TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጎንደር⬆️

የጎንደር ከተማ #እስልምና ዕምነት ተከታዮች #የመስቀል በዓል በከተማዋ በድምቀት እንዲከበር ቀድመው ያደመቁት እነርሱ ናቸው፡፡ የመስቀል በዓል የሚከበርበትን ቦታ ቀድመው በማጽዳት #አንድነታቸው መቼም እንደማይላላ ያሳዩበት ነው፡፡ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከትም ለከተማዋ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች #ምስጋናውን ችሯል፡፡ እውቅናም ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ትግራይ #እስልምና
 
ለዓመታት የተቋረጠው ግንኙነት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱ ተነገረ።

በአስከፊውና ደም አፋሳሽ ጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮችና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግንኙነት የቀረበውን ይፋዊ ይቅርታ ተከትሎ ግንኙነቱ ወደ ቀድመው እንዲመለስ መወሰኑ ታውቋል።

የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 2014 ዓ/ም ላይ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተለይቶ ራሱን ችሎ እንደተቋቋመ በይፋ አስታውቆ ነበር።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ጦርነቱ መቆሙን ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ግንኙነት ወደነበረበት እንዲመለስ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም አልተሳካም ነበር።

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በመቐለ ከተማ ባካሄደው #አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አቀረበ ባለው የይቅርታ ደብዳቤ ላይ ከተወያየ በኃላ በሙሉ ድምፅ በመቀበል ከሶስት አመታት በላይ የተቋረጠው ግንኙነት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል።

በደም አፋሳሹ እና አስከፊው የትግራይ ጦርነት ምክንያት በተፈጠረ መቃቃርና አለመጣጣም የትግራይ የኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ከኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን ተለይተው " መንበረ ሰላማ " በሚል የራሳቸው ቤተክህነት ማቋቋማቸው ይታወቃል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ሲሆን በነገው ዕለት ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
                                       
@tikvahethiopia            
በነገው ዕለት የዐቢይ ጾም እንዲሁም የረመዷን ወር ጾም ይጀምራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልካም የዐቢይ ጾም እንዲሁም መልካም የረመዷን ጾም እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

በነገው ዕለት የሚጀምሩት አጽዋማት የፈጣሪን በረከት ፣ ዕርቅ ፣ ምህረት ፤ ለመላው ሀገራችን ፍጹም ሰላም እና መረጋጋትን የሚያመጡ እንዲሆኑ እንመኛለን።

#ኢትዮጵያ #Ethiopia #ክርስትና #እስልምና

@tikvahethiopia