TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያን ያስቆጣው የሀርቪስቶ አስተያየት :

ከ3 ቀን በፊት የፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ለአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ነበር።

በዚህ ሪፖርታቸው ላይ ስለ #ትግራይ ጉዳይ የተናገሩ ሲሆን በይበልጥ ግን የብዙሃን መነገሪያ የሆነው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በነበረኝ ቆይታ፥ "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት #የትግራይ_ተወላጆችን_ለማጥፋት እንደሚፈልጉ /ታጋሩዎችን ለ100 ዓመታት ማጥፋት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል" ብለው የተናገሩት ነው።

የትኛው የኢትዮጵያ ባለስልጣን ይህን እንዳለ / ሲናገር እንደሰሙት ግን በስም ገልፀው ሲናገሩ አልታዩም።

ሀርቪስቶ የአውሮፓ ህብረትን በመወከል ለጥቂት ቀን በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገው እንደነበር አይረሳም።

ፔካ ሀርቪስቶ ከቀናት በፊት ያቀረቡት አጠቃላይ ሪፖርት ኢትዮጵያን ክፉኛ አስቆጥቷል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሀርቪስቶ ያቀረቡት ሪፖርት ኃላፊነት የጎደለው፣ መሰረት የሌለው፣ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ያልተከተለና ከቅኝ ገዢነት የመነጨ ነው ብሎታል።

ሚኒስቴሩ “ፔካ ሃቪስቶ መንግስት እያከናወነ ያለውን ስራ የሚያጣጥል እና በሐሰተኛ መረጃዎች የተመሰረቱ ሪፖርቶችን፣ ውሸቶችን በማቅረብ ተገቢ ያልሆኑ ጣልቃ ገብነቶች እንዲኖሩ አድርጓል” ብሏል።

በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ ፔካ ሃቪስቶ ከጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ፣ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ከም/ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አውስቶ፤ የቀረበው ሪፖርት ግን ሃሰተኛና የተካሄዱ ሰፋፊ ውይይቶችን ያላካተተ መሆኑን ተገልጿል።

* የፔካ ሀርቪስቶ ሪፖርት ፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia