TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መምህራን

" ለልማት በሚል ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው " - መምህራን

" እውነት ነው። ከህግ አግባብ ውጪ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር

የደመወዝ በወቅቱ አመከፈል፣ የጥቅማጥቅም ክፍያ አለማግኘት ችግር ባልተቀረፈበት ሁኔታ፣ ያለፈቃዳቸው ከደመወዝ ለልማት በሚል እየተቆረጠባቸው መሆኑን መምህራን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

መምህራኑ በሰጡት ቃል፣ " ለልማት በሚል እስከ 50 በመቶ ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው። የወር አስቤዛን በቅጡ ከማይሸፍን ደመወዝ ላይ እየተቆረጠ እንዴት ቤተሰብ እናስተዳድር ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

ይህ የመንግስት ድርጊት ሰንበትበት እንዳለ ገልጸው፣ ጭራሽ ቤተሰብ ማስተዳደር አቅቷቸው በብድር እየማቀቁ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

መምህራኑ ያቀረቡት ቅሬታ እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበለት የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር፣ " እውነት ነው ችንሩን በደንብ ነው የምናውቀው "  ብሏል።

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " በየክልሉ የተለያየ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ። ያለመምህራን ፈቃድ የደመወዝ  ቆረጣም በጣም #ትክክል ያልሆነ፣ #ጉልበተኝነት የበዛበት፣ #ሰሚ ያጣ ነው " ብለዋል።

ታዲያ ለቅሬታው ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ትክክል አይደለም ብለን እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድርሰናል። ባለፈው ነሐሴ ወር በነበረን ውይይት " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አሁንም በተለይ ዳውሮ ዞን የሚገኙ መምህራን እንደሚያለቅሱ፣ ማኀበሩም ለትምህርት ሚኒስቴር እንዳሳወቀ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ያለፈቃዳቸው ደመወዝ እንዳይቆረጥ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ደብዳቤ እንደጻፈ፣ ክልሉም ደመወዛቸው እንዳይቆረጥ ለሚመለከተው አካል እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

" ዞኑ ላይ 'ለማዕከል ግንባታ' በሚል ለዛ ነው ደመወዛቸው እየተቆረጠ ያለው። መምህራኑም እዚህ ድረስ መጡ። እኛም ለእንባ ጠባቂ ተቋም ደብዳቤ ጻፍን። የተለያዩ አካላትን ለመድረስ ጥረት አደረጉ። ግን እንባ ጠባቂም ምን ያህል ኃላፊነቱን እንደተወጣ አላውቅም " ነው ያሉት።

" በእኛ በኩል ያላረግነው ነገር የለም " ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ " ግን አሁን ህግ የሌለ በሚስል ሁኔታ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " ብለዋል።

መምህራኑ ደመወዛቸውን ቀድመው ለተለያዩ ፕሮግራሞች ከፋፍለው የሚጠቀሙበት ብቸኛ ገቢያቸው እንደሆነ ገልጸው፣ " መካከል ላይ ደመወዝ ሲቆረጥ ምስቅልቅል ይወጣል " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህንን የማያይ ምን አይነት የዞን አመራር እንዳለ አይገባኝም በበኩሌ። እጅግ በጣም ጫፍ የወጣ ስልጣን መጠቀም እንደሆነ ነው የምረዳው። መምህራን እየተሰቃዩ ነው የሚያዳምጣቸው አጥተዋል " ሲሉ አክለዋል።

ምን ያህል መምህራን ናቸው ደመወዝ የተቆረጠባቸው ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ሽመልስ፣ " ለምሳሌ ዳውሮ ላይ የዞኑ መምህራን በሙሉ ተቆርጦባቸዋል። ኦሮሚያ ላይ የ230 ሺህ መምህር ይቆረጣል ደመወዙ " ነው ያሉት።

የሚቆረጠው መጠን በሁሉም ቦታ እንደየሁኔታው እንደሚለያይ አስረድተው፣ የክልል መንግስታት በማናለብኝነት ደመወዝ መቁረጥ አግባብነት እንደሌለው ቆም ብለው እንዲያስቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመምህራኑን ቅሬታ በተመለከተ ምን ሀሳብ እንዳለው በቀጣይ የመረጃ የምናደርሳችሀ ይሆናል።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ…
#OLF

🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ መንግስት በተለዬ መልኩ ጫና እያደረሰብን ነው ” ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ ወቀሰ።

ፓርቲው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በዚህም በወቅታዊ እና በአገራዊ ጉዳዮች እንደ ፓርቲ ያለውን ግምገማና የመፍትሄ ሀሳብ አጋርቷል።

Q. ስለ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፓርቲው ግምገማ ምንድን ነው ?

ኦነግ ፦

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ብቻ የሚዘወር ከመሆኑም ባሻገር ፓርቲዎችን ያገለለ ነው። ገና ከጅምሩ ብዙ መንገራገጮች አሉበት።

በአዲስ አበባ ደረጃ በተካሄደው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ፓርቲያችን አልተሳተፈም። 

በምክክሩ መፍትሄ አዘል ውጤት ለማምጣት ሂደቱ አሳታፊ ሊሆን ይገባል። ካልሆነ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ተካሂዷል እንዲባል ብቻ የይስሙላ ይሆናል።

Q. እንደ ፓርቲ ከመንግሥት የሚደርስባችሁ ጫና አለ ? ካለ ምንድን ነው?

ኦነግ ፦

መንግስት ከሌሎች በተለዬ መልኩ ጫና እያደረሰብን ነው።

በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አመራሮች ደጋፊዎች በእስራትና እንግልት ከፍተኛ ጫና ይደርስባቸዋል።

የፓርቲያችን ተሽከርካሪዎች እና ሌሎችም ንብረቶች ተዘርፈዋል። ለጉዳዩ የተለያዩ የሚመለከታቸውን ተቋማትን እያነጋገርን ነው።

ይህ ብቻ ሳይሆን እንደ ህጋዊ ፓርቲ ተንቀሳቅሰን ለመስራት እና የፓርቲውን አባላት ፣ ደጋፊዎቻችን ለማግኘት ሁኔታዎች እየፈቀዱልን አይደለም። 

ቢሯችን ገብተን መስራት አልቻልንም። በጥቅሉ ከፍተኛ ጫና ነው የሚደርስብን።

Q. የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ቦታቸው መገደላቸው የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው። ፓርቲው ስለጉዳዩ ምን እየሰራ ነው ?

ኦነግ ፦

የጃል በቴን ግድያ በተመለከተ በወቅቱ መግለጫ ከማውጣት ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራን ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን (ኢሰመኮ) ጨምሮ ከሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ምርምራው እንዲቀጥል እየተነጋገር ነው።

Q. በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የፍጥ ያነገቡ ኃይሎች አሉ። የሰው ልጅ ህይወት እየተቀጠፈ ነው። መፍትሄው ምንድን ነው ?

ኦነግ፦

ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ለሀገሪቱ ሰላም ይበጃሉ ያልናቸውን የመፍትሄ ሀሳቦች እያቀረብን ቆይተናል።

መንግስት ግን የመፍትሄ ሀሳቦቹን ወደ ጎን መተውን መርጧል።

በዚህም በአማራ፣ በኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር አሁን ካለበት አስከፊ ደረጃ ደርሷል።

ግጭቶቹን ለማስቆም ነፍጥ ያነሱ ኃይሎች እገዛ ማስፈለጉ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት ግን ግጭቱን የሚፈልገው ይመስላል። 

የኦሮሚያም ሆነ የአማራ ህዝብ በመካከል ከፍተኛ ጉዳት እየተደረሰበት፣ መጥፎ የሚባል ጊዜ እያሳለፈ ነው።

Q. በቀጣዩ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ የምታደርጉት ዝግጅት ምን ይመስላል ?

ኦነግ ፦

ለቀጣዩ ምርጫ እንዲካሄድ በመጀመሪያ ሰላም መስፈን አለበት። ሰላም ሲሰፍን ነው ሁሉም ነገር ሁሉም ነገር በሰላም የሚካሄደው።

የምናደርጋቸው ዝግጅቶች ይኖራሉ። ግን የምርጫ ጊዜ ሲደርስ ጊዜው ራሱ ቢነግረን ይሻላል። ያለንን የዝግጅት ሂደት ወደ በቀጣይ እንገልጻለን።

---

የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? የሌሎች ፓርቲዎች ምልከታም ይቀጥላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ፦
- እናት
- ነእፓ
- ኢዜማ
- ጎጎት
- ሕብር
- ኦፌኮ ፓርቲዎችን በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምልከታቸውን እንዲያጋሩ ማድረጉ ይታወሳል።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Urgent🚨

እየደበደቡት ጥርሱን አውልቀውታል። ሙሉውን ቪዲዮ ለመመልከት ሰቀጠጠኝ። አጋቾቹ 800 ሺሕ ብር ጠይቀዋል” - እርዱኝ ያሉ የታጋች ወንድም

በባህር ዳር ዩቨርቨሲቲ የ4 ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ የነበረው ወጣት ሙላት ተቀባ አስረሴ በሊቢያ በአጋቾች ተይዞ በድብደባ አካላዊ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን ቤተሰቦቹና የቅርብ ሰዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የታጋች ወንድም አቶ ደጉ ተቀባ አስረሴ፣ “ ጎንደር ጦርነት ስላለ ገንዘቡን ለመላክ ተንቀሳቅሶ መስራት አልተቻለም። ቦታ ነበረችኝ ለመሸጥ እንኳ በዚሁ በጸጥታው ችግር ገዢ የለም። እባካችሁ ወንድሜን አድኑልኝ ” ሲሉ ተማጽዋል።

ታጋቹ ያለበትን ሁኔታ ሲገልጹም፣ “ እየደበደቡት ጥርሱን አውልቀውታል። ሙሉውን ቪዲዮ ለመመልከት ሰቀጠጠኝ። አጋቾቹ 800 ሺሕ ብር ጠይቀዋል። ገንዘቡን መላክ አልቻልኩም። ወላጆቻችን አዛውንቶች ናቸው ” ነው ያሉት።

በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አቃቢ ሕግ በመሆን ተቀጥረው እንደሚሰሩ ገልጸው፣ አሁን ባላቸው አነስተኛ ደመወዝ የተጠየቀውን ገንዘብ ማሟላት እንደማይችሉ አስረድተዋል።

“ አጋቾቹ ‘ቶሎ ካላክ እንገለዋለን እያሉኝ’ ነው ” ያሉቴ አቶ ደጉ፣ ወጣቱ ዘንድሮ ተመራቂ እንደነበር፣ ወደ አውሮፓ ድንበር ሊያቋርጥ ሲል ከታገተ ወራቶች እንዳስቆጠረ ገልጸዋል።

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሁለት የታጋቹ የቅርብ ጓደኞች በበኩላቸው፣ ተማሪ ሙላት ታግቶ እየተደበደበ እንደሆነ፣ ከዩኒቨርሲቲው ደብዳቤ አጽፈው ገንዘብ እያሰባሰቡ መሆኑን ነግረውናል።

ከጓደኞቹ አንዱ በሰጠው ቃል፣ “ ተማሪ ሙላት ወደ አውሮፓ ሊወጣ ሲል ታግቶ ይገኛል። እንደኛ ተመራቂ ነው የነበረው በዚህ ዓመት። የሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ነዋሪ ነው ” ብሏል።

የታጋቹ ወንድምና ጓደኞቹ፣ ታጋቹ በአጋቾች እየደረሰበት ያለውን ስቃይ የሚያሳይ ቪዲዮ የላኩ ሲሆን፣ ከላይ ተያይዟል።

መርዳት ለምትሹ 1000281326795 የአቶ ደጉ ተቀባ አስረሴ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው። አቶ ደጉን በዚህ ስልክ 0931494332 ማግኘት ይቻላል።

የፖሊ ግቢ ተማሪዎችም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000660181036 እና በአቢሲንያ ባንክ 209476797 አካውንት በመክፈት ድጋፍ እያሰባሰበ ነው።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia