ጉለሌን የሚመለከት ነው ሲሉ አስረድተውናል።

በአጠቃላይ 17ቱም የጊብሰን ቅርንጫፎች ላይ የተወሰነ ነው ሲሉም አክለዋል።

አሁን የተላለፈው የዕውቅና እገዳ ውሳኔ በዚህ አመት እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳትም ሆነ ተፅእኖ እንደማያደርስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መ/ቤት ለመስማት ችሏል።

የጊብሰን ትምህርት ቤት በጉዳዩ ላይ የሚሰጠን ማብራሪያ ካለ የምናቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia