TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TikvahFamily

ስለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ፦

• ቲክቫህ/ተስፋ ኢትዮጵያ ሰውነትን ያስቀደሙ ሁሉንም የሰው ፍጡር፣ ህዝብን እና ሀገርን የሚያከብሩ ፣ በማንኛውም ጉዳይ ሚዛናዊ አመለካከት ያዳበሩ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።

• የቤተሰቡ አባላት መረጃ ማካፈል፣ አንዱ ያልሰማውን ሌላው እንዲሰማው መጠቆም ፣ በሚዲያ ላይ የሚከታተሉትን ሌላው የቤተሰቡ አባል እንዲያውቀው ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ የቤተሰብ አባላቱ እርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው። (ምንጭ በመጥቀስ)

• በቤተሰቡ / አባላት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ የሚቻል ሲሆን አንዲት ቃል ስድብ ሆነ የሰዎችን ክብር ፣ ሃይማኖት፣ ብሄር ማንነትን የሚነካ መልዕክት መላክ ከቤተሰቡ ወዲያው በቀጥታ ያስቀንሳል።

• ቲክቫህ ኢትዮ. ከተመሰረተ አንስቶ ከማንም ወገን ፣ ከየትኛውም አካል (የመንግስት ሆነ ተቃዋሚ፣ አልያም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት) ጋር ግንኙነት የሌለው ሲሆን በየትኛውም አካል አይደግፍም፤ አይታግዘም። ለስራ በሚል ከቤተሰቡ ገንዘብ አይጠይቅም አያሰባስብም።

ተቋርጠው የነበሩ የቤተሰቡን ስራዎች ስለማስቀጠል ፦

- ባለፉት ሁለት ክረምቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ዓመታዊ ለገጠር ት/ቤቶች የሚደረገው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እና የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ አመት ለማስቀጠል ዝግጅት ተደርጓል።

- ሲቆራረጥ የነበረው ለግለሰቦች የሚደረግ የህክምና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻም በዚህ ዓመት የሚጀምር ሲሆን ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ስራው ይሰራ የሚለውን ሃሳብ ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

- ከዚህ ቀደም በቤተሰቡ አባላት የሚተላለፉ አጭር የቅሬታ ፣ የጥቆማ፣ የፀጥታ ችግር ማሳወቂያ ፣ ትችት፣ ጥያቄ በስፋት መላክ ይቻላል። እንደከዚህ ቀደሙ መልዕክት ሲላክ አጭር ከጥላቻ ሃሳብ የፀዳ እና የመፍትሄ ሃሳብንም የሚጠቁም ሊሆን ይገባል።

- ለጀማሪ ወጣቶች ላለፉት ዓመታት ክፍት የተደረገው የነፃ ማስታወቂያ ስራም በዚህ ዓመት ይቀጥላል። በግል ሆነ ተደራጅተው እራስን ሆነ ሀገርን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ወጣት የቤተሰቡ አባላት ስራቸውን ሆነ አገልግሎታቸው በነፃ ያለምንም ክፍያ ለሌሎች የቤተሰቡ አባላት ማስተዋወቅ ይችላሉ መብታቸውም ጭምር ነው። ነገር ግን በሚሰሩት ስራ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል።

- በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥ ያሉ የቤተሰባችን አባላት እንዲሁም ደራስያን መፅሀፍቶቻቸውን በነፃ ለቤተሰባችን እንዲያስተዋውቁ የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመት የሚቀጥል ይሆናል።

#ማሳወቂያ፦ የ "ዕርቅ ሀሳብ አለኝ" በሚል በቲክቫህ አስተባባሪነት የተካሄደው ሀገር አቀፍ በሀገር በቀል ባህላዊ የዕርቅ ስነስርዓት ላይ ባተኮረው ውድድር ላይ የቀረቡ ፅሁፎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደቤተሰቡ ይላካል።

#ማሳሰቢያ ፦ ማስታወቂያን በተመለከተ በቀን እጅግ ውስን ማስታወቂያ ለቤተሰቡ ይላካል ፤ የሚላከው ማስታወቂያ ጠቃሚ እና ህጋዊ ሲሆን ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የሚያስነግሩትም የቤተሰቡ አባላት በመሆናቸው የእርስ በእርስ ተውውቅን ያጎለብታል። በዚህ መሃል ችግር ቢፈጠር በማስታወቂያ ስም ማጭበርበር ቢሰራ ድርጅቱን ከነስሙ የምናጋልጥ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላትን ገንዘባቸው እንዲመለስ ይደረጋል። ድርጅቱም ከቤተሰቡ ይቀነሳል።

#ከአጭበርባሪዎች_ተጠንቀቁ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
- " Tikvah Mart "
- " Tikvah Market "
- " Tikvah Business " በሚሉ አድራሻዎች/ቦታዎች አይሰባሰቡም። በእነዚህ ገፆች የሚተላለፉ ሁሉ ሀሰተኛ መልዕክቶች ናቸው። በማስታወቂያ ስም ገንዘብም እንደሚቀበሉ ደርሰንበታል ፤ ከዚህ በፊትም እንዳልነው ተጠንቅቋቸው። ቻናሎቹንና ግሩፖቹን ለቴሌግራም ሪፖርት አድርጉ ፤ ይህን ስራ ለመስራት የሚጠቀሙበትን የስልክ ቁጥር ካላቸውም ላኩልን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ ምንም አይነት የ #Youtube#TikTok#Facebook አካውንት የለም።

መልዕክት ማስቀመጫ ፦ @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#TikTok #Kenya

በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ከኩባንያው ጋር መስማማቷን ሀገሪቱ ማስታወቋን ቪኦኤ ዘግቧል።

ስምምነቱ የተደረሰው " ቲክቶክ ያልተገቡ ቪዲዮዎችን ያሰራጫል " በሚል እንዲታገድ ከአንድ ግለሰብ ለሀገሪቱ ፓርላማ ከቀናት በፊት ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡

የአጭር ቪዲዮ ማጋሪያው ኩባንያ ቲክቶክ፣ በመድረኩ ላይ የሚወጡትን ቪዲዮዎች መቆጣጠርን በተመለከተ ከኬንያ ጋር በጋራ ይሠራል ሲል የፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጽ/ቤት አመልክቷል።

ይህን በተመለከተም ከኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾ ዚ ችው ጋር መነጋገራቸውን ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል።

በስምምነቱ መሠረት፣ " ያልተገቡ ናቸው " የሚባሉ ቪዲዮች ከመድረኩ እንደሚወገዱ ታውቋል።

በአፍሪካ በቲክቶክ ላይ የሚወጡትን የቪዲዮዎች ይዘት በተመለከተ ቁጥጥር ለማድረግ ኩባንያው በኬንያ ቢሮ እንደሚከፍት ዋና ሥራ አስፈጽሚው ሾ ዚ ችው ይፋ ማድረጋቸውም ታውቋል።

ቲክቶክ ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዊታንጉላ ፤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦
- ግጭቶችን በማባባስ፣
- ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣
- የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣
- የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣
- አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ነበር።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፤ ህዝቡንም እያሳሳተ ነው በሚል ቲክቶክ እንዲታገድ አዛለች። እግዱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በተመሳሳይ ቴሌግራምም እንዲታገድ ውሳኔ ከተሰጠባቸው መተግበሪያዎች አንዱ ነው።

ሶማሊያ አሸባሪ ድርጅቶችና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውሏል በሚል ነው እንዲታገዱ ያዘዘችው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ ለምንድነው ሀገራት " ቲክቶክ " ን ለማገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ? ከቅርብ ወራት ወዲህ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ ያሉ የህግ አውጪዎች ከፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ጋር በማያያዝ ግዙፉን የአጫጭር ቪድዮዎች ማጋሪያ " ቲክቶክ " ን ለማገድ / ለመገደብ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል። ዋይትሃውስ እኤአ በፌብሩዋሪ 27 የፌዴራል  ኤጀንሲዎች አፕሊኬሽኑን ከመንግሥት…
#USA #TikTok

" ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " - ግሌን ያንግኪን

በአሜሪካ የቨርጂኒያ ግዛት ገዥ ግሌን ያንግኪን ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች " ቲክቶክ "ን እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳወቁ።

ያንግኪን ፤ " ቲክቶክ " የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ለህጻናት ልጆቻችን አእምሮአዊ ጤንነት እጅግ ጎጂ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሪፐብሊካኑ ሰው ወደዚህ እርምጃ እንደሚመጡ ያሳወቁት ባለፈው አመት ቲክቶክን ከማንኛውም የመንግስት ኤሌክትሪክ መሳሪያዎች እና ዋይፋይ #ካገዱ በኋላ ነው።

ያንግኪን ፤ በአጠቃላይ ማህበራዊ ሚዲያ በልጆቻችን ላይ ከባድ እና ቀጣይነት ያለው አሉታዊ ተጽእኖዎች እያሳደረ ነው ብለዋል።

ከነዚህም ውስጥ ፦
- የማህበራዊ ክህሎታቸው እንዲያጡ ፣
- በሳይበር አማካኝነት የማዋረድ፣ ስድብና ሌላም ጎጂ ድርጊት እንዲደርስ፤
- የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲስፋፋ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አመላክተዋል።

በመሆኑም " ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቲክቶክ " ን ልጆች እንዳይጠቀሙ ከሚያግደው ረቂቅ በተጨማሪ ልጆች ከማህበራዊ ሚዲያ ግብይት እና መረጃዎቻቸውን ከመጠቀም እና ከመሸጥ የሚከላከሉ ህጎች እንደሚያወጡ ገልጸዋል።

የቨርጂንያው ገዥ " ሱስ አስያዥ " ብለው ከጠሯቸው የማህበራዊ ሚዲያ የማርኬቲንግ ስልቶች ልጆችን እና ታዳጊዎችን ለመጠበቅ የሚረዱ ረቂቆችን ይፋ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ቢሆንም " መቼ ? " የሚለውን አልገለፁም።

በአሜሪካ እንደ አጠቃላይ እስካሁን " ቲክቶክ " ባይታግደም፤ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ግን ተደጋጋሞ ተነግሯል።

በተለይም በርካታ የሪፐብሊካን ዕጩዎች በቀጣይ ምርጫ አሸንፈው ፕሬዜዳንት መሆን ከቻሉ በአጭር ጊዜ መተግበሪያውን ለማገድ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በተለያዩ ግዛቶች ደግሞ ከደህንነት እንዲሁም ወጣቶችን ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ " ቲክቶክ " ከመንግሥት የኤሌክትሪክስ መሳሪያዎች ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጅ ካምፓሶች ዋይፋይ እንዲታገድ ተደርጓል።

" ቲክቶክ " ባለቤት የሆነው የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ በተለያየ ጊዜ የሚነሳበትን ወቀሳ ውድቅ ሲያደርግ መቆየቱ እየሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
" ' ሳር ቤት አካባቢ በአውቶብስ ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ ' እየተባለ በቲክቶክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።

ፖሊስ ፤ የከተማው ሰላም መሆን እንቅልፍ የነሳቸው አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች የተለያዩ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ስጋት ላይ ለመጣል በቻሉት መጠን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።

እነዚህ አካላት ህዝቡ ደህንነት እንዳይሰማውና ከተማውም ሰላም አንደሌለው ለማሳየት ብዙ ሞክረው አልሳካ ሲላቸው የፈጠራ ሀሰተኛ ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ይዘው መጥተዋል ሲል ገልጿል።

ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ የተደራጀ ቡድን እንዳለ በማስመሰል ሳር ቤት አካባቢ አውቶቡስ ላይ #ቦንብ_ማፈንዳቱን የሚገልፅ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል።

" ይህ ከእውነታ የራቀ በአዲስ አበባ ሰላም የለም ለማስባል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ ነው " ያለው ፖሊው ሁሉም የከተማው ነዋሪ ይህን ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።

ፖሊስ ፤ የከተማዋን ሰላም የማይፈልጉ አካላት የሌት ተቀን ህልማቸውን " ቲክ ቶክ /#TikTok " በተባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየገለፁ ናቸው ብሎ " በአዲስ አበባ ያለው ሰላም አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ስራውን እያከናወነ ይገኛል " ሲል ገልጿል።

ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያዳብር እንደሚገባ አሳስቧል።

ሀሰተኛ መረጃን በሚያሰራጩ አካላት ላይም በህግ አግባብ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#TikTok #USAHouse

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል/ፓኬጅ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።

" ቲክቶክ " በአሜሪካ እንዲታገድም ድምጽ ሰጥቷል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ድምፅ የሰጠው በ " #ቲክቶክ " ጉዳይ ሲሆን ባለቤትነቱ የባይትዳንስ የሆነው መተግበሪያ ለአሜሪካ ኩባንያ ካልተሸጠና ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቋረጠ በመላው አሜሪካ ውጤታማ በሆነ መንገድ #ለማገድ 360 ለ 58 በሆነ ድምጽ ረቂቅ ሕግ #አጽድቋል

" ቲክቶክ " በአሜሪካ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።

በመቀጠል ምክር ቤቱ ፦

➡️ ለዩክሬን 60.8 ቢሊዮን ዶላር (3,422,796,000,000 ብር)፤

➡️ ለእስራኤል 26.4 ቢሊዮን ዶላር  (1,483,211,600,000 ብር)፤

➡️ ለታይዋን እና ለኢንዶ ፓስፊክ ሀገራት  ' ቻይናን ለሚጋፈጡ ' የ8 ቢሊዮን ዶላር (456,372,800,000 ብር) የእርዳታ ድጋፍ በድምሩ የ95 ቢሊዮን ዶላር ጥቅል እርዳታ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።

የምክር ቤቱ አባላት የዩክሬን ድጋፍ ሲጸድቅ ፤ " ዩክሬን !! " እያሉ በመጮህ የሀገሪቱን ባንዲራ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።

@thiqahEth @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ ላይት " ጥያቄ ቀረበበት። አዲሱ መተግበሪያው ' ቲክቶክ ላይት ' በፈረንሳይ እና ስፔይን አገልግሎት የጀመረው ቲክቶክ በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ያለውን ግምገማ በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲያቀርብ ዛሬ የአውሮፓ ኮሚሽን ጠየቀ። ከዋናው ቲክቶክ መተግበሪያ አነስ ብሎ የወጣው የቲክቶክ መተገበሪያ ተጠቃሚዎች #ተከፍሏቸው የቪዲዮ ምስሎችን እንዲመለከቱ…
#TikTok #EU

" የቲክቶክን አደጋ በትክክል እናውቃለን " - ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን

' ቲክቶክ ' አውሮፓ ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተሰማ።

ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ' ቶክቶክ ' በመላ ሀገሪቱ እንዲታገድ አልያም ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ ሕግ ማውጣቷ ይታወቃል። ለዚህም የሰጠችው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

አሁን ደግሞ መተግበሪያው የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተነግሯል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ለኮሚሽኑ የ2024 ምርጫ በተደረገ አንድ ክርክር ላይ ' ቲክቶክ ' በአውሮፓ ሀገራት የመታገድ ዕጣፋንታው ዝግ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ይህን ያሉት የአሜሪካ ' ቲክቶክ ' ን የማገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሷን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው።

ቮን ደር ሌየን ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም በተቋሙ ስልኮች ላይ መተግበሪያው እንዳይሰራ ያደረገ የመጀመሪያ ተቋም መሆኑን አስታውሰዋል።

" የቲክቶክን አደጋ በትክክል ምንእንደሆነ እናውቃለን " ሲሉ አክለዋል።

ምንም እንኳን የአውሮፓ ኮሚሽን አውሮፓ ሀገራት ውስጥ ' ቲክቶክ ' ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ቢሰጥም ልክ እንደ አሜሪካ በፍጥነት ተመሳሳይ መንገድ ይከተል እንደሆነ ለመደምደም ገና ነው ተብሏል።

የአውሮፓ ኮሚሽን በቅርቡ ከዋናው ቲክቶክ አነስ ብሎ የተዘጋጀው ' ቲክቶክ ላይት (ተጠቃሚዎች ተከፍሏቸው ቪድዮ የሚያዩበት) ' በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ጥያቄ ማንሳቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Australia የአውስትራሊያ የተወካዮች ም/ቤት ከ16 ዓመት በታች ያሉ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ በሃገሪቱ የእንደራሴዎች ም/ቤት (ሴኔት) ከጸደቀ በዓለም የመጀመሪያው ይሆናል። የተወካዮች ም/ቤቱ በ102 ድጋፍ እና 13 ተቃውሞ ድምጽ አጽድቆታል። በሃገሪቱ የሚገኙ ዋና ፓርቲዎች የደገፉት ሕግ ፦ ➡️ ቲክቶክ፣ ➡️ ፌስቡክ፣ ➡️ ስናፕቻት፣ ➡️ ሬዲት፣…
#ቲክቶክ #ስናፕቻት

በአልባኒያ አንድ የ14 ዓመታ ታዳጊ ልጅ ትምህርት ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ከተገደለ በኃላ የሀገሪቱ መንግሥት ቲክቶክ እና ስናፕቻትን እስከወዲያኛው ለማገድ ሊያቅድ እንደሚችል ተነገረ።

ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በዋና ከተማዋ ቲራና በሚገኝ ፋንኖሊ በተባለ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በሌላ ተማሪ በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሏል።

ተማሪዎቹ ክርክራቸው እና አለመግባባታቸው የጀመረው በማህበራዊ ሚዲያ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ ጠ/ሚ ኢዲ ራማ ባለፈው ሳምንት ከሀገሪቱ የካቢኔ ስብሰባ በኃላ በሰጡት ቃል ፤ " አሰቃቂው የታዳጊው ሞት ከመንግሥት እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጠንካራና ውጤታማ ምላሽ የጠየቀ አሳዛኝ ክስተት ነው " ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ቲክቶክ እና ስናፕቻት የተባሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን " እስከመጨረሻው ድረስ ሀገሪቱ ላይ ለማገድ እናስብበት ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።

አንዳንድ ሀገራት ከ16 አመት በታች ለሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽነትን እንደሚገድቡ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ሀገሪቱ የማጣሪያ መንገዶች (ለልጆች የማይሆኑትን ማጣሪያ ሲስተም) ውጤታማ ከሆኑ በሚል ሲታዩ ቢቆዩም ውጤት አልባ እንደሆኑ ገልጸዋል።

" ይልቅም የኦንላይን ጥቃት ፣ ሰዎችን ማዋረድና ማጥቃት እየጨመረ መጥቷል " ብለዋል።

ራማ ቲክቶክ እና ስናፕቻትን እስከመጨረሻ የማገድ ሃሳቡ ከወላጆች እና ትምህርት ቤቶች ጋር ውይይት እንደሚደረግበት ጠቁመዋል።

ይህም የውሳኔ አሰጣጡ ሂደት በተቻለ መጠን ዲሞክራሲያዊ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

#TikTok #Snapchat #Albania

@tikvahethiopia