TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia, #WestGuji 📍

በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በሸኔ በመከበቡ ውሎ መግባት አስቸጋሪ መሆኑን አመለከቱ።

ነዋሪዎች የታጣቂ ቡዱን በርካታ የወረዳውን ቀበሌዎችን መቆጣጠሩን በመግለፅ ሰዎች እንደሚገደሉ፣ ንብረትም እንደሚወድም እና እንደሚዘረፍ ገልፀዋል።

ወረዳው ነዋሪ ፦

" ያለንበት ሁኔታ አሰቃቂ እና ተስፋ የሌለው ነው።

በአሁን ጊዜ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ነን። ታጣቂዎች ቤት አይሉ ማህበረሰቡ የሚገለገልባቸው የመንግስት ተቋማንት እያቃጠሉ እና እያወደሙ ነው። 

በየቀኑ የ4 እና 5 ሰዎች መገደል ይሰማል። አርሶ አደር በከብቶቹ መሃል ይገደላል።

ተሽከርካሪ እንደልብ አይንቀሳቀስም ይዘረፋል። ለማን አቤት እንደምንል አናውቅም እያለቅን እየተሰቃየን ነው። " 

ሌላ ነዋሪ ፦

" ከወረዳው ከታጣቂዎች ንፁህ የሚባለው ሁለት ቀበሌ ብቻ ናቸው።

እዚህ ደረጃ ከደረሰ ቆይቷል። የወረዳ የፀጥታ ኃላፊን ጨምሮ ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሻዎች፣ የቀበሌ ሊቀመንበሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልቀዋል "

የገላና ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሞርከታ ሴሮ ፦

" እነዚህ ታጣቂዎች የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው።

እንቅስቃሴያቸውን መግታት አልቻልንም ስለዚህ ችግሩ በጣም እየከፋ በመምጣቱ እኛም ለመንግስት አካል አመልክተናል።

በተለይ የወታደር ኃይል ገብቶ ይህን ኃይል እንዲመታው እና ህብረተሰቡ በነፃነት ወጥቶ እንዲገባ የሚደረግበትን ሁኔታ እየፈጠርን ነው።

ሁኔታው ትንሽ ከበድ ይላል። እውነቱን ለመናገር የወረዳው ብዙ ቀበሌዎች ላይ ገብተዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይገባሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገርን ነው። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Gelana-Woreda-02-01
#WestGuji

ትላንት በምዕራብ ጉጂ ዞን ጤና ፅ/ቤት የCOVID-19 ክትባት ዘመቻ ስራ የማስጀመር ፕሮግራም ተካሂዷል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ የተሳተፉት አባገዳዎች ፤ የዕምነት ተቋማት ተጠሪዎች እና የተለያዩ አካላት ናቸው ።

ክትባቱን ዕድሜያቸው ከ 18 ዕድሜ በላይ የሚሰጥ ሲሆን ክትባቱን በመውሰድ ያስጀመሩት አባ ገዳ እና የ ዕምነት ተቋማት መሪዎች የሚመለከተው አካል በሙሉ ክትባቱን እንዲወስዱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ ፦ ምዕራብ ጉጂ ጤና ፅ/ቤት

@tikvahethiopia