TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ColonelBezabihPetros
ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ በኢትዮጲያ አየር ኃይል ታሪክ ውስጥ በብዙዎች ዘንድ የብሔራዊ ጀግና ተምሳሌት ተደርገው ይቆጠራሉ።
በተለይም በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት /ሚግ 23 ጀት በማብረርና ሞቃዲሾ ድረስ በመዝለቅ / በሰይድ ባሬ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይ ያደረሱት ተደጋጋሚ ጥቃት ዛሬም ድረስ ይነገርላቸዋል።
በ1977 ከኤርትራ ሻዕቢያ ኃይሎች ጋር በነበረ ውጊያ በናቅፋ ግንባር አውሮፕላኑ ተመቶ ወደቀ በኃላም በሻዕቢያ እጅ ገቡ ታስረውም ቆዩ በ1983 (ከ7 ዓመት በኃላ) ግን ከእስር ተፈቱ።
በኃላም ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በባድመ ድንበር ውዝግብ ምክንያት ወደ ጦርነት በገቡበት ወቅት ኮሎኔሉ ለሀገር ክብር በድጋሚ ሻዕቢያን ለመደምሰስ ዘመቱ።
የኤርትራ አየር ኃይል የኢትዮጵያን አየር ጥሶ ትግራይ ግብቶ በአይደር ትምህርት ቤት ላይ ያደረሰውን ድብደባ ለመበቀል የኤርትራን የአየር ክልል ጥሰው ገቡ።
ግን ኮሎኔሉ ሲያበሩት የነበረው ጀት ተመቶ መውደቁን ተከትሎ / በምርኮ በኤርትራ ወታደሮች እጅ ከገቡ በኋላ / እስከዛሬ ከምናልባት በስተቀር ስለአሳቸው አውነተኛ መረጃዎችን ማግኘት አልተቻለም።
ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ለሀገራቸው በኢትዮ ሶማሊ ጦርነት ሆነ ከሻዕቢያ ጋር በተደረገው ጦርነት የሰሯቸው የጀብድ ታሪኮች በርካታ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል።
ይበልጥ በእሳቸው ዙሪያ የተፃፉ ፅሁፎችን መፅሀፍትን አግኝታችሁ ብታነቡ ለሀገራቸው ስለሰሯቸው ስራዎች ብዙ ታውቃላችሁ።
@tikvahethiopia

ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ህዳር 21 ቀን 1972 ዓ/ም ለንባብ ለበቃው “ታጠቅ” ለተሰኘ የሰራዊቱ ጋዜጣ በሰጡት ቃለምልልስ የተናገሩት ፦
“… እኛ ብንሞት ሌላ ሰው ይተካናል ፤ መተኪያ የሌላት ኢትዮጵያ ከሞተች ግን ተተኪው ትውልድ ስለሚሞት ዋጋ አይኖረውም፡፡
የሀገርን ሉአላዊነት በአስተማማኝነት መጠበቅ ቆራጥነት እና ልበ ሙሉነት ይጠይቃል፡፡
እኛ በሕይወት ቆመን እያየን ጠላት አንዲት ስንዝር መሬት ቆርሶ መሄድ ቀርቶ በአንድ እግሩ እንኳ ሊቆምባት አይችልም፡፡
ከሀገር ወዲያ ሌላ መኖሪያ ዋሻ ስለሌለ በሃገርና በነፃነት ጉዳይ ምንም ቀልድ ሊኖር አይችልም፡፡ ”