TIKVAH-ETHIOPIA
#ፅጌሬዳ_ግርማይ ስለፅጌሬዳ ግርማይ ግድያ ጓደኞቿ ምን አሉ ? አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ከአባቷ ከአቶ ግርማይ ገ/መድን እና ከእናቷ ከወ/ሮ ያበሻ ያዘዘው በወልቃይት አድ ረመጽ ከተማ በ1993 ዓ/ም ነው የተወለደችው። የመሰናዶ ትምህርቷን በወልቃይት ጌታቸው አዘናው 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንደተከታተለች ፤ ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመመደብ በሆቴልና…
#ፅጌሬዳ_ግርማይ
የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን ግድያ በተመለከተ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ መረጃ ሰጥቷል።
ሰኞ ዕለት ህይወቷ ያለፈው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተጠረጠረ ተማሪ ትላንት ከሰዓት ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ምስክርነት የሰጡ የተጠርጣሪው #ሁለት_ጓደኞቹ የሚከተለውን ብለዋል :-
"ተማሪ ፅጌሬዳ ከተጠርጣሪ ወንጀለኛው ጋር ግንኙነት የነበራት ሲሆን በመሀል ውጪ የነበረ ጓደኛዋ ስለመጣ ግንኙነቱን ማቋረጥ እንደምትፈልግ ገልጻለታለች። በዚህም ተጠርጣሪው ደስተኛ እንዳልነበረና ዛቻና ማስፈራሪያ በጓደኞቿ በኩል ይልክላት ነበር።"
ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ከሁለቱ ጓደኞቹ በአንደኛው ስልክ በመደወል ወደ አስተዳደር ህንጻ አካባቢ እንድትመጣ አድርጓል።
በወቅቱ ስልክ ደዋዩና ሌላኛው ጓደኛው አብረውት ነበሩ። "ጉዳያችንን እኛ እንጨርሳለን እናንተ ሂዱ" ብሏቸው ብዙም ሳይቆይ በስለት እንደወጋት ጓደኞቹ ምስክርነት ሰጥተዋል።
ሟች ልቤን ብላ ስትጮህ በቅርብ ርቀት የነበሩ የግቢው ጥበቃ አባላት ደርሰው ለማምለጥ የሞከረውን ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውለውታል።
ተጠርጣሪው በሕግ ጥላ ስር ውሎ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ሲሆን ፍ/ቤት ቀጣይ ቀጠሮ እንደሰጠው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በድሩ ሂሪጎ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
የሟቿ አስክሬን ትላንት ቤተሰቦቿ ወደሚገኙበት ወልቃይት ወረዳ አድ ረመጽ ከተማ መላኩንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በ20 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ተማሪ ፅጌሬዳ በዩኒቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡
More : @tikvahuniversity

ለAU ስብሰባ የሚዘጉ እና ተለዋጭ መንገዶች !
ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ/ም 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል::
ቀደም ብሎ ጥር 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ/ም 40ኛው የህብረቱ አባል ሀገራት የሚኒስትሮች ሥራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይልም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡
በዚህም፦
• ከአዋሬ በጥይት ቤት ወደ ፓርላማ
• እንዲሁም ከቡልጋሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት የሚወስዱ መንገዶች በሁለቱም አቅጣጫ የስብሰባው ተካፋዮች ጠዋት ለስብሰባ ፣ ለምሳና ከሰዓት በኋላ ከስብሰባ ሲወጡ እነዚህ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት ፤ ለአጀብ ስራ መንገድ ሲዘጋ ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆን ድረስ አሽከርካሪዎች ትዕግስት ተላብሰው በመጠበቅ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡-
• ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ -ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ -ኤርፖርት
• ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሄራዊ ቤተ - መንግስት -በፍልውሃ - በብሄራዊ ቲያትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ፡-
• ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር -ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት
• ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቲያአትር ዙሪያውን
• ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከዓርብ ጥር 27 ቀን / 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው።
• ከጦር ሃይሎች - ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ፦
• በኮካ-ኮላ ድልድይ - በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር- ጎማ ቁጠባ
• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፡-ሳር ቤት-ካርል አደባባይ - በልደታ አድርገው ወደ መርካቶ እና ጎማ ቁጠባ
• የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፦
• በአትላስ - ዘሪሁን ህንፃ- ሲግናል
• ቀለበት መንገድ - ቦሌ ሚካኤል-ሃኪም ማሞ - ወደ ጎተራ
• ቀለበት መንገድ - መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ - እንግሊዝ ኤምባሲ
• ቀለበት መንገድ -መገናኛ - አድዋ ጎዳና - አዋሬ - ቤልኤር
• በፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ መስቀል ፍላወር መጠቀም ይቻላል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia

#Update መንግስት በቅርቡ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በተናገሩት ንግግር ላይ ምላሽ ሰጠ። የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ጋር ድርድር አለመጀመሩን ዛሬ አስታውቋል። የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ባለፈዉ ሳምንት ከቢቢሲ ኒውስ ሀወር ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሌሎች አካላት (ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ) ንግግር መጀመራቸውን…
" መንግስት እስካሁን ከህወሓት ጋር የጀመረው ንግግርም ሆን ድርድር የለም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
በቅርቡ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ለቢቢሲ ኒውስ ሀወር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ንግግር መጀመራቸው መግለፃቸውን በተመለከተ ትላንት የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ሀሰት ነው ሲሉ ማጣጣላቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ ዛሬ ረቡዕ ለአል ዓን ኒውስ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፦
" የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለሚያስጠብቅ የትኛውም ለሰላም አማራጭ በራችን ከፍት ነው።
ሆኖም ግን ከህወሃት ጋር ስለመደራደር እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል የተወሰደ አቋም የለም።
ህወሃት ማንኛውንም አይነት የፖለቲካ መሳሪያ ከመጠቀም ወደ ኋላ አይልም፤ ህብረተሰቡ ውስጥ ክፍፍል መኖሩን ካረጋገጠ አለመተማመን እንዲፈጠር እንዲህ አይነት ነገር ይጠቀማል።
ህዝቡ ዘንድም መንግስት እኛን ዋሽቶ ከጀርባችን ከእነሱ ጋር እየተነጋገረ ነው እንዲባል ስለሚፈልጉ ነው እንደዛ የሚያደርጉት።
መንግስት እስካሁን ከህወሓት ጋር የጀመረው ንግግርም ሆን ድርድር የለም " ብለዋል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። ታህሳስ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ (የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ) በጥር ወር ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ
አንዳንድ ኩባንያዎችና የነዳጅ ማደያዎች ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር እያደረጉ ካለው ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጥር 26/2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2014 ዓ.ም ድረስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲሸጥ ወስኗል፡፡
ሚኒስቴሩ መንግስት ምንም እንኳን ነባራዊ የዓለም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በመጨመር ላይ ቢሆንም የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል ውሳኔውን ማሳለፉን ገልጿል።
በዘርፉ በየተሰማሩ ተዋንያን ከህገወጥ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ሚኒስቴሩ የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት ያልተገባና ህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኩባንያዎችና ማደያዎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

Photo
#ችሎት
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በስልክ በትግረኛ ቋንቋ እንዲያወሩ ፍርድ ቤት ፈቀደ።
የቀድሞ የፌደሬሽን ም/ቤት አፈጉባዬ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በማረሚያ ቤት ስልክ በትግረኛ ቋንቋ ለማውራት እንዲፈቀድላቸው በታሳስ 21ቀን 2014 ዓ/ም ለችሎቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር።
አቤቱታው የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቤቱታውን መርምሮ በዛሬው ቀጠሮ ትዛዝ ሰቷል።
በዛሬው ቀጠሮ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ የትግራይ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አሰፉ ሊላይን ጨምሮ 5 የተለያዩ አቤቱታ ያቀረቡ ተከሳሾች በችሎት ተገኝተዋል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ ፤ " ማንም ሰው በቋንቋው የማውራት ህገመንግስታዊ መብት አለው " ሲል ወ/ሮ ኬሪያ በስልክ በትግረኛ ቋንቋ እንዲያወሩ እንዲመቻችላቸው ትዛዝ ሰቷል።
በተጨማሪም ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ማስታወሻ ደብተር እንድንይዝ ትዛዝ ይሰጥልን ሲሉ አቅርበው የነበረውን አቤቱታ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ማስታወሻ ደብተር እንዲይዙ እንዲመቻችላቸው ትዛዝ አዟል።
በሌላ በኩል 43ኛ ተከሳሽ አቶ ተክላይ አብርሐ መንጃ ፍቃድ እና ፖስፖርት ለማሳደስ እንዲፈቀድላቸው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ፍርድ ቤቱ ፓስፖርትና መንጃ ፍቃዳቸውን በአጃቢ እንዲያሳድሱ እንዲመቻችላቸው ፈቅዷል።
በባለፈው ቀጠሮ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ፍርድ ቤት በህመም ምክንያት ስንቀር በሚዲያ ሲዘገብ ቤተሰቦቻችን ሰምተው እየተጨነቁ ስለሆነ ሚዲያዎች ችሎት እንዳይገቡ ይታዘዝልን ሲሉ አቅርበውት የነበረውን አቤቱታን በተመለከተ ችሎቱ ምንም ሳይል አልፎታል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#Update
የሁለተኛው ቀን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።
በፀጥታ ችግር ምክንያት ከዚህ ቀደም በተሰጠው ብሄራዊ ፈተና ላይ መቀመጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ባሉባቸው የአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋርና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከትላንት ጀምሮ ፈተናው መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።
ብሄራዊ ፈተናው ከነገ በስቲያ ይጠናቀቃል።
ፎቶ ፦ ወልዲያ ኮሚኒኬሽን (ዛሬ ጥር 25)

#OromiaRegion
Biiroon Fayyaa Oromiyaa Hakimoota (GP) baay'inni isaanii 2000 (Kuma lama) ta'e qacaree hojjachiisuu barbaada.
የኦሮሚያ ጤና ጥበቃ ቢሮ ' 2,000 ' የሚሆኑ አዲስ የተመረቁ ሀኪሞችን(GP) በክልሉ ባሉ ሆስፒታሎች በቋሚነት ለመቅጠር እንደሚፈልግ ባወጣው ማስታወቂያ አስታውቋል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሀኪሞች ተመዝግበው ምደባ መውሰድ ይችላሉ ብሏል።
በዚህም መሰረት፦
👉 የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን መናገር፣ ማንበብና መጻፍ የሚችል
👉 ብዛት - 2,000
👉 ደሞዝ - 9,056 ብር
👉 የትምህርት ማስረጃ - ዋናውንና ኮፒ፤
👉 የሞያ ፍቃድ - ዋናውና ኮፒ፤
👉 የምዝገባ ቀን - ማስታወቂያው ከተነገረበት ቀን አንስቶ ላልተወሰነ ጊዜ ባሉ የሥራ ሰዓቶች፤
👉 የምደባ ቀን - በዕጣ የሚወጣ ሲሆን ቀኑ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል።
👉 የመመዝገቢያ ቦታ - የኦሮሚያ ጤና ቢሮ 3ኛ ፎቅ በሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ።

#Update ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጤና ችግር አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል። ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ በቅዱስነታቸው አለመገኘት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል። ቅዱስነታቸው ፥ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና…
#Update
ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የመስቀል አደባባይ፣ የጃንሜዳና ልሎች የቤተክርስቲያን ይዞታዎች ጉዳይ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ ዙሪያ ባካሔደው ስብሰባ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚደረገው ውይይት ቋሚ ሲኖዶስ በሚያስቀምጠው አቅጣጫና ጊዜ ቀጠሮ መሰረት በተለዋጭ ቀጠሮ የሚካሔድ ይሆናል ብሏል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚቀጥለው ቀጠሮ ጀምሮ ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ዛሬ የመስቀል አደባባይን አስመልክቶ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዞ እንደነበር አስታውሷል።
የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ቀጠሮ በተያዘበት ቦታና ሰአት የተገኙ ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶሱ በላከው መልእክት ዛሬ በስብሰባው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲያዝ በመጠየቅ የዛሬው ስብሰባ ሳይካሄድ ቀርቷል ብሏል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ለመወያየት እና አብሮ ለመስራት በማንኛውም ሁኔታና ሰአት ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።
ከላይ ያሉት መረጃዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገኙ ሲሆን የዛሬው ስብሰባ ለምን እንደቀረ የተሰጠ ግልፅ ማብራሪያ ማግኘት አልቻልንም።

#Abyei #UNISFA
ተመድ ሜ/ጄነራል ቤንጃሚን ኦሉፊሚ ሳውየርን የአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ሃይል አዛዥ አድርጎ ሾሟል።
ሜ/ጄነራል ቤንጃሚን ኦሉፊሚ ዜግነታቸው ናይጄሪያዊ ሲሆኑ በኢትዮጵያዊው ሜጀር ጀነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ ምትክ ነው በቦታ የተሾሙት።
ሜ/ጀነራል ከፍያለው አምዴ በአብዬ ግዛት የነበረውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ሲመሩ እንደነበር ይታወቃል።
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሜ/ጄነራል ከፍያለው አምዴ የአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ኃይል አዘዥ ሆነው ከተሸሙበት ጊዜ አንስቶ ላሳዩት ትጋት፣ የሰጡት አግልግሎትና ውጤታማ አመራር ምስጋና አቅርበዋል።
ሱዳን በአብየ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከስፍራው እንዲወጣ ጥያቄ ማቅረቧ ይታወሳል።
ከሳምንታት በፊት ተመድ በአብዬ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የመተካቱ ሂደት በየካቲት ወር እንደሚጀመር መግለፁ አይዘነጋም።

#ETHIOPIA
‘‘... ኢትዮጵያ ለእኛ ለአፍሪካውያን እና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች እናታችን ናት፤ የነጻነታችን ትእምርት/Symbol የሆነች አገርም ናት።
ስለሆነም አዲስ አበባ 'የፓን አፍሪካን መዲና' (የአፍሪካ አንድነት ከተማ) መባሏ ከዚህ ታሪካዊ ሐቅ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ " - (የናይጄሪያው ሳንዴይ ኦብዘርቨር/ጁላይ 23፣ 1972)
#TadeleDerseh
ፎቶ፦ ፎቶግራፈር - አቡቲ እንግዳሸት

የኬንያንው ፕሬዜዳንት ተማፅኖ ....
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት መቋጫ ያገኝ ዘንድ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ከሚነገርላቸው ሀገራት ጎረቤታችን ኬንያ አንዷ ናት።
የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዚህ በፊት ለግጭቱ መቆሚያ መፍትሄ እንደመጣ ጥሪ ሲያቀርቡ እንደበር አይዘነጋም።
ትላንት ለሊት የተ.መ.ድ ዋና ፀሀፊት አንቶኒዮ ጉተሬዝን መልዕክት ተንተርሰው በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ተማፅነዋል።
ኬንያታ ምን አሉ ?
- የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚጋሩ አስታውቀዋል።
- በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ግጭት ውስጥ የሚሳተፉ አካላት ሁሉ ጦርነቱን እንዲያቆሙም ተማፅነዋል።
- የቀጠለው ግጭት የኢትዮጵያን ህዝብ እየዘረፈ እና የዚህ ታላቅ ህዝብ ባህልና ስልጣኔ ውስጥ ያለውን ክብር እያሳጣ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
- አስተማማኝ ሰላም የሚሰፍነው እንዲሁም የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን የምትሆነው ሁሉም የኢትዮጵያ አካላት ዘላቂ በሆነና በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ባለው መንገድ ፈተናዎችን ማለፍ ሲችሉ ብቻ ነው ብለዋል።
- ሁሉንም ያሳተፈና በመስማማት መንፈስ የሚካሄደው ሀገራዊ ውይይት፤ በግጭቱ ምክንያት ለተጎዱ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ማህበረሰቦች ያለውን ሸክም ከማቅልለ አንጻር ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።
- የኢትዮጵያ፣ የቀጠናውና የአህጉሪቱ ብልፅግና፤ ዘላቂ በሆነ ሰላም እና ደህንነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። አንድ ላይ ሆነን የተሻለ ዓለም መፍጠር እንችላለን ብለዋል።
ምንጭ፦ State House Kenya

#Borana
የኢትዮጵያጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስጣናት በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ ጉብኝት እያደረጉ ነው።
የጠ/ሚ ፅ/ቤት ጉብኝቱ ፥ " በድርቅ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ተግዳሮቶች በጥልቀት ለመገምገም " እንደሆነው ገልጿል።
ፅ/ቤቱ የዝናብ ውሀ እጥረት መከሰቱ የእንስሳት መኖ እጥረት እና የውሃ አቅርቦት ውስንነትን ጨምሮ በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎችን ማስከተሉን አሳውቋል።
በሌላ መረጃ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ያቤሎ ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መጎብኘታቸው ተገልጿል።