TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ጠርቷል ?

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፏል።

በሀገራችን በተከሰተ ሰላም እጦት ምክኒያት የዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደት መቋረጡን አስታውሷል።

ነገር ግን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ተማሪዎች ጥሪ እንዳስተላለፈ ተደርጎ እየተወራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው እስከ አሁን ምንም አይነት የጥሪ ማስታወቂያ #እንዳላስተላለፈ አስገንዝቧል።

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ይህን አውቀው አዲስ ማስታወቂያ ሲኖር #በተረጋገጡ የዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ እንደሚያሳራጭ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

@tikvahethiopia