TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። መግለጫውን የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ ሲሆኑ ታንዛኒያ ውስጥ እየተካሄደ ነው ስለተባለው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ተጠይቀው ቀጥተኛ ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል። አቶ ኃይሉ ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም በክልሉ ዘላቂ ለሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ፅኑ…
" ድርድሮች መፍትሔ ይዘው የሚመጡት ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽነት የተላበሱና በአግባቡ የሚመሩ ሲሆኑ ብቻ ነው " - የ5 ፓርቲዎች የጋራ መግለጫ

መኢአድ ፣ ኢህአፓ ፣ የዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲና እናት ፓርቲ ዛሬ ከጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ፓርቲዎቹ ምን አሉ ?

- ማንኛውም የሚደረጉ ድርድሮችና ዉይይቶችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ ሊያውቃቸው ይገባል።

- ግልጽ ያልሆኑና ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ ድርድሮችና ስምምነቶች ከመድረኩ እንደተወጣ ጥያቄ የሚያስነሱ መሆናቸዉ እንዳለ ሆኖ ዉለዉ አድረዉ ወደ ከፋ ጥፋት አገርንና ሕዝብን እንደሚወስዱ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን የምንረዳዉ ጉዳይ ነዉ፡፡

ለምሳሌ ፦

* " ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ከአምስት ዓመታት በፊት አስመራ ላይ ተደረገ " የተባለዉና የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልፅ ምንነቱን ያላወቀዉ ኋላም " የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት " ብሎ ራሱን ለሚጠራዉ ታጣቂ ኃይል መፈጠር ምክንያት እንደሆነ የሚነገረዉ ድብቅ ስምምነት አንዱ ነው።

* ፕሪቶሪያ ላይ የተደረገዉና እርሱን ተከትሎ ናይሮቢ ላይ በፌደራል መንግሥት እና በሕወሃት መካከል የተደረጉ የተሸፋፈኑ ድርድሮችና ተደረሰባቸዉ የተባሉ ስምምነቶች ዛሬም ድረስ ጥያቄ የሚያስነሱና ወደፊትም ጥያቄ በማስነሳት የሚቀጥሉ ናቸዉ።

- ለፖለቲካዊ ጥያቄ ፖለቲካዊ መፍትሄ ብቻ ሊሰጥ ይገባል። ለዚህም ግልፅነት የተላበሰ ድርድር ብቸኛ አማራጭ ነው።

- ከጥቂት ቀናት ወዲህ በመንግሥትና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ድርድር እየተደረገ ነዉ " በተባለዉና የፌዴራል መንግሥት ድርድሩ ስለመታሰቡም ሆነ ስለመጀመሩ እንዲሁም የድርድሩ ተሳታፊዎችን ማንነት ባልገለፀበት ሁኔታ ላይ መረጃዎች መደመጣቸው የተደበላለቀ ስሜትና ከፍተኛ #ስጋት_አንዲሰማን አድርጓል፡፡

- አብዛኛዉ የኦሮሚያ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ በተሰነዘሩ የተለያዩ ዘግናኝ ጥቃቶች በግንባር ቀደምነት የአማራ ማኅበረሰብ ለአሰቃቂ ጅምላ ጭፍጨፋ መዳረጉ የማይታበል ሐቅ ሲሆን፤ ቀን በብልጽግና ማታ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቀንበር ሥር ወድቆ የመከራ ህይወት እየገፋ ለሚገኘዉ የኦሮሞ ማኅበረሰብም ከመከራዉ ቀንበር የሚገላገልበት የተስፋ ጭላንጭል የሚፈጥር በመሆኑ የፖለቲካ ልዩነቶች በድርድር እንዲፈቱ ዛሬም ጽኑ ፍላጎታችን ነው።

- ድርድሩ እየተካሄደበት ያለዉ መንገድ የተሸፋፈነ መሆን፣ ለድረድሩ ምክንያት የሆኑ አጀንዳዎች ይፋ አለመደረጋቸው እና ከአገራችን ሕዝብ ጀርባ እየተከናወነ የሚገኝ ድርድር መሆኑ፣ ሠላም የራቀዉ ህዝባችንን ተስፋ መልሶ የሚያጨልም የጎራ ድርድር እንዳይሆን ያለንን ስጋት እንገልጻለን።

- የአገራችን ጉዳይ በመጠነ ሰፊ ችግሮች የተሞላ ሆኖ ሳለና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ባሻገር ድርድሩ ሁሉን አቀፍ መሆን ሲገባዉ የተድበሰበሰና ቁንጽል መሆኑ ያሳስበናል።

(ከፓርቲዎቹ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

NB. ምንም እንኳን መንግሥትም ይሁን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ለሰላም ድርድር መቀመጣቸውን እስካሁን በይፋ ባያሳውቁም / ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ባይሰጡም ፤ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የዲፕሎማቲክ ሰዎች ግን የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን አሳውቀዋል። ድርድሩ እየተመራ ያለውም በጦር አዛዦች ነው።

@tikvahethiopia