TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update  ባጋጠመው የበጀት እጥረት ውዙፍ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መክፈል አለመቻሉን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታውቋል። ከፌደራል መንግስት ያልተላከ በጀት ጨምሮ የ300 ሚሊዮን ብር የበጀት ጉድለት አለበኝ ብሏል የጊዚያዊ አስተዳደሩ በፋይናንስና ሃፍት አሰባሰብ አስተዳደር ቢሮ በኩል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ።  የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ምሕረት በየነ እንዳሉት ፤ የተላከው በጀት ከ4 ዓመት…
#መምህራን

" የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን እንዲከፍለን እንጠይቃለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር

የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የመምህራንን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፍል ጠየቀ።

ማህበሩ ይህን ያለው ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ነው።

ማህበሩ ፤ " የመምህራን መብትና ጥቅማ ጥቅም ሲከበር የትምህርት ጥራት ይረጋገጣል " በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፤ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም በውቕሮ ከተማ ባካሄደው አስቸኳይ የምክክር መድረክ ከመምህራን የደመወዝ ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ የሚፈታበት አቅጣጫ አስቀምጧል።

ከመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ የደመወዝ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ባለፉት ቀናት የ33 የመንግስት ትምህርት ቤቶች መምህራን ስራ ሲያቆሙ ፤ የተቀሩ ስራ ለማቆም ፊርማ የማሰባሰብ ስራ በማካሄድ ላይ መሆናቸው መግለጫው ገልፆ ፤ ችግሩ ይፈታሉ ያላቸው 8 ነጥቦች ዘርዝሯል ፦

1. የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት የተላከው የ2015 ዓ.ም ውዙፍ የ5 ወር ደመወዝ " በቅርብ ቀን እከፍላለሁ " እያለ እስከ አሁን አለመክፈሉ መምህራንን ችግር ላይ ስለጣለ አስተዳደሩ ይህንን ችግር በመረዳት ውዙፍ ደመወዙ እንዲከፍል ወይም ቁርጥ ቀን እንዲያስቀምጥ፤

2. የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሚመራውን መምህርና ትምህርት በቅጡ በመረዳት የመምህራን ጥያቄ እንዲመልስ፤

3. የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የ2014 ዓ.ም የ12 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፍል፤

4. በመቐለ በአንድ ክፍለ ከተማ የተጀመረው የመኪና የሰርቪስ አገልግሎት በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንዲጀመር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቅጣጫ እንዲሰጡ፤

5. ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም በክልሉ የፋይናንስ ፣ የሃብት ማሰባሰብ አስተዳደርና የትምህርት ቢሮዎች የተሰጠው መግለጫ ጊዜው ያልጠበቀና ውዝግቡ ከመፈጠሩ በፊት መሰጠት የነበረበት ነው፤

6. መምህራን ለቤት መስሪያ ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ ሌሎች ባንኮች ከወሰዱት ብድር ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም ያለው ደመወዝ ያልነበረበት መሆኑ እየታወቀ ክፈሉ መባሉ አግባብ ስላልሆነ የመምህራንን ችግር ከግምት በማስገባት ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው አበዳሪ ተቋማት በመወያየት የብድር ወለድ #እንዲሰረዝ

7. ከ1 እስከ 6 የተዘረዘሩ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ ባጠረ ጊዜ መልስ ካልተሰጠ እስከ ጥር 15/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት በክልል ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል።

8. የመምህራን ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ፤ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለትውልድ ሲባል ከታህሳስ 18/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቀጥል መምህራን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማህበሩ ውሳኔ አሳልፏል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia            
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የ4 አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት #እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።

ሠርተፍኬታቸው የተሰረዘው ፦

1ኛ. ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ነብይ ኢዮብ ጭሮ

2ኛ. ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ካሳ ኪራጋ

3ኛ. የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ሚስጥሩ መዝገቡ

4ኛ. የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ መጋቢ  ቢንያም ሽታዬ ... ናቸው።

ውሳኔው የተለለፈባቸው በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ምክንያት ነው።

ካውንስሉ እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን የሕግ ከለላ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበሩ ገልጿል።

ከዚህ ተግባራቸው ይመለሱ ዘንድም አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ምክሩ ተቀበለው ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው #ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ሠርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ ወስኗል።

(ካንውስሉ ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia