TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዓድዋ

" ኢትዮጵያ ምን ጊዜም አሸናፊ ናት " - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ በተመረቀው " የዓድዋ ድል መታሰቢያ " እየተከበረ ይገኛል።

በዚሁ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መሪዎች፣ የተለያዩ ባለልስጣናት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ለመረዳት ተችሏል።

በዓሉ በሀገር መከላከያ ወታደራዊ ትርኢት እና በሌሎችም ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፥ የዓድዋ ድል ደማቅ ታሪክ የተጻፈበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

" ቀደም ሲል #ለትውስታ ብቻ ይከበር ነበር " ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ " ዘንድሮ ግን ድሉን የሚመጥን መታሰቢያ በዚህ ትውልድ ተገንብቷል " ብለዋል።

" የጦር መሪዎችን ጨምሮ ብሔር ብሔረሰቦች በመታሰቢያው መካተታቸውን የሚደነቅ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" የመከላከያ ሠራዊት የዓድዋ ጀግኖችን ሥራ ውርሱ አድርጎ ለሀገሩ በኩራት ዘብ ይቆማል " ብለዋል።

ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ " ሀገራችን ጠንካራ የመከላከያ ኃይል እንዳላት ለኢትዮጵያውያን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ " ነው ያሉ ሲሆን " የኢትዮጵያ መከላከያ ከሀገራችን አልፎ ለሌሎች ሀገራትም ኩራትና መከታ ነው ይህንንም የወደቀላቸው ይመሰክራሉ " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

" ኢትዮጵያ ምን ጊዜም አሸናፊ ናት፤ ዛሬም የዓድዋ ጀግኖች ልጆች መሆናችንን እያስመሰከርን እንቀጥላለን " ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia