TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ShabelleBank

የሸቤሌ ባንክ ምስረታ ስነ- ስርአት ተካሔደ።

የሸቤሌ ባንክ መመስረቻ ስነ ስርአት ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተካሒዷል።

በ2011 የሶማሊ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም " ሄሎው ካሽ " በሚል የገንዘብ ግብይትና ዝውውር አገልግሎት መስጠት የጀመረው ተቋሙ ለመቶ ሺህ ለሚሆኑ የአካባቢው ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሮ እያገለገለ ይገኛል።

በማይክሮ ፋይናንስነት አገልግሎቱ እስከ አሁን 1 ሚሊየን 3 መቶ ሺህ በላይ የሚደርሱ ደንበኞችን እንዳሉት ይገለፃል።

ተቋሙ በእስከ አሁን ሒደቱ በ43 የተለያዩ የአገልግሎት ማዕከላት ሲኖረው 500 ቋሚ ሰራተኞችን ይዞ በ 3.7 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ጠቅላላ የሐብት መጠን በማስመዝገብ በ2013 አመተ ምህረት ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው እውቅና ወደ እስላሚክ ሸቤሌ ባንክነት ማደግ ችሏል።

በዛሬው የባንክ በምስረታ የሐገር ሽማግሌዎች ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፣ አምባሳደር ዶ/ር መሐሙድ ድሪር ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሐሰን መሐመድ፣ የተለያዪ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#SRTV

@tikvahethiopia