TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SituationReport | #Amhara #Tigray #Afar

#UN_OCHA በአፋር ፣ ትግራይ እና አማራ ክልል ስላለው ሁኔታ እና እየተደረገ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴ ሪፖርት አውጥቷል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

- በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት 9.4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

- እኤአ ከህዳር 20 ጀምሮ ከትግራይ ምዕራብ ዞን ወደ ማይ-ፀብሪ፣ ሸራሮ እና ደደቢት ወረዳዎች በርካቶች ተፈናቅለው የገቡ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሽሬ በስተ ምዕራብ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደደቢት ብዙ ሺህ ሰዎች ደርሰዋል፤ አዲስ ተፈናቃዮች ፍሰት የቀጠለ በመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል።

- በትግራይ ክልል 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 400,000 ያህሉ በርሃብ መሰል ሁኔታ ላይ ያሉ ናቸው።

- በአፋር ክልል በዚህ ዙር በተደረገ ድጋፍ ከ86,000 በላይ ሰዎች ምግብ አግኝተዋል።

- በአማራ ክልል 3.7 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

- በአማራ ክልል በሰ/ወሎ፣ ዋግ ኽምራና ከፊል ደቡብ ወሎ እንዲሁም በአፋር ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ በተለይ በአኗኗር ፣ በገበያ መቋረጥ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ ባለመቻሉ አሳሳቢ ነው።

- በአማራ ክልል አዲስ ተፈናቃዮች አሁንም አሉ። በደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቃዮችን የሚያስተናግዱ የጋራ ቦታዎች ቁጥር ከስድስት ወደ 10 ከፍ ብሏል፣በተመሳሳይ በኮምቦልቻ ከ2 ወደ 17 ከፍ ብሏል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

@tikvahethiopoa
#SituationReport

#Tigray #Amhara #Afar

የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /UN OCHA/ ሪፖርት ፦

- ከጥር ወር ጀምሮ በትግራይ እና በአማራ ክልል 728 ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተለያዩ ህጻናት ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን ይህም ከጠቅላላው 9 በመቶውን ብቻ የሚወክል ነው ተብሏል።

- ግጭቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ በሰሜን ኢትዮጵያ በሶስቱ ክልሎች ከ1,000 የሚበልጡ ከፆታ ጥቃት በህይወት የተረፉ ሴቶች በጤና አገልግሎት ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።

- 500,000 የሚገመቱ ህጻናት ላይ ትኩረት ያደረገ ሰፊ የአመጋገብ ዘመቻ ለማካሄድ ከ5,700 በላይ እሽጎች ቫይታሚን ኤ ወደ አፋር ተልኳል።

- ይህ ሪፖርት በተዘጋጀበት ሳምንት በአማራ ከ 560 ሺህ በላይ ሰዎች የምግብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ፤ በአፋር ከ88 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲሁም በትግራይ ከ138 ሺህ በላይ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።

- በትግራይ ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት አንዳንድ አጋሮች ከታህሳስ 10 ጀምሮ የምግብ አቅርቦትን አቁመዋል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

@tikvahethiopia
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_3_Feb_2022.pdf
3.4 MB
#SituationReport

በተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (UNOCHA) ሪፖርቱን አውጥቷል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ውጥረት ያለበት እና ተለዋዋጭ መሆኑን ገልጿል።

ይህ ሪፖርት በተደረገበት ሳምንት በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ቢሆንም፣ በአፋር ክልል ከትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች መካከል በአባላ፣ በርሀሌ፣ ዳሎል፣ ኤሬብቲ፣ ኮኔባ እና መጋሌ ወረዳዎች ከፍተኛ ግጭቶች መከሰታቸው ታውቋል።

የተከሰቱት የቅርብ ጊዜ ግጭቶች የዜጎችን ህይወት ለአደጋ እያጋለጡ፣ በተለይ ከፍ ያለ የህዝብ እንዲፈናቀል እያደረጉና በህዝቡ ኑሮ ላይ ተጽዕኖ በማሳደር የሰብአዊ ፍላጎቶች እንዲጨምሩ አድርጓል።

ግጭቶቹ በአፋር ለተጎዱ አካባቢዎች ሰብአዊ አቅርቦት እንዳይደርስም ገድበዋል።

የአፋር ክልል ባለስልጣናት በቅርቡ በክልሉ በተቀሰቀሰው ግጭት ከ200 ሺ በላይ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አሳውቀዋል።

አጭር መረጃ፦

- በቅርቡ በአፋር ክልል በተቀሰቀሰው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንዲፈናቀሉ አድርጓል፤ ለሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነቱም አስቸጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል።

- በአማራ ክልል በቅርቡ በተካሄደው የስርጭት ስራ ከ811,000 በላይ ሰዎች እና ከ420,000 በላይ ሰዎች በቀድሞው የስርጭት ስራ ከጥር 24 እስከ 30 ባለው ጊዜ የምግብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

- በሰመራ-አባላ-መቐለ መንገድ ወደ ትግራይ የሚደርሰው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እኤአ ከታህሳስ 15 ቀን ጀምሮ በተፈጠረው ግጭትና የጸጥታ ችግር እንደተቋረጠ ነው።

- በአፋር ክልል ከ2,500 በላይ ህጻናት ከ1,000 በላይ ሴት ልጆችን ጨምሮ ይህ ሪፖርት በወጣበት ሳምንት መደበኛ ባልሆነ የትምህርት መርሃ ግብሮች የትምህርት ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።

*ሙሉ ሪፖርት በPDF ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_19_Feb_2022.png
#SituationReport :

#Tigray #Amhara #Afar📍

የሰሜን ኢትዮጵያ #ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ወይም #UN_OCHA የዚህን ሳምንት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

#Afar

• በአፋር የተለያዩ አካባቢዎች #አሁንም ግጭት ቀጥሏል። በዋናው ኮሪደር (A1) [አፋር ሰመራን ከመቐለ ትግራይ የሚያገናኘው] እና ትግራይ እና አፋር በሚዋሰኑባቸው ኤሬብቲ ፣ በርሀሌ እና መጋሌ ወረዳዎች ፣ በኡሩህ እና ዋህዲስ ቀበሌዎች፣ በሁሉም የኬልበቲ ዞን ግጭት መኖሩ ተመላክቷል።

• በአፋር ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። መጠነ ሰፊ መፈናቀል በመኖሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

• በአፋር ክልል በተከሰተው ግጭት እስካሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የተፈናቀሉ ሲሆን አብዛኞቹ በመጋሌ፣ በርሀሌ፣ ኮነባ፣ ኢረብቲ እና ዳሎል ወረዳዎች መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ። አካባቢዎቹ በመንገድ ሁኔታ እና በፀጥታ ስጋት ምክንያት ለሰብአዊ አጋሮች ተደራሽ አይደሉም።

#Tigray

• በትግራይ ክልል እ.ኤ.አ. የካቲት 12 በምስራቅ ዞን አፅቢ ከተማ ላይ በደረሰ የአየር ድብደባ የንፁሀን ዜጎች ህይወት መጥፋቱ እና ሰዎች መቁሰላቸውን ተመድ አመልክቷል። የተመድ አጋሮች እስካሁን የተጎጂዎችን ቁጥር ማረጋገጥ እንዳልቻሉ ተገልጿል።

• በትግራይ ክልል በአብዛኛው ሰሜናዊ ክፍል [ከኤርትራ ድንበር በሚዋሰኑ ቦታዎች] የተወሰኑ ቀበሌዎች በማዕከላዊ ዞን ራማ ፣ በምስራቅ ዞን ኢሮብ፣ በምስራቅ ዞን ዛላ አምበሳ ከተማ ጨምሮ ተደራሽ አይደሉም። በእነዚያ አካባቢዎች ላለፉት ጥቂት ወራት ምንም አይነት እርዳታ ሳያገኙ የቆዩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች አሉ።

• እኤአ ከታህሳስ 15 አንስቶ የፀጥታ ችግሮችና ግጭቶች ወደ ትግራይ ክልል በየብስ በ #ሰመራ- #አብዓላ- #መቐለ መንገድ እርዳታ እንዳይገባ እንዳገዱ ይገኛሉ። ከታህሳስ አጋማሽ በፊት ተፈቅዶ የነበረው የአቅርቦት መጠን በዋናነት በቢሮክራሲያዊ እክል ከሚያስፈልገው በታች በመሆኑ አሁን በፀጥታ ችግር እና በግጭት መንገድ መዝጋቱ ወደ ትግራይ ክልል የሚደርሰውን የሰብአዊ አቅርቦት ችግር የበለጠ እንዳባባሰው ተገልጿል።

• እ.ኤ.አ. ከሀምሌ 12 አንስቶ አጠቃላይ 1,339 የጭነት መኪናዎች ከሰመራ ወደ ትግራይ ክልል የገቡ ሲሆን ይህ በትግራይ ክልል ያለውን ሰፊ ​​የሆነ የሰብአዊ ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስፈልጉት አቅርቦቶች ውስጥ 8 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ተጨማሪ 17 የጭነት መኪናዎች ባለፈው ህዳር ወር ከኮምቦልቻ ፣ አማራ ክልል ወደ ትግራይ ገብተው ነበር።

• የዓለም ጤና ድርጅት-WHO የላከው የህክምና ቁሳቁሶች መቐለ ቢደርሱም አጋር አካላት በነዳጅ እጥረት ምክንያት በክልሉ ወዳሉ ጤና ተቋማት መላክ እና ማከፋፈል እንዳልቻሉ ተመድ ገልጿል። በተለይም ከ800 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ወዳስጠለለው የሰሜን ምእራብ ዞን ማድረስ አልተቻለም። በዞኑ ከአጠቃላይ የውስጥ ተፈናቃይ 1.8 ሚሊዮን 44 % ይሸፍናል።

• በሰሜን ምዕራብ ዞን ተፈናቃዮችን ባስጠለሉ ቦታዎች የእከክ በሽታ እና ወባ ኬዞች መጨመራቸው ተመላክቷል። ከ1,100 በላይ የእከክ በሽታ ኬዝ በ22 ሳይቶች ፣ከ1800 በላይ የወባ ኬዞች በዞኑ ከዓመቱ መጀመሪያ (የፈረንጆች) ጀምሮ ተመዝግቧል። የአቅርቦት ችግር፣ የመድሃኒትና የነዳጅ እጥረት ተመድ የጤና አጋሮቹ የበሽታዎችን ስርጭት እንዲቀንስ ለማድረግ የሚሰሩትን ስራ እየገደበ መሆኑን ገልጿል።

• ተ.መ.ድ. በትግራይ ክልል ላሉት የሰብአዊ ድጋፍ አጋሮቹ ያለው ነዳጅ፣ ጥሬ ገንዘብ እና አቅርቦቶች በጣም አነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ ይህም ሁኔታ የሰብአዊ አገልግሎቶችን በተለይም የምግብ ፣ የውሃ ፣ የጤናና የስነ - ምግብ አገልግሎቶች ስርጭትን በእጅጉ እየቀነሰው መሆኑን አመልክቷል።

#Amhara

• በአብዛኛው የአማራ ክልል በአንጻራዊ የተረጋጋ ሁኔታ ያለ ሲሆን በሰሜን ወሎ በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ ግን ውጥረት እንደነገሰበት ነው።

• አማራ ክልልን ከትግራይ ክልል የሚያዋሱ አካባቢዎች አሁንም ባለው የፀጥታና የደህንነት ስጋት ተደራሽ አይደሉም። መድረስ አልተቻለም። ይህም በሰሜን ጎንደር፣ ዋግ ኽምራና ሰሜን ወሎ ያሉ አካባቢዎች ያካትታል። ባለው ሁኔታ ህዝቡ የአስፈላጊ የምግብ እደላ ጨምሮ አጠቃላይ ሰብአዊ ርዳታ እንዳያገኝ ሆኗል።

• በሰሜን ጎንደር ፣ ዋግ ኽምራ እንዲሁም ሰሜን ወሎ ዞኖች አካባቢዎች አዲስ መፈናቀል መኖሩ ተመላክቷል።

• በዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው። በርካታ ሰዎች በተደጋጋሚ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በአዋሳኝ አካባቢ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖች ውስን የሰብዓዊ ዕርዳታ ብቻ እንዳገኙ ተገልጿል። በዋግ ኽምራ በዋናነት በዝቋላ ወረዳ እና ሰቆጣ ወረዳ በአሁኑ ወቅት ከ30,000 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።

• ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ12,000 በላይ ሰዎች ሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት ወደ ራያ ቆቦ አማራ ክልል ገብተዋል።

• በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ ከ21 ሺ የሚበልጡ ተመላሾች አስቸኳይ የመጠለያ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የመኖሪያ ቤታቸውን መልሶ የማቋቋም እና የመልሶ ግንባታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በዞኑ ሆስፒታሎችና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶችና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የመንግስት ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_3_Mar_2022.pdf
#SituationReport

#Tigray #Amhara #Afar📍

የሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ የዚህን ሳምንት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

#Afar📍

- በአፋር ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል። በተለይም በራህሌ፣ ኢሬብቲ፣ ኬልቤቲ ዞን (ዞን 2) ውስጥ የትጥቅ ግጭቶች መኖራቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በአፋር እየተካሄደ ያለው ግጭት የሰብአዊ ድጋፍ መርሃ ግብሮችን እያደናቀፈ ፤ የሲቪሎችን ህይወት፣ ደህንነታቸውን አደጋ ላይ እየጣለ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄደው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥርም የሰብአዊ ፍላጎቶችን እየጨመረው ይገኛል።

- በአፋር ክልል ዞን 4 መረጋጋት በመፈጠሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የውስጥ ተፈናቃዮች ወደ ቀደመው ቀያቸው ተመልሰዋል።

- በዞን 2 በቀጠለው ግጭት ምክንያት ተጨማሪ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። ተፈናቃዮቹ በተለይም ከአባላ፣ ኢረብቲ፣ በረሃሌ፣ መጋሌ እና ዳሎል ወረዳዎች መሆናቸው ተገልጿል። አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በአሁኑ ወቅት በዳሎል፣ አፍዴራ፣ ሲልሳ/ጉያህ እና ሰመራ እየተጠለሉ ሲሆን አንዳንድ ተፈናቃዮች ደግሞ ራቅ ባሉ እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ነው ያሉት።

- የተመድ አጋሮች በተደራሽነት ውስንነት ምክንያት በዞን 2 የሚገኙትን የተፈናቃዮች ቁጥር ማረጋገጥ አልቻሉም።

- ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ ከአፋር የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች በትግራይ ክልል በሚገኙ ጥቂት ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ።

#Tigray 📍

- አሁን ላይ የ ሰመራ - አብአላ - መቐለ መስመር መዘጋት ወደ ትግራይ የሚደርሰውን የሰብአዊ አቅርቦት የበለጠ አባብሶታል። ሰብዓዊ አቅርቦቱ ከታህሳስ አጋማሽ በፊት ከተፈቀደው ውስን አቅርቦት ጋር ተዳምሮ በዋነኛነት ቀደም ባሉት አስተዳደራዊ ርምጃዎች ምክንያት ሰብዓዊ አቅርቦቱ ከሚያስፈልገው በታች ነበር።

- እኤአ ከሃምሌ 12 ጀምሮ አስፈላጊውን የሰብአዊ አቅርቦት ከያዙ 16,500 የጭነት መኪናዎች ውስጥ 8 በመቶው ብቻ ትግራይ ገብተዋል። በዚህም የተመድ ሰብአዊ አጋሮች ተግባራቸውን መቀነሳቸውን ቀጥለዋል።

- ይህ ሪፖርት በተዘጋጀበት በዚህ ሳምንት የሰብአዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች 47 ሜትሪክ ቶን የህክምናና የስነ ምግብ አቅርቦቶችን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቐለ በበረራ አድርሰዋል። ይህ እኤአ ከጥር 24 አንስቶ በበረራ ወደ ትግራይ የገባውን አጠቃላይ አቅርቦት 144 ሜትሪክ ቶን አድርሶታል።

- በዚህ ሳምንት ወደ ትግራይ ከቀረበው አቅርቦት መካከል 10 ሜትሪክ ቶን የተመጣጠነ ምግብ (Ready to Use Therapeutic Food - RUTF) ይገኝበታል። ይህም ከታህሳስ አጋማሽ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባ ሲሆን በመቐለ፣ በምስራቅ እና ደቡብ-ምስራቃዊ ዞን ይከፋፈላል። ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ለመንከባከብ ይውላል።

- ባለፉት ሳምንታት ወደ መቐለ የደረሱ የህክምና ቁሳቁሶች ይህ ሪፖርት በተዘጋጀበት ሳምንት ወደ ምስራቅ ዞን ውቅሮ እና ዓዲግራት አጠቃላይ ሆስፒታሎች፣ ወደ ማዕከላይ ዞን ዓድዋ፣ አክሱም፣ አቢአዲ ጠቅላላ ሆስፒታሎች እና አክሱም ሪፈራል ሆስፒታል፣ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ ስሁል ሽሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ተከፋፍለዋል።

- አሁንም የነዳጅ እጥረት ቀሪዎቹን ቁሳቁሶች ለማከፋፈል እንቅፋት እንደሆነ ነው።

- በትግራይ አሁንም የህክምና ቁሳቁሶች ችግርና የተወሰኑ አይነት መድሃኒት እጥረቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል HIV ላለባቸው ሰዎች ሚሰጥ መድሃኒት ይጠቀሳል፣ የHIV መመርመሪያ ኪት፣ የፀረ ራቢስ መድሃኒት፣ የኮሌራ ክትባት እጥረትም አለ።

#Amhara 📍

- በአማራ ክልል አንዳንድ ' ከትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ' አሁንም ተደራሽ አይደሉም። በተለይም በሰሜን ጎንደር ፣ ዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ያሉ አካባቢዎች እጅግ አሳሳቢ ሲሆኑ አልፎ አልፎ በሚከሰቱት ግጭቶች ምክንያት ሰዎች ወደ ዝቋላ ፣ ሰቆጣ ፣ ቆቦ እና ዛሪማ መፈናቀላቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉ።

- በሰቆጣ እና ዝቋላ ከ40 ሺ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚኖሩ ይገመታል።

- በአማራ ክልል በዘጠኝ ዞኖች እኤአ ከታህሳስ እስከ ጥር ባለው ጊዜ ውስጥ በ " Find -and - Treat " ዘመቻ ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ህጻናትን የመለየት ዘመቻ የተካሄደ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 21,804 ህጻናት ወይም 1.1 በመቶው ህጻናት በከፋ የምግብ እጥረት (SAM) ተጠቅተዋል።

- በምስራቅ አማራ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 14 ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው 'find and treat' ዘመቻ እስካሁን ምርመራ ከተደረገላቸው 293,208 ከ5 አመት በታች ህጻናት 8,160 SAM ኬዝ ወይም 2.7 በመቶና 48,118 GAM ኬዞች ወይም 16.4 በመቶ ተገኝቷል። ምርመራ ከተደረገላቸው 52,828 ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ውስጥ 21,687 ሴቶች ወይም 41 በመቶው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አለባቸው ተብሏል።

#UNOCHA

@tikvahethiopia